Please read in PDF
የዚህ
ጽሁፍ ዋና ጭብጥ፥
1.
ዋናችን ጌታ ኢየሱስን በክርስትና ሕይወታችን ሁሉ ትኩር ብለን እንድንመለከት፤
2.
ዋናችን የሆነውን ጌታ ኢየሱስን ትተን በእርሱ “ሎሌዎች” ላይ ዓይናችንን የተከልን፥ በንስሐ እይታችንን እንድናጠራ፥
ከሰባኪ አድናቂነትና ተከታይነት ወደጸጋ አደላዳዩና ሠጪው ጌታ እንድናተኩር፤
3.
አገልጋዮች የሆንንም፥ “የሚከተሉንን” ምዕመናንና ምዕመናት የተሰጠንን “ስጦታ” ሳይሆን፥ ሰጪውንና ሁሉን አድራጊውን
እንዲመለከቱ፥ በሁላችንም ላይ የሚፈርደውንና የሁላችንን ሥራ ለሚያየው ጌታ ሕይወታቸውንና መንገዳቸውን አሳልፈው በማስጨከን እንዲሰጡ
በማሰብ የተዘጋጀ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምልከታ ነው፡፡
መንደርደርያ
ለብዙ ዘመናት ሰይጣን ሰዎች ዋናውን ጌታ እንዳይመለከቱና
“ሥጦታውን መመልከት ሠጪውን የመመልከት ያህል ነው” ወደሚል ከንቱ ማታለል ብዙዎችን ሲመራ አይተናል፡፡ በተለይም በዘመናችን ይህ
እውነታ ጎልቶና ደምቆ በመካከላችን በሚገባ ይስተዋላል፡፡ ሰዎች ሰባኪ[ሎሌውን] ብቻ መስማትን ልክ እግዚአብሔርን እንደመስማት ሲቆጥሩት፥
ቅዱሱን ወንጌል ከመመርመርና ጌታ ኢየሱስን በትክክል በመመልከት የክርስትና ሕይወት ሩጫቸውን ከመሮጥ ተዘናግተዋል፤ [ይህ በወንጌሉ
ፍጹም እውነትነት ላይ የቆሙትንና ለቃሉ ፍጹም በመታመን በማገልገል ያሉትን የጌታ ታማኝና እውነተኛ አገልጋዮችን አይመለከትም]፡፡