Read in PDF: Meskel Lay yalacheu
![]() |
ሥቁል ነኝ ለዓለም የማልረባ ባዶ
እርሷም በእኔ ፊት ፍሬ የሌላት ነዶ
የዓለምን አምሮት ቋቅ እንትፍ አድርጌ
በሞት ኢየሱስን ደግሞም በመቃብሬ
“አደግድጌ” ልቀኝ ተፈቶልኝ እስሩ
ገና በሰማያት በጽዮን ሀገሩ
እኔም እንደጌታ ሞትን አሸንፌ
እነሳለሁ ኃይሉን በግርማ ለብሼ፡፡
እኔን በመዋጋት ‘ምትደክመው ጠላቴ
ተስፋህን ቁረጠው በ‘ጁ ናት ህይወቴ
አንተ ወደቁልቁል እኔ ወደክብሩ
እገባለሁ በድንቅ አይሻርም ቃሉ፡፡
ጠላት ብዙ አቁስሎ መስቀል ላይ ያላችሁ
ታገሱ በጌታ ትንሣኤ አላችሁ
bereta arife geteme new
ReplyDelete