Please read in PDF
ቤተ ክርስቲያን እንኳን የተፈጸመን ያልተፈጸመን ኀጢአት ማየት የምትችልበትን ነቢያዊ ችሎታ በመንፈስ ቅዱስ ተችሯታል። ኀጢአትን ለመቃወምና ለመጠየፍ፤ አለማዊነትንም ለመካድ ጭምር በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠ የእግዚአብሔር ጸጋ ለቤተ ክርስቲያን ተገልጧል፤ (ቲቶ 2፥11-13)። ቤተ ክርስቲያን ይህን የተገለጠ ጸጋ በእውነት በመቀበልና በማመንም ጭምር፣ የሰማይ መንግሥት እንደ ራሴነቷን ማስቀጠል ይኖርባታል። ቤተ ክርስቲያን ይህን ዘላለማዊ አደራ ይዛ ለመሄድ ግን የሞተላትንና አንድ ቤዛዋን ክርስቶስ ኢየሱስን ትኵር ብላ መመልከት የዘወትር ተግባርዋ ሊኾን ይገባል።

ክርስቶስ ኢየሱስ
ጌታችንን እንደ ተሰቀለ ኾኖ ትኵር ብሎ አለማየት ለድንዛዜና ለክፋት፤ ለእውነት ለማያሳዝዝ አዚም ሳያጋልጥ አይቀርም፤ (ገላ.
3፥1)፤ አዚም የአእምሮ ችግር አይደለም፤ ራስንም የመሳት ጉዳይ አይደለም፤ ፍጹም አለማወቅና አለመረዳትም አይደለም፤ ነገር ግን
መረዳት እየቻሉ አለመረዳት፣ ማስተዋል እየቻሉ ተላላ በመኾን አለማስተዋል፣ ማየት እየቻሉ መታወር፣ መጠንቀቅ እየቻሉ ፍጹም ቸለተኛ
የመኾን ጉዳይ ነው። የገላትያ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊቷ ያለውን እውነት በዝንጉነትና በቸለተኝነት ባለማስተዋል በአዚም ተያዘች።
እናም የተሰቀለውን ክርስቶስን ባለማየት ስንፍና ተያዘች።