Saturday, 30 March 2013

መፃጉዕ ነኝ ልጅህ


Please read in PDF

ቁስሌ የሸተተ ነውሬ የተገለጠ
ነፍሴ የዘር ቃልዋ በክህደት ያረጠ
ስጋዬ በኃጢአት ጤናው የታወከ
መንፈሴ በፍርሀት ጽናቱ የተናደ
ውስጤ የተጎዳ ደህንነት የራቀኝ
 አቤቱ ጌታዬ እኔ መፃጉዕ ነኝ!!
ልቤ በክፋት የተላ
ሰውነቴ በእባጭ የፈላ
ፈነዳድቶ አፉን ከፍቶ 
ውስጤ በሀዘን ተመቶ
እግሬ ተሰባብሮ እጄ ተስኖት ማገልገል
ውሀ ቋጥሮ በንፍገት መግል
አቤቱ አትለፈኝ ተመልከተኝ
መፃጉዕ ባርያህን ራርተህ ፈውሰኝ
እንኳን መድኀኒቱን መች ለይቼ በሽታዬን
አለሁኝ በፊትህ በመዝራት እንባዬን
ስቃይ ሆኖብኝ  በደጅ በቤቴ
 አቃስታለሁ ገርጥቶ ፊቴ
ማረኝ መድሀኒቴ በመሐሪው ስምህ
አልጋ ላይ ባልተኛም መፃጉዕ ነኝ ልጅህ
አልጋ የያዘማ አውቆ ተሸንፎዋል
የእኔ ለብቻ ነው!!
        ቆሜ እየሄድኩኝ ሰውነቴ አልቆዋል
ነፍሴን ፈውስልኝ ወልደ ዳዊት መሲህ
ስብራቴ ይጠገን ለውጠኝ በቃልህ
ልነሳ ከአልጋዬ ፍታኝ አርነቴ
ሁሌ እንድቀኝልህ ተስለህ ከፊቴ።


No comments:

Post a Comment