Tuesday, 30 July 2013
Monday, 29 July 2013
በልክ የሚገስጹንን አስነሳልን
Please read in PDF:- belik yemigesitsunin asnesalin
ሁል ጊዜ ጣፋጭ ነገሮችን መመገብ ጤናን የሚያናጋ መሆኑን ከመረጋገጡም በላይ፥ በተለይ ወጣትነትንየዘለሉ እንዳይጠቀሙም በሕክምና ባለሙያዎች ሲመከር እንደሰማሁት፥ ተመካሪዎቹም ተጠንቅቀው ሲርቁ ደጋግሜ አይቻለሁ፡፡ ይህ ማለት ሰውነታችን እየጨመረ በሄደ ቁጥር ኮስተር ወደሚያደርጉና ጣፋጭነታቸው ወዳልበዛ ነገሮች መቅረብና መውደድ መጀመር መቻል አለበት ማለት ነው፡፡ ይህንን ወደሕይወት ትርጉም ስናመጣው ጣፋጭ የሆነን ነገር ሁል ጊዜ መሻት፣ ቀለል ያሉ ነገሮችን ብቻ መርጦ መኖር፣ ሁል ጊዜ እሽሩሩ እየተባባሉና በምክር እያባበሉ መጓዝ፣ ልምምጥና ቁልምጫ፤ ወተት እንደሚጋት ሕጻን መጋት፣ እየተመሰጋገኑ፤ እየተንቆለጳጰሱ … ለመጓዝ ማሰብ ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ነው፡፡ በሕይወት ጉዞ ምክር አስፈላጊ የመሆኑን ያህል የሚመረውም ተግሳጽ የዚያኑ ያህል ያስፈልገናል፡፡

Wednesday, 24 July 2013
ልከኛው ጳውሎስ - 1
Please read in PDF:- Likegnaw Pawlos
እንደኰከብ ፈርጥ ለአሕዛብ በማለዳ የፈካ ፣ በነፍስ ተወራርዶ ኢየሱስን
ክርስቶስ ነው ብሎ የሰበከ ፣ በከሳሾች ፊት ለቅንጣት እንኳ አንገቱን ሳይደፋ የኢየሱስንበስም የገለጠ ፣ ቃሉና ሕይወቱ ነገሥታትንና
ፈላስፎችን ለክርስቶስ የሚማርክ ፣ በሥጋ ባለው ባዕለጠግነት ሳይመካ ፤ ላገለገለበትም የሚገባውን አንዳች ሳይጠይቅ እየተራበና እየተጠማ
ለክብሩ ወንጌል ያደላ ፣ በክርስቶስ ፊት እንጂ በሰው ፊት መከበርን የጠላ ፣ በአገልግሎቱና በጉዞው ሁሉ ላይከብድ የተጠነቀቀ ፣
ሲታይ ሞኝ በሕይወቱ ግን ለክርስቶስ ብልኅ የሆነ ፣ በድካምና በመገረፍ ያበዛ ፣ በድብደባ ብዙ ጊዜ በመታሰርም ያተረፈ ፣ ለሞት
እስኪቀርብ በድንጋይ ለወንጌሉና ኢየሱስ ለሚለው ስሙ የተወገረ …
Friday, 12 July 2013
የምድረ በዳው ዋርካ
Please read in PDF
የበረሃ ጉዞ ከዋዕዩና ከንዳዱ ጽኑዕነት የተነሳ እንዲህ እንደዋዛ የሚታሰብ ጉዞ አይደለም፡፡ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ከወጡ በኋላ ዳግመኛ ወደኋላ መመለስ እንዳይችሉ የኤርትራን ባሕር በደረቅ ተሻግረው የባሕሩ ደጅ ሲዘጋ ከፊት ለፊታቸው የገጠማቸው ታላቁ የሲን ምድረ በዳ ነው፡፡
የበረሃ ጉዞ ከዋዕዩና ከንዳዱ ጽኑዕነት የተነሳ እንዲህ እንደዋዛ የሚታሰብ ጉዞ አይደለም፡፡ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ከወጡ በኋላ ዳግመኛ ወደኋላ መመለስ እንዳይችሉ የኤርትራን ባሕር በደረቅ ተሻግረው የባሕሩ ደጅ ሲዘጋ ከፊት ለፊታቸው የገጠማቸው ታላቁ የሲን ምድረ በዳ ነው፡፡
Wednesday, 10 July 2013
Sunday, 7 July 2013
አንድ ሰው
please read in PDF
አገልግሎት የሚጀምረው ከአንድ ሰው ነው፡፡ ከአንደ ሰው
የማይጀምር ፣ አንድ ሰው የማያከብር አገልግሎት ደጋፊ እንጂ አማኝ አያፈራም፡፡ ይህን እውነት ያስተማረን ትልቅ ሰው መድኃኒአለም
ነው፡፡ ጌታ በአደባባይ ካገለገለው አገልግሎት ይልቅ ብዙ አንድ ሰዎችን ያገለገለው አገልግሎት ይበዛል፡፡ ሁል ጊዜ ከአንድ የሚጀመር
ማንኛውም ነገር ጤናማና የስኬት እውነተኛ መንገድ ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)