በአዲስ ኪዳን ወይም በመላው ክርስትና ውስጥ፣ እግዚአብሔር በብዙ ጸጋውን ያበዛለትና በወንጌል አገልግሎት ብዙ ሺህ ማይሎችን ተጉዞ በማገልገል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ምሕረት የገነነለትና የተትረፈረፈለት ብርቱ አገልጋይ “ያለ አይመስልም”። የጽድቅ ቀናተኛ፣ የማያመቻምች፣ ባለ ብዙ ሐብተ ጸጋ፣ አያሌ አብያተ ክርስቲያናትን የመሠረተ፣ የአዲስ ኪዳንን ግማሽ ያህል መጻሕፍት የጻፈ፣ አስደናቂና ተወዳጅ የእግዚአብሔር ምስጢራትን በትምህርትና በስብከት የመገበ፣ ክርስቶስን አክብሮና አስከብሮ በሕይወቱ ጭምር መስክሮ በጽድቅ መሥዋዕት የኾነ ሐዋርያ ነው።
Saturday, 27 December 2025
Friday, 5 December 2025
የታይታ አገልግሎት የለንም!
ሽልማታችን ሰማይ፤ ዋጋችን ኹሉን በዓይኑ በሚቆጣጠር ጌታ ዘንድ እንደ ኾነ
አውቀንና አምነን፣ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው የተከተሉ የጽድቅ መናንያን፤ የቅዱስ ቃሉን ሰማዕታት፤ እንደ ጨው በምድር
ዳርቻዎች ኹሉ የተበተኑ ሐዋርያትን፤ እውነትና ፍትሕን እንደ ውኃ ከፈሰሰ ሕይወት ጋር የሰጡ ነቢያትን፤ ታርዶ እንደ ተወራረደ
መሥዋዕት ኹለንተናቸውን የሰጡ ሰባክያንን፤ የምድረ በዳውን ዋዕይ፣ የበረሃውን ሚራዥ ታግሠው ሳይናወጡ የተጉና የኖሩትን እንደ
ደመና ዙሪያችን ዘወትር የከበቡንን “ሕያዋን ጻድቃንን” አሠረ ፍኖታቸውን የምንከተል የተሰቀለው መሲሕ ማኅበረ ሰብ ነን። እናም
መሲሑ እንዲልቅ፤ መንግሥቱ እንዲሰፋ፤ ለቤተክርስቲያን ጥቅምና መታነጽ እንጂ ለታይታ የምናደርገው አንዳችም የለንም።
Wednesday, 3 December 2025
ከዶክተር ገመቺስ ምክር ተጠበቁ!
ከሰሞኑ ዶክተር ገመቺስ እንዲህ ብሎአል፤
“ዳዊት ድሪምስ የወደቀውን የሰውን ሥነ ልቦና
ለማነሳሳት የሚተጋ ሰው እንጂ የአዲሱ ዘመን ዕሳቤ አራማጅ አይደለም።”
ስለ
አዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ አማኞችና ተከታዮች በሰፊውና በተከታታይ መጻፋችን ይታወሳል። ዶ/ር ገመቺስ ፈጽሞ እንደ ተናገረው ሳይኾን፣
እነ ዳዊት ድሪምስ፣ አሸናፊ
ታዬ፣ ኤልያስ ገብሩ(ዶ/ር)፣ ዳግማዊት ክፍሌ፣ ነፃነት ዘነበ፣ ማንያዘዋል
እሸቱና ሌሎችም በአገራችን የትምህርቱና የልምምዱ ዋና አቀንቃኞች መኾናቸውን አንስተን ጽፈናል፤ ዛሬ ደግሞ ዶክተሩ፣
ስለ ዳዊት ድሪምስ የተናገረውን በጥቂቱ እንቃኝ።


