4. እውነት አንጻራዊ ናት፦ በአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ አስተምህሮ መሠረት ፍጹም እውነት የለም፤ ምክንያቱም ኹሉም እምነቶች ትክክልና ትክክለኛ ናቸው። ለምሳሌ፦ በክርስትና አስተምኅሮ አንድ ሰው ከጋብቻ ውጭ የሚያደርገው ማናቸውም ሥነ ምግባራዊ ርኩሰት አመንዝራነት ነው፤ ለአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ ግን ርኩሰት ሳይኾን ትክክል ነው። በጋብቻ ውስጥም፤ ከጋብቻ ውጭም የሚደረግ አመንዝራት እውነትና ውሸት ቢኾንም፣ ለነርሱ ግን ኹለቱም እውነት ነው።
Wednesday, 12 November 2025
Friday, 7 November 2025
ቤን ሂንና ኑፋቄው!
ሰውየው አስቀድሞ መጠሪያው “Faith World Church - የእምነት ዓለም ቤተክርስቲያን” በተባለ፣ በአኹን ወቅት
ደግሞ “World Healing Center Church - የዓለም የፈውስ ማዕከል ቤተክርስቲያን” የሚል ስያሜ የተሰጠው የግል “ቤተ ክርስቲያን” ያለውና “የብልጽግና
ወንጌልን” አቀንቃኝ “ንጥጥ ባለጠጋ” ነው። ከባለጠግነቱና ከቅምጥልነቱ የተነሣ፣ የሂን የወንድም ልጅ የኾነው
ፓስተር ኮስቲ ሂን በርሱ ቤት ተጠልሎ ሳለ ያየውን ሲናገር፣ ቅዱስ ጳውሎስና
እነርሱ የሚለያዩበትን አንድ እውነት፣ “እኛ የጳውሎስን አይነት ወንጌል አንሰብክም ነበር።” በማለት ገልጦታል።[1]
በምስክርነቱ ላይ ኮስቲ ሂን፣ እሱ እና ቤተሰቡ የያዙትን ውድ መኪናዎች እና ውድ ቤቶችን እና በጉዞው ዙሪያ ስላለው የቅንጦት ኹኔታ
ገልጦአል።[2]
ኮስቲ ሂን የአጎቱን የብልጽግና ወንጌል እና አስተምህሮ በመተቸት ብዙዎቹ ትንቢቶቹ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚቃረኑ ጽፎአል።[3]
Tuesday, 4 November 2025
ቃሉን የሚያነብብ ብፁዕ ነው!
ቅዱስ ቃሉን ማንበብ መንፈሳዊና ታላቅ አምልኮ ነው፤ አቡቀለምሲሱ ቅዱስ ዮሐንስ፣ “[ቅዱስ ቃሉን] የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።” (ራእ. 1፥3) ይለናል። ሐዳሲው ቅዱስ ዕዝራ፣ “... ወንዶችና ሴቶች የሚያስተውሉም ሲሰሙ፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር።” (ነህ. 8፥3) እንዲል፣ ቃሉን ከእኩለ ቀን በላይ ማንበብ እጅግ ታላቅ አምልኮ ነው።

.jpg)
