ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፤ እርሱ ብቻ ደግሞ ራስዋ ነው። የሚያምርና የተንቆጠቆጠ ካቴድራል አልያም ጽርሐ ወንጌል ላይኖራት ይችላል። አማኞቿ ጥልቅ ድኾች፣ ደምግባት አልባ፣ ያልተማሩ ገበሬዎች አልያም ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ቢኾኑም፤ በክርስቶስ ፊት እኩልና አንድ፤ ኹሉም ለክርስቶስ በኵራት ናቸው። በጌታ ቤት ታላቅና ታናሽ የለምና!
Friday, 29 October 2021
በአንድ ቀን የወደቀ የለም!
“ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።” (መዝ. 19፥12)
ሔዋን ከእባብ ጋር በማይጠቅምና በማያንጽ ወሬ መዘግየቷ ዋጋ አስከፍሎአታል (ዘፍ. 3፥1-6)፤ የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሳዖል ውድቀቱ የጀመረው፣ ትንሽ ከምትመስል ነገር ግን አደገኛ ከኾነ ክፉ የባልንጀርነት ቡድን ውስጥ መሳተፉ ነው (1ሳሙ. 14፥2-3)፤ ጅማሮው መልካም የነበረው ያ ንጉሥ በፍጻሜው፣ ጠንቋይ እንደ ፈለገ፣ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዘ ክፉ ሞት ሞተ፡፡ ሳምሶንን የሚያህል ብርቱ አገልጋይ፣ የመውደቁና የመንኮታኮቱ ጅማሮ፣ “ሶምሶንም ወደ ተምና ወረደ፥ በተምናም ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አየ።” (መሣ. 13፥1) ከምትል ቀላል ሐረግ ነው፡፡
Wednesday, 20 October 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲፬)
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት
የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ ስለ ነገረ
ድኅነት ያን ያህል ሰፊ ጽሑፍ ሲጽፍ፣ አንድም ቦታ ከውኃ ጥምቀት በስተቀር ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አለመጻፉ፣ ምን ያህል
ከመንፈስ ቅዱስ እውነት፣ ከኢየሱስ ትምህርትና ሕይወት መራቁን፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን ኃይል ባለማወቅ እንዴት እንደ ሳተ
እንመለከታለን።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን፣ በግልጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በሚገባ ያስተምራል፤ ደግሞም ከነገረ ድኅነት ጋር ተያያዥና ቊልፍ ትምህርት መኾኑን በሚገባ እናስተውላለን። የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መመልከት እውነታውን እንድናስተውል ይረዳናል።
Thursday, 14 October 2021
“ለምን ሄዱ?” አንልም!
(ይህ ጽሑፍ፣
በእውነተኛ ልብ ወንጌልን በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ውስጥ ለማድረስና ለሚሽነሪ አገልግሎት በሕይወታቸው ተወራርደው የሚያገለግሉ ታማኝ
አገልጋዮችን አይመለከትም!)
ለምን አንልም?
ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ከውስጥ በሚነሳ አሸናፊነትና “ዘገምተኛ” በኾነ ጽኑ የፍቅር መንገድ የሚያሸንፍ እንጂ፣ በግድና በኃይል ማንንም መያዝና አብሮት እንዲኖር አይፈልግም። ጽድቅን ወዳዱ ጌታ፣ ጽድቅን ያደርግ ዘንድ የምድርን የታችኛው ክፍል በትእግሥት ዝግታ ረግጦ መራመዱ ይህን እውነታ በአድናቆት ያሳየናል! ከዚህ በተቃራኒ ግን “ሰሞነኞቹ”፣ እንደ 1980ዎቹ ትውልዶች፣ “‘እስክንድያ እናቴ’ ኦርቶዶክስ ሃይማኖቴ” ብለው መሄዳቸውን ስናይ ምን እንላለን? ምንም!
Wednesday, 6 October 2021
አትደነቁ!
“ወዳጆች ሆይ፥
በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤” (1ጴጥ. 4፥12)
ቅዱስ ጴጥሮስ በአማኞች መካከል እንደ እሳት የሚፈትን ፈተናና መከራ ሊነሣ እንደሚችል በግልጥ ያስተምረናል። የፈተናው መነሻ ደግሞ እዚያው መካከላችን መኾኑንም ጭምር፤ አዎን! ከኢየሱስ ጎን ይሁዳ፣ ከጳውሎስ ጎን ዴማስ፣ ከዮሐንስ ጎን ዲዮጥራጢስ፣ ከኤልሳዕ ጎን ግያዝ … መኖራቸው እንግዳና ልዩ ነገር አይደለም። ዛሬ ላይም እንዲህ ያሉ ወገኖች መነሳታቸው ፈጽሞ አይደንቅም፤ አይገርምም። ገንዘብን ለማካበት መጐምጀት፣ ተሰሎንቄን አይቶ ከቅድስና መልፈስፈስ፣ በወንድሞች ላይ የጐበዝ አለቃ ለመኾን መቋመጥ … ያኔም ነበረ፤ አኹንም መኖሩ አይደንቅም፤ አይገርምምም!
Tuesday, 5 October 2021
“ኑ! አለቃ ሹመን እንመለስ” ለምትሉ!
ከሰሞኑ ጯኺ መፈክሮች ውስጥ፣ “ወደ ተቋማዊው ኦርቶዶክስ (institutional Orthodox) እንመለስ” የሚለው አንዱ ነው። የሚመለሱበት የአብዛኛዎቹ ምክንያታቸው ደግሞ፣ “‘ተሐድሶ’ ወደ ወንጌላውያን አፍላሽ ኾኖአል እንጂ፣ በራሱ መቆም ያልቻለ ነው፤ ስለዚህም ወደ ተቋማዊው ኦርቶዶክስ ተመልሰን አስቀድመን ከጴንጤነት እንዳን፤ ቀጥለን ደግሞ በኦርቶክሳዊ መንገድ ‘ክርስትናን’ እንስበክ” የሚል ነው። እኒህ ሰዎች፣ አኹን ላይ፣ ወደ ተቋማዊው ኦርቶዶክስ መመለስን ቀለል አድርገው ሲናገሩ፣ በወንጌላውያን “pulpit” ላይ የማርያምን ምልጃ ብንሰብክ፣ ከልካይ የለንም ባይ ፍጹም ተላላዎች ይመስላሉ!
Monday, 4 October 2021
የአፈግፋጊዎቹ ሰበብ!
አንድ የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን አባባል አለ፤ “በምድር ላይ ፍጽምት ቤተ ክርስቲያን የለችም፤ ምናልባት ካለች፣ አንተ የገባህባት ቀን ፍጽምናዋን ታጣለች” ይላል። ሙሉ ለሙሉ ባልተዋጀው ዓለም ስንመላለስ ፈተናና ውጊያ፤ መሰናክልና ወጥመድ፣ መከራና ተግዳሮት አለብን፤ ጌታችን ኢየሱስ ራሱ፣ “እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤” (ማቴ. 10፥16) ብሎ ተናገረን እንጂ፣ ወደ ሰላማውያንና ፍጹማን አማኞች ወይም ማኅበረ ሰቦች ዘንድ እልካችኋለሁ አላለንም። እናም ውጊያችን ፈርጀ ብዙና በዚህች ምድር ላይ እስካለንም ድረስ የማያቋርጥም ነው።
Sunday, 3 October 2021
የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ተሐድሶና ከዳተኛ ወንድማቸው
እስጢፋኖሳውያን፣
የወንጌላውያን ተሐድሶ በአውሮፓ ከመጀመሩ ከዓመታት በፊት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የወንጌል ችቦ እንደ ለኮሱ ይታመናል፤ አንዳንዶች የተሐድሶ
አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ አጭር ታሪክ ያለው ይመስላቸዋል። ነገር ግን እስጢፋኖሳውያን በኢትዮጵያ ውስጥ አስደናቂና ወንጌላዊ
የኾነ ተሐድሶ አሥነስተው ለብዙዎች መዳንና ከጨለማው ዓለም ማምለጥ ምክንያት ኾነዋል። የዚህን ዘመን ክስተት፣ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ታላቅ ዕድል እንደ ነበርና እንዳልተጠቀመችበት የደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን ገድል በጻፉት መጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ።