ሰው መንፈስ ነውን?
ሰው ሥጋና ነፍስ ወይም ሥጋና መንፈስ
ነው፤ የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት የብልጥግና ወንጌል[1] መምህራን፣
“ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ ያድራል፡፡”[2] በሚለው
ፍጹም ክህደት ደምድመውታል፡፡ “ሰው መንፈስ ነው” የሚለው ትምህርታቸውን የሚያስተምሩበት ዓላማቸው ኋላ ላይ አግተልትለው ከሚያመጡት
“ፈጣጣ ክህደት” አንጻር እንጂ ወዲያው አይገባንም፡፡ በአጭሩ “ሰው መንፈስ ነው” የሚሉበት ዋና ዓላማቸው ሥጋ ለባሹን ሰው፣
“እግዚአብሔር ለማድረግ” ከሚባዝን ከንቱ ምናባዊ ቅዠት የተነሣ ነው፡፡ ይህንን በድፍረት ኢትዮጲያዊው የቃል እምነት መምህሩ ኃይሉ
ዮሐንስ እንዲህ ይላል፦
“ … አዎ ልክ እንደእግዚአብሔር ነን[ኝ] በሚለው እስማማለሁ፤ ምን ማለት ነው ይህ? መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ማስረጃዎች አሉኝ፤ በመጀመርያም የምሄደው ዘፍ.1፥26-28 ያለውን በመጥቀስ ነው፤ … ያ መልክና አምሳል ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን
እንድንመስል ያደርገናል የሚል አመለካከት አለኝ፡፡ ግን “detail” መሄድ ቢያስፈልግ ጌታችን ኢየሱስ ስለራሱ የተናገራቸው
ነገሮች ትዝ ይሉኛል፤ በዮሐ.14፥8 ላይ … “እኔና አብ አንድ ነን” ያለበት ሃሳብ በእኔ አመለካከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ደግሞ ሰው ነው፤ በእኔ አመለካከት የሌላውን ሰው አመለካከት ልጋፋው አልችልም፡፡
ጌታ ኢየሱስ “እኔና አብ አንድ ነን” ካለ፣ ታላቅ ወንድማችን እንደዛ ካለ፣ እኛ ደግሞ ከአባታችን ጋር አንድነታችንን መናገር
እንችላለን፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው እኛም ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፡፡
|