Friday, 30 August 2013

"ነገር ሁሉ ለበጎ አይደለም !!! "

Please read in PDF
      የመጽሐፍ ቅዱስን ሙሉውን ሃሳብና መለኮት ለእኛ ያለውን ዘላለማዊ እቅድ ማወቅና ማመን የሚቻለን የተነገረውን ቃል በትክክል ማንበብና መረዳት ሲቻለን ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ሐሳብ እጅ ጠምዝዞ የመተርጎምና ከተነገረለት አላማ ውጪ አመሳስሎ ማቅረብ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ አሁን በእኛ ዘመን በሚያሳዝን መልኩ ይስተዋላል፡፡
         "እግዚአብሔርን እንወደዋለን እናመልከዋለን" የሚሉ ብዙ ሰዎች እርሱን መውደድና ማምለክ ማለት መነሻውና መድረሻው ለእርሱ ቃል መገዛትና ቃሉን ማክበር መሰረት እንደሆነ ቢያስተውሉ እንዴት የተወደደ ነበር!!! ለቃሉ ክብርን ሳይሰጡ "እግዚአብሔርን " እንወደዋለን ማለት በሌላ ትርጉም የአምልኮ መልክ ይዞ ሙሉ ኃይሉን ከመካድ እኩል ነው፡፡

Tuesday, 27 August 2013

የእግዚአብሔር መላዕክት ደስታ

       ባዕለጠጋውና ምንም ያልጎደለበት ትልቁ እግዚአብሔር መልኩን  የሚመስል (የጸጋ እውቀት ያለውና ህያው ሆኖ እስትንፋሱን የተካፈለ) እንደምሳሌውም (ገዢነትና ስልጣንን ሁሉ ከሰማይ በታች ያለውና በራሱም ነጻ ፈቃድ መወሰን የሚቻለውን) ክቡር ፍጡር ሰውን ፈጠረ፡፡ እንዲሰግድለት፣ እንዲገዛለት፣ ባርያ ሆኖ እንዲያገለግለው፣ እንዲያመልከው አልፈጠረውም  … እርሱን መስሎ የእርሱ የሆነውን እስትንፋሰ መለኮቱን እንዲካፈለው ፈጠረው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የእርሱ የሆነውን እንዲወርስና እንዲካፈል ፈጠረው፡፡ ባሕርይው ቅዱስ የሆነ ጌታ አመስጋኝ ባይኖር የተመሰገነ ምስጉን የተቀደሰ ቅዱስ ነው፡፡ አመስጋኝ ባይኖር እግዚአብሔር ምስጉን ነው፡፡

Saturday, 24 August 2013

ባዶ ትምክህት!



የቄስ ዘር ነኝ የጻድቅ
ጎመን ዘሬ ሊቃሊቅ
እኔ እንዲህ ነኝ ምንትስ
የዚያ ወገን ቅብርጥስ

Tuesday, 20 August 2013

ራስን በልክ አለማየት


    የንስሐ ልብ ያለው ተነሳሒ ሰው የመጀመርያ ጠባዩ ራሱን በልኩ ማየቱ ነው፡፡ በየትኛውም ጊዜ ለመጸጸት፣ ይቅርታ ለመጠየቅና በግልጥ ኃጢአቱን ተናዞ ንስሐ ለመግባትም ራሱን ያዘጋጀ ብርቱ ሰው ነው፡፡ በመንፈሳዊውና በዓለማዊው ህይወት ራስን በልክ እንደማወቅ ያለ ታላቅነትና አሸናፊነት ያለ አይመስልኝም፡፡ እንዲህ ያለ ሰው ምን ቢሆን እንደሚሸነፍ ምን ቢያደርግ እንደሚረታ ስለሚያውቅ ተግዳሮትን ማለፍ ድልንም መቀዳጀት ይችልበታል፡፡
         ሁሉን እንደሚችሉ ማሰብና ሁልጊዜ የቀዳሚነቱን ሥፍራ ያለጌታ ለመጨበጥ መቋመጥ ከጎልያዳዊ መንፈስነትና ውድቀት አያዘልልም፡፡ ጎልያድ ምናልባት ቁመቱ ስድስት ጫማ ያህል ሁለንተናው በብረት የተጋጠመና የማይረታ ቢመስልም ልኩ የነበረው ግን መታጠቂያውን በወግ እንኳ ባልታጠቀው በዳዊት ኮሮጆ የነበረችዋ ሚጢጢዬዋ ጠጠር ነበረች፡፡በወንጭፍ ተወንጭፋ ከአናቱ ተሰክታ የጣለችው፡፡

Sunday, 18 August 2013

የምስክርነታችን ማህተም

   Please read in PDF
     ከገሊላ ባህር በስተሰሜን ከሔርሞን ተራራ ተዳፋት ሥር ባለችው የፊሊጶስ ቂሳርያ በምትሆነው ከተማ ፍጹም ሰው የሆነው ኢየሱስ ቀላል ግን ሰማያዊ መገለጥ ከሌለበት የማይመለስ ጥያቄ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው ፡፡(ማቴ.16÷13)፡፡ደቀመዛሙርቱ ሰዎች የሚሉትን ብዙውን ተናገሩ፡፡ዋናው የተፈለገው የእነርሱ ሐሳብና መልስ ነበር፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ ከሁሉም ቀድሞ በሰማያዊ መገለጥ በሥጋ ተገልጠህ ያየንህ ፍጹም ሰው የእግዚአብሔር ልጅም የሆንክ ፍጹም አምላክ ነህ ብሎ መሰከረ፡፡
https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEiQAc1b0AaCff1Z3E3LQosXOJq8pbSAnWbdz7-QSoPEyx7BlOwuV5SPIPplRFhT6knlKj2TV4LWfWzKbKd_6x65Kxr3w5yLgkZVyktchQoutWIshJxc50laFHZcH0V2RUSTZVDGiYfnNOY/s320/life-of-jesus-pic-08.jpg

Monday, 12 August 2013

የገሊላዋ ናዝሬት እመቤታችን



ቅድስት ድንግል ማርያም መኖርያዋና እድገቷ የዛብሎን ነገድ ድርሻ በምትሆነው በተራራማዋ ሐገር በገሊላ ናዝሬት ከተማ እንደሆነና ጌታ ኢየሱስንም በዚያ ፀንሳ በኋላም እንዳሳደገችው ታላቁ መጽሐፍ ይነግረናል፤ (ሉቃ.1÷26-272÷39-50)፡፡ ናዝሬት በብሉይ ኪዳን ካልተጠቀሱት ከተሞች አንዷ ስትሆን ብዙ የማትታወቅም ነበረች፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ከተማይቱ ምንም አይነት በጎ ገጽታ አልታየባትም፡፡  ይልቁን ከተማይቱ ፈጽሞ ተስፋ የተቆረጠባትና አንዳች መልካም ነገር አይገኝባትም የተባለችም ናት፤ (ዮሐ.1÷47)፡፡

Wednesday, 7 August 2013

ታናሽነት


         እግዚአብሔር ሥራውን የሚሰራው እንደሰው ልማድ አይደለም፡፡ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በእኛ ታሪክ ውስጥ ለእኛው ቢሆንም የሥራው ዋና ባለቤት እግዚአብሔር  ሥራውን እንደፈቃዱ ብቻ እንደሰራ በመንፈስ ከሆንን ማስተዋል አያዳግተንም፡፡
         ታናሽነት በሰው ፊት ከማይፈለጉና  ከሚናቁ ነገሮች የመጀመርያ ተርታ ላይ ያለ ነገር ነው፡፡ እንደሰው ልማድ ታላቅና የመጀመርያ መባል የሚያስከብርና ቦታን የሚያሰጥ ሥፍራ ነው፡፡ ስለዚህም ታላቅና የመጀመርያ ለመባል የማያባሩ እልፍ እልቂቶችና የመጨካከን የጦርነት ዘመኖችን ምድራችን ከማተናገድ አላረፈችም፡፡
           ሁላችን የእጁ ፍጥረቶች ሆነን ተፈጥረን ሳለ (ሸክላ ሰሪው ጌታ የሚያድፍ የመሰላቸው በዝሙት የሰከሩ አንዳንዶች "እጁን ታጥቦ" የፈጠረሽ ሲሉ ባያፍሩም) በቁሳዊው ነገር ለመበላለጥ ህያው አካል ያለውን ነፍስ ለማጥፋት መሮጣችን ላስተዋለው ከነውር የከፋ ድርጊት ነው፡፡ በተቃራኒው በእግዚአብሔር ከተወደዱ መልካም ነገሮች  ያልተናቀን ፣ዝቅ ያለን ታናሽነት እንደሚመርጥ ስናይ "ሥራህ ግሩም" ጌታ ነህ ብለን እጅን በአፍ እንጭናለን፡፡

Sunday, 4 August 2013

እረግጣለሁ ገና



የአሸዋ ላይ ሕንፃ ለነፋስ እስክስታ
የነፋስ ላይ ጐጆ ለእሳት ተሰጥታ
የውኃ ላይ ኩበት ዝም ብሎ ጉዞ
ዕረፍት አልባ ትጋት ፈዞና ደንግዞ

Friday, 2 August 2013

የተሰሎንቄ እብዶች


     በቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞዎች ከማይረሱ ከተሞች መካከል አንዷ ተሰሎንቄ ናት፡፡ ከአውሮፓ ወደእስያ ለሚዘዋወረው ሰውና ንግድ ዋና የባህር በር ሆና የሰረገላም መንገድ ተሰርቶባት ያለችግር መመላለሻ ነበረች፡፡ከተማይቱ ብዙ የአይሁድ እምነት ተከታዮች ያሉባትና እኒህም ምኩራብ ሰርተው ያመልኩ የነበሩ ናቸው፡፡
        የሐዋርያት ሥራን የዘገበልን ቅዱሱ ተጓዥ ሉቃስ ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚህች ከተማ መጥቶ ሦስት ሰንበት ያህል ከመጽሐፍ እየጠቀሰ " … ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ፦ ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው" እያለ ተርጉሞ በማስተማሩ "ከእነርሱም አንዳንዶቹ ተረድተው ከሚያመልኩም ከግሪክ ሰዎች ብዙ ከከበሩትም ሴቶች ጥቂቶች ያይደሉ፥ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ" ይለናል (ሐዋ.17÷1-4)፡፡