Please read in PDF
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኃጢአተኛው ዓለም ራሱን አሳልፎ
ሰጥቷል፤ ራሱን አሳልፎ የሰጠበትና ተሰቅሎ ዓለምን የሚያድንበት፣
ሁሉን ወደራሱ የሚያቀርብበት ኹኔታም፣ “እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ፤” (ዮሐ.12፥32)
ተብሎ ተገልጧል፡፡ እርሱ የወደቁትን በማንሣት ወደር የለሽና የማይዝል የአብ ክንዱ ነው። ቢዋረድም፣ ዝቅ ዝቅ ቢል፣ በሰው ምስል
ኾኖ እንደባርያ ቢያገለግልም ... እርሱ ለአብ አንድያ ልጁ፣ ከአምላክ የተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን የተገኘ እውነተኛ ብርሃን ነው።
“መጽሐፍ
እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን የተነሣ” ነው፤ (1ቆሮ.15፥3-4)፡፡
ታላቁ መጽሐፍ ይህን እውነት የሚያስረዳን አጉልቶና አድምቆ ነው፤ የቤተ ክርስቲያንም ታላቅና ውድ ምስክር ነው፤ ምስክርነቷም የቃል
ብቻ ሳይኾን በሚያስፈልግም ጊዜ በሕይወት ጭምር ዋጋ በመክፈል የምትመሰክረው የሕይወት ዘመን ምስክርነቷ ነው። ደግሞም ይህ የከበረ
እውነት በብዙ ምስክሮች ያጌጠና ያሸበረቀ ነው።