Please read in PDF
አስቀድሜ ትልቁን የሰማይ አምላክ አንተ ብዬ በምጠራበት ዓውድ፣ ከኹለት አንዳችሁን ሳነሣ “አንተ” ብዬ ብጣራ “ባህል
ጣሽ፣ አክብሮት ገሳሽ” [በምን አቅሜ - አንድዬ እያለ] አንባቢዎቼም እናንተም እንደማትሉኝ በመተማመን ነው። ስለዚህም አንተ ብዬ
በምናገርበት ቦታ ላይ የንቀት ወይም ሌላ ምንም ነገር በውስጤ እንደ ሌለ አስቀድሜ መናገር እፈልጋለሁ።
መቼም፣ “ይህ ጽሑፍ በየት በኩል ለእነርሱ ይደርሳል?” እንዳልባል፣ ኹለቱም መገናኛ ብዙሃንንና ማኅበራዊ መገናኛዎችንም
በቅርብ ተከታታይ መኾናቸውን በተለያየ መንገድ አጣርቻለሁ፤ ከዚህ ባሻገር ኹለቱም በጽሕፈት ቤታቸው ብዙዎች የሚከታተሉት ማኅበራዊ
መገናኛዎች አሏቸው፤ እናም ሊደርሳቸው እንደሚችል በማሰብ በእርግጠኝነት መጻፍን መርጫለኹ። ልጽፍ ያነሳሳኝ ዓቢይ ነገር ልቤ ላይ
ደጋግሞ ስለመጣና ውጤቱንም በተደጋጋሚ በማየቴ፣ በሌሎች አገራትም ላይ ተመሳሳይ የታሪክ ስህተት መፈጸሙን በማስተዋሌም ጭምር ነው።
የዚህ ጽሁፍ ዋነኛ ዓላማ፣ ኀጢአትን ለመኰነን ብቻ እንጂ የማንንም ባህልና ወግ የሚነካ ተግባርን የሚያካትት አይደለም።






