"ጸበል" ለአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አ.ተ.ት) ወረሽኝ መዛመት፥ ምክንያት ከሆኑት መካከል ዋነኛው መኾኑን የተለያዩ የጤናና የመንግስት ተቋማት በማሳሰብ ላይ ናቸው፡፡ የአ.ተ.ት ወረሽኝ ከሰውነታችን ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ፈሳሻችን በተቅማጥ እና በትውከት መልኩ በመውጣት የሰው ልጅን ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡ (የጤና ባለሙያዋ ውዷ ባለቤቴም፥ እንደነገረችኝም ከኾነ አ.ተ.ት ይባል እንጂ የኮሌራ ወረሽኝ መኾኑን ነው)፡፡ ይሄም እንግዲህ፤ ሌላኛው የእኛው ቤት ዕዳ ነው፡፡ ለማስረጃነት ይረዳን ዘንድ፥ ከዚህ በታች የሰበሰብኳቸውን የተለያዩ ተቋማት ሪፖርት እንመልከት፥
1- የምዕራብ ጐጃም ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ የኾኑትት፤ ወንድሜነህ ልየው በ2ዐዐ9 በጀት ዓመት የግምገማ ውይይት ላይ እንደተናገሩት፥ "በዞኑ በተለይም በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ #በፀበል ቦታዎች ምክንያት የአተት በሽታ ተከስቷል፡፡ ሰዎች ከፀበል ቦታዎች ወደ አካባቢያቸው በሽታውን ይዘው በመመለሳቸው ምክንያት በሌሎች ወረደዎችም ተከስቶ በአጠቃላይ በዞኑ #884 ሰዎች በሽታው ተገኝቶባቸው ህክምና ተደርጐላቸዋል #የሞቱም አሉ" ብለዋል፡፡
2- የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኮስትር በሰጡት አስተያየትም፥ "ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ #ከአንዳሳና #አቡነሐራ #ፀበል ቦታዎች ጋር ተያይዞ ለአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አ.ተ.ት) ተጋላጭ" መኾኑን ተናግረዋል፡፡ በ2ዐዐ9 በጀት ዓመት እስከ ሰኔ 3ዐ ድረስ 638 ሰዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና መሰጠቱን የተናገሩት ኃላፊው አሁንም #አንዳሳ #ፀበል ቦታ ላይ በሽታው መኖሩንና በተቋቋመው ጊዜያዊ ህክምና መስጫ ቦታ #4 ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
3- የይልማና ዴንሳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሳይት ኃይሉ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት "በሸታው በወረዳቸው ባይከሰትም በአንዳሳና #በአቡነ #ሐራ #ፀበል ቆይተው በሚመጡ ሰዎች ሊከሰት ይችላል በሚል በጤና ጣቢያዎችና በወረዳው በሚገኙ አምስት #የፀበል ቦታዎች ስለበሽታው መንስኤ፣ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዘዴዎች" ግንዛቤ ተሰጥቷል፡፡
4- የኪንፋዝ በገላ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን እና ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት
የአ.ተ.ትን በሽታ ምክንያት አድርጎ ባወጣው ዘገባ፥ ይህን አስቀምጧል፥ "ለበሽታው መተላለፍ አመች ሁኔታ ሊፈጠሩ የሚችሉ ቦታዎች፥ "ምግብ ቤቶች፣ ሀዘን ቤቶች፣ #ፀበል ቦታዎች፣ ማረማያ ቤቶች" መኾናቸውን ጠቁሟል፡፡
የአ.ተ.ትን በሽታ ምክንያት አድርጎ ባወጣው ዘገባ፥ ይህን አስቀምጧል፥ "ለበሽታው መተላለፍ አመች ሁኔታ ሊፈጠሩ የሚችሉ ቦታዎች፥ "ምግብ ቤቶች፣ ሀዘን ቤቶች፣ #ፀበል ቦታዎች፣ ማረማያ ቤቶች" መኾናቸውን ጠቁሟል፡፡
5- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) "በትግራይ ክልል በተከሰተ የአ.ተ.ት በሽታ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 326 ሰዎች በጠና ታመዋል። በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ባጋጠመው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አ.ተ.ት) በሽታ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ ... የዞኑ አስተዳዳር የማህበራዊ ልማት አማካሪ አቶ ግደይ በርኸ እነሸደተናገሩት "... በ2010 ዓመተምህርት በአህፈሮም ወረዳሴሮ ቀበሌ እንደ አባ እንድርስ በተባለው #የፀበል ቦታ የተፈጠረው ጉዳት #የከፋ ሲሆን እስከ አሁንም #መቆጣጠር#አለመቻሉንም ጠቅሰዋል"፡፡
6- ANRS Communication Affairs Office
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ፥ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ ተክለኃይማኖት ገብረ-ህይወት በቢሯቸው ስለ አ.ተ.ት በሽታ በሰጡት መግለጫ፥
"የበሽታው መንስኤዎች በርከት ያለ ህዝብ በጋራ አገልግሎት በሚያገኝበትና በሚሰጥበት እንደ እርሻ ቦታ፣ #ጸበልና ፍልውሃ ቦታዎች ሲሆን፣ የሚተላለፈውም ንጽህናው ባልተጠበቀ እንደ ምግብና ውሃ ባሉ ወደ አፋችን በሚገቡ ነገሮች ነው ብለዋል፡፡ አቶ ተክለኃይማኖት አያይዘውም በክልላችን እስካሁን አምስት ሽህ 61 ሰዎች በበሽታው የተጠቁ ሲሆን 45 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 28 የሚሆኑት ወደ ጤና ተቋማት ሳይደርሱ ህይወታቸው ያለፉ ሲሆን ቀሪዎቹ 17 ሰዎች በጤና ተቋማት ውስጥ ያረፉ ናቸው ብለዋል፡፡
በሽታው በወቅቱ ወደ ጤና ተቋም ለደረሰ ሰው በቂ ህክምና ያለው ነው ያሉት አቶ ተክለኃይማኖት፣ በጤና ተቋማት ከገቡ በኋላ #ህይወታቸው #ያለፉ #ሰዎች #አብዛኛዎቹ #በጸበል #ቦታ #የታመሙና ቀደም ሲልም አብሯቸው የቆየ ሌላ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ናቸው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ ተክለኃይማኖት ገለጻ ጤና ቢሮው በሽታውን ለመቆጣጠር መከላከል ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡ ... #በጸበል ቦታዎች ስላለው ችግርም #በየሀገረ-ስብከቱ #ሊቀጳጳሳት ጋር በመመካከር #በየ #ጸበልቦታዎቹ በቂ መሠረ ተልማት እስኪሟላ ላልተወሰነ ጊዜ #ጸበልተኛ እንዳይገባ እስከማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
ማጠቃለያ፥
ጸበል (Holy Water) መጽሐፍ ቅዱሳዊ የፈውስ አገልግሎት እንዳልሆነ የታወቀ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ግን ዛሬም ድረስ ይሄን አገልግሎት ቀጥላበታለች፡፡ ከሚማቅቅበት በሽታና ደዌ እፈወሳለሁ ብሎ በተስፋ የመጣን ሕመምተኛ፥ እንደገና ለኮሌራ በሽታ አሳልፎ መስጠት የግፍ ግፍ ነው፡፡ የእግዚአብሔርንም ሥም ለአሕዛብ መሳለቂያ ይኾን ዘንድ እንደመፍቀድ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጅ፥ ይህን ነገር ባወቅሁ ጊዜ በጣም አፍሪያለሁ፡፡ በመሰረቱ፥ የጸበል አገልግሎት "በመንፈሳዊ ዓለም መመዛኛም ኾነ በአመክንዮዊ ምልከታ" ቅቡልነት የሌለው ነው፡፡ ሲጀመርም ቅዱሳት መጻሕፍትም ኾኑ ቀዳማውያን ሐዋርያትና አበው፥ ፈውስ "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም" ብቻ እንደኾነ ከማስተማራቸው በቀር ስለ ቅዱስ ውሃ ያስተማራን አንዳችም ነገር የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ከጥንት እንዲህ ዓይነት ልማድ የለትም፡፡ መዳን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ ነውና!

አሜን፥ ወስብሃት ለእግዚአብሔር!
No comments:
Post a Comment