Friday, 29 March 2013

ትንሽ ነኝ! አትበል

Please read in PDF

ከትልቁ ቤተ መቅደስ
በአገልግሎቷ ሳታንስ
ከብራ በቅድስና፥ ረብቦባት መንፈሱ
ነፍሳት ለዘወትር እንደውኃ ሲፈሱ

በንስሐ ለቅሶ ከለመዱት ኃጢአት ልባቸው ተሰዶ
ከልብሳቸው ይልቅ ልባቸው ተቀዶ                              
ከምሕረቱ ምንጭ ተቃጥለው በጥማት
ሲሹ ፍለጋውን በትንሿ ምኩራብ
ሁሌ መልስ አላቸው ከሰማዩ አምላክ፡፡

ምኩራብ አካልህን ስትቀድስ ለጌታ
መሥዋዕት ልታቀርብ በአርምሞ በእልልታ
የክፋትን አጸድ የመርገምን መንገድ
የሞትን መሠውያ የኃጢአትን ሕንጻ ገልብጠህ ልትንድ
ከሥር መሠረቱ ደምስሰህ ልትሽር
የመርገምን ተክል
አጥፍተህ ልትነቅል
ትንሽ ነኝ! አትበል  ምንም የማልረባ
ሥጋህን ቀድሰህ ሥራ ልትሠራ
ትንሽ ነኝ! አትበል አንደበቴ ያልቀና
ኸረ አይሆንም ከቶ አልበቃሁም ገና፡፡

ልትሠራ ልትተክል ጽድቅን ልትመሰክር
ትንሽ ነኝ! አትበል፡፡
በትንሿ ምኩራብ ብዙ ጸሎት ሰምሯል
ባንተ በትንሹ ብዙ ሊሠራብህ
የተቆረጠ ሃሳብ ከፈጣሪህ ወጥቷል፡፡


1 comment: