Tuesday, 24 July 2018

“የኹለቱ ሲኖዶሶች” ነገረ ዕርቅ


     አንድ ሰው ከወንድሙ ጋር ተጣልቶ ሳይታረቅ ለጸሎት ወደ እግዚአብረር ፈፎሐሔሔር ቢቀርብ፣ በራሱ የቀረቀረውን በር መልሶ የማንኳኳት ሥራን ነው የሚሠራው፤ ይህ ደግሞ ከንቱ ልፋትና ድካም ነው። በጠብና በቅያሜ የሚኖር ሰውም ኾነ ቤተክርስቲያን ጸሎት የሚሰማውን የሰማይ ደጅና በርን የዘጋው ራሱ በራሱ ላይ ነው። ይቅር ለመባል፣ ይቅር ማለት የሚቀድም ከኾነ፣ ይቅር አልልም በማለታችን ይቅርታችንን የገፋነው እኛው እንጂ ይቅር ባዩ ጌታ አይደለም። በጠብና በበቀል፣ በጥላቻም መኖር ጸሎትንና በእግዚአብሔር ፊት የምናደርገውን ማናቸውንም “መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ያረክሳል”። ጌታችን ኢየሱስ ለዚህ ነው፦ “ስለዚህ መባህን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር በምታቀርብበት ጊዜ ወንድምህ የተቀየመብህ ነገር መኖሩ ትዝ ቢልህ፣ መባህን በዚያው በመሠዊያው ፊት ተወው፤ በመጀመርያ ሄደህ ከወንድምህ ጋር ተስማማ፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን ለእግዚአብሔር አቅርብ” (ማቴ. 5፥23-24) (ዐዲሱ መደበኛ ትርጉም) በማለት፣ ወንድምን አለመቆጣት፣ አለመሳደብ፣ አለመራገም፣ አለመናቅ፣ አለመግደል ብቻ ሳይኾን፣ ከወንድማችን ጋር የማንስማማበትና የማንግባባበትም ነገር ሊኖረን እንደማይገባ ጭምር የነገረን። መሥዋዕትና ማናቸውም መንፈሳዊ ነገር ከማከናወናችን በፊት፣ በመካከላችን ያለውን አለመስማማት፣ ክፉ መንፈስ፣ ቅራኔ፣ ቅያሜ ማስወገድ ይገባናል፤ በምትኩ መስማማት፣ ይቅርታ ፍቅር ምሕረት ማድረግ ይገባናል።

Wednesday, 18 July 2018

በሕማሙና በትንሣኤው ዙርያ የነበሩ ምስክሮች (ክፍል ኹለት)

2   ሴፍጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ወቅት እጅግ አስደናቂና አስገራሚ ክስተቶች ተከስተዋል፤ አንክድህም አብረንህ እንሞታለን ያሉቱ መከራና ፍርሃት ፈቷቸዋል፤ ፈጽመው ወደ ኋላ አፈግፍገዋል፤ ምንም እንኳ መከራ እንደ ሚመጣ ጌታችን አስቀድሞ የተናገረ ቢኾንም፣ በሥጋ ጉልበት ሊቋቋሙ በማሰባቸው ተሸንፈዋል፤ ጴጥሮስ በፈሪ ሰይፉ ጆሮ ሲቆርጥ ተስተውሏል።

Wednesday, 11 July 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (የመጨረሻ ክፍል)

ሰው ታርዶ ብርሃን ከሰማይ ይወርዳልን?

  ተአምረ ማርያም እስጢፋኖሳውያን በንጉሡ ዘርዓ ያዕቆብ በመታረዳቸው ምክንያት ብርሃን መውረዱን ሲናገር እንዲህ ይላል፦
  “... እኒህን ከሐዲያን ከወገሯቸው ወዲህ ሠላሣ ስምንት ቀን በሆነ ጊዜ  ... ስለእናቱ ስለእመቤታችን ስለከበረ መስቀሉም የክርስቶስ መስቀል በሚከበርበት በመጋቢት ዐሥር ቀን ሰኞ ሌሊት እግዚአብሔር ድንቅ ተአምር አደረገ። በንጉሡ ድንኳን ላይ ፍጹም ብርሃን ወጥቶ እንደ ጎርፍ ፈሰሰ። ... የዚያ ብርሃን መልኩም እንደ እሳት ላንቃ ይመስላል። ነገር ግን አያቃጥልም ነበር። ወደ ሰውም በቀረበ ጊዜ ፊት ያበራል የብርሃኑም መታየት ልቡናን ደስ ያሰኛል ...” (ተአምረ ማርያም)[1]
  “… ከዚህ በፊት ከቤተ ክርስቲያን የተቀበሩትን ቅዱሳንም (ከመቃብር) አውጥተው በድንጋይ እንዲወግራቸው አዘዘ።  ወታደሮቹ እንዳዘዛቸው አደረጉ። በዚህ ምክንያት በመንግሥቱ ብሔሮች ሁሉ ትልቅ ፍርሃት ሆነ። ንጉሡ ለነዚህ ጥቂት መንጋ በሆኑ በቅዱሳን ዘንድ በቀር ክህደቱን እንደ ከሐዲው እንደ ዲዮቅልጥያኖስ አልገለጠም። “እግዚአብሔር አማሌቅን ዘር ማንዘራቸውን በድብቅ እጅ ይመታቸዋል” ተብሎ እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር ሲመታ አይገልጽም። እግዚአብሔር እንዴት እንደ መታ (እነሆ)፤ ቅዱሳኑን ባሠቃያቸው ጊዜ እንደ ሚበተን የወናፍ ምድጃ እሳት ዓይነት እሳት አመጣ፤ በድንኳኑ ላይም ታየ፤ እሱና ሠራዊቱ ግን ተደስተው፥ “ብርሃን በእኛ ላይ ወረደ” አሉ። ከሊቃውንቱ አንዳንዶቹ፥ “ብርሃን አይደለም፤ ይህ እንዲያውም የእግዚአብሔር የቁጣው ምልክት ይመስላል። ይኽ ሰው የእግዚአብሔርን ባሮች ስላሠቃያቸው በላያችን ላይ የሚመጣብንን መቅሠፍት እንዴትና ምን (እንደሚሆን ምን) እናውቃለን?” አሉ።” [2]


Thursday, 5 July 2018

ፊታችንን መልስ

Please read in PDF

ግፍ ደንደስ አወጣ፣ ዓመጽ ሥር ሰደደ፤
ቀንበር እንደ ጸና፣ መቃናት ሳይመጣ፣ ቀኑ ተዋገደ፤
ስል ኃጢአት ወረረን፣ ንቅዘታችን ታየ፤