Friday, 27 September 2019

Lallaba gowwummaa (1Qoro. 1:21)

Please read in PDf
  Waaqayyoon ilma namaa cubbuudhaan bade jiru gara qulqullumaa fi qajeelumaatti deebisuuf; ilma isaa tokkicha Goofta Yasuus Kiristoos gara biyya lafaatti ergee jira. Ilmi isaa tokkichaan haalli inni gara biyya lafaatti ittiin dhufe bayyee kan nama haawachisuufi gammachiisu miti. Tasumaa karaan itiin dhufe kabajaa fi jaalatamummaa biyya lafaa barbaadu hundaaf faallaa ta’eti.



Wednesday, 25 September 2019

ሾላኮቹ (ክፍል ፭)


Please read in PDF
ሾላኮች በምን ይታወቃሉ?
   አማኞች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመናቸው የክርስቶስ ሕይወትና ትምህርት የሚያንጸባርቅ ሕይወት ሊኖሩ ተጠርተዋል፤ ጌታችን ኢየሱስ ቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱን እንደ ተናገረው፣ “ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።” (ዮሐ. 15፥16) እንዳለው፣ ደቀ መዛሙርት ፍሬ ሊያፈሩና በፍሬአቸውም ኖረው ሊታዩ ተጠርተዋል። ፍሬ ኹለንተናዊ መገለጫ ነው፤ ጠባያችን፣ አስተሳሰባችን፣ ንግግራችን፣ ድርጊታችን … ኹሉ የፍሬያችን መገለጫ ወይም የኖርንበት መታያችን ነው።


Monday, 23 September 2019

ሾላኮቹ (ክፍል ፬)

Please read in PDF
 ባለፈው በተመለከትነው ክፍል ሾላኮቹ ማንን ያስታሉ? ብለን በቀዳሚነት ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሰን  “ውነትን ማወቅ የማይወዱ ሞኞች ሴቶችን” እንደሚያስቱ ተመልክተናል፤ ዛሬ ደግሞ የዚኹን ቀጣይ ክፍል እንዲህ እንድታነቡት ጋብዛችኋለሁ፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፤ አሜን።
2.      ዳዲስ አማኞችን፦ አዳዲስ አማኞች ለቃለ እግዚአብሔር ጥማት የተጋለጡ ናቸው፤ ከቃለ እግዚአብሔር ጋር የተያያዘ ማናቸውንም ትምህርቶች ለመስማት ይቸኩላሉ። በተለይም ሾላካ መናፍቃን የሚጠቅሷቸውንና እውነተኛ መምህራን የሚጠቅሷቸውን እውነተኛ ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በማነጻጸር የትኛው እውነተኛና የትኛው ደግሞ ሾልኮ እንደ ገባ የመለየትና የማስተዋል እንከን አለባቸው።

Wednesday, 18 September 2019

ሾላኮቹ (ክፍል ፫)

Please read in PDF

   በባለፉት ኹለት ክፍሎች የመናፍቃንን የሾላካነት ጠባይ መመልከታችን አይዘነጋም፤ ከዚያ በመቀጠል ዛሬም እንመለከታለን፤ የጌታ ጸጋና ሰላም ከኹላችሁ ጋር ይኹን፣ አሜን፡፡
4.      ዩነትን ወይም እንግዳ ዘርን ለመዝራት፦ ጌታችን ኢየሱስ እንክርዳድ ዘሪው ክፉ፣ ማንም ሳያየው በሌሊት ወይም ጨለማን ለብሶ በመሹለክ ተግባር እንዳደረገው ነግሮናል፤ ጠላት እንክርዳድ የዘራው በዚያው መልካሙ ዘር በተዘራበት እርሻ ላይ ነው፤ አበቃቀሉም ኹለቱም በአንድነት በቀሉ፤ የስንዴውም የእንክርዳዱም አበቃቀላቸው ተመሳሳይና አንዱን ከሌላው ለመለየት እጅግ አዳጋች እንደ ኾነ፣ “እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም” (ማቴ. 13፥29) ከሚለው ከጌታችን ኢየሱስ ንግግር እናስተውላለን።

Wednesday, 11 September 2019

መጨመሩን ሳይኾን

Please read in PDF

አዲስ ዐመት መጣ ዘመን ተጨመረ
ፊተኛው አረጀ አዲስ ተሞሸረ                                                               
ይህ ለእኔ አይደለም ላመንኩት በልጁ  ... 

Monday, 2 September 2019

ሐዋ. 2 ላይ የብሔርተኞቹ ሸቃጭነት!



በቃሉ ውስጥ ባዕድ ዐሳብ ቀላቅሎ ማቅረብና መሸቀጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የማይታዘዙ ሰዎች ኹነኛ መገለጫ ነው (2ቆሮ. 2፥17፤ 4፥2)፤ ከሰሞኑ የተነሡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ ዝቅ ብለውና ወርደው “በክልል ደረጃ፣ በአንድ ብሔር ስም” ክርስትናን “እንመስርት” ባዮቹ አካላት፣ እጅግ ድፍረት በተሞላበት ንግግር መጽሐፍ ቅዱስን ጠቅሰው፣ ይህን እኩይና እቡይ ድርጊታቸውን እንደሚደግፋቸው ሲጠቅሱ ሰምተናቸዋል፤ በቋንቋና በብሔር ክርስትናን ለመደራጀት እንደሚፈቅድላቸው ከጠቀሱት ጥቅስ አንዱ ደግሞ  የሐዋርያት ሥራ ኹለትን ነው።