እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት እጅግ
አስነዋሪ ኀጢአትን ሠራች። የሠራችውም ኀጢአት መቅደሱን የሚያረክስ፣ የእግዚአብሔርን አምልኮ በባዕዳንና በብዙ የአማልክት
አምልኮ በመለወጥ በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ ነበር። ከዚህ ዓመጿም እንድትመለስ፣ እግዚአብሔር አያሌ ቅዱሳን ነቢያትን ቢልክም፣
እስራኤል በልብዋ ከመኩራራት በዘለለ ወደ እግዚአብሔር ልትመለስ አልወደደችም።

በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ እንደ ተናፈቀና እንደ ተቃተተለት የኖረ ታላቅ እውነት ቢኖር፣ ቅዱሱ መሲሕ ብቻ ነው። መሲሑን ሲፈልጉ ነቢያት አልታከቱም፤ አበው ፈጽሞ ዓይናቸው አልፈዘዘም፤ ያመኑ ሴቶች ሙታናቸውን በእምነት ለመቀበል አላመነቱም፤ ካህናት መሥዋዕትን ሲያቀርቡ ፈጽሞ አልተጠየፉም። እንደ ናፈቁት ኖረው፣ እንደ ናፈቁት ሞቱለት። ባያገኙት እንኳ፣ ምሳሌውን አገልግለው ለማለፍ ለቅንጣት እንደ ጉድለት አላሰቡም።