ከጥቂት ዓመታት ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ
ከተደረጉ “ፖለቲካዊ የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎች” አንዱ፣ ሰዎች በቋንቋቸው ወንጌል ሊማሩ ይገባል የሚል ነበር፤ በዚህ ዐሳብ
ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ “በወንጌል ልብ” በተደጋጋሚ ይጠይቁ ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዱ በመኾኔ፣ በጥያቄው ፍጹም እስማማለኹ።
ነገር ግን መልሱ የተሰጠውና በተግባር ላይ የዋለው ፍጹም መንፈሳዊ ባልኾነ መንገድ ባለ መኾኑ ሳዝን ዳሩ ግን በእግዚአብሔር
ሉዓላዊነት እጽናናለኹ!
Wednesday, 31 July 2024
ለእውነተኛ ተሐድሶ ኦርቶዶክስን አይጠቅማትም!
Sunday, 28 July 2024
የፓሪስ ኦሎምፒክ ሴሰ*ኝነት፣ ሰዶ*ማ*ዊነት፣ በጌታ እራት ሲሳ*ለቁ!
Friday, 19 July 2024
ስለ ኦርቶዶክስ በልቤ ያለ ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት!
ከልጅነቴ ያደግኹት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነው፤ የተጠመቅኹት፤ የቆረብኹት፤ በቅንአትና
በትጋት ያገለገልኹት … በዚያ ነው። በዚያ የነበረኝ አገልግሎት በዕውቀትም በቅናትም እንደ ነበር ብዙዎች ምስክሮቼ ናቸው።
የክብሩንና የትንሣኤውን ወንጌል በትክክል ስረዳና ስመሰክር ግን ብዙዎች ተቃወሙኝ፤ እናም አብረኸን ልትኾን አይገባም ሲሉኝና
ሲገፉኝ ወጣኹ።
Friday, 5 July 2024
ወርቅ ሲደብስ!
ጳጳሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን አላነበቡምን?
ጳጳሱ ለማርያም ያላቸው አስተምኅሮ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ
በተቃራኒ የቆመ ነው፤ እንዲህ ያለ ነገር በርግጥ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ “የታወቁ መምህራን” የሚናገሩት ነው፤ ከዚህ ቀደም
ዲያቆን ኃይሌ፣ “እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን መሥራት ትችላለች” ብሎ መናገሩንና ለዚህም ምላሽ መስጠታችን
ይታወሳል፡፡ ለምን ኾን ብለው ማርያምን በማግነንና በማስመለክ፣ እግዚአብሔርንና ስሙን መሳደብ እንደሚፈልጉ አላውቅም፤
እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር በልጁና በመንፈሱ የሠራውን ሥራ ባለማወቃቸውም እጅግ እደነቃለሁ!
Tuesday, 2 July 2024
ጌታ ኦርቶዶክስን በወንጌል ሊጎበኝ እያሰበ ቢኾንስ?
“የስብከተ ወንጌል”ና “የመንፈስ ቅዱስ ቀን”
በኹለቱ ተቋማት ዕይታ!
በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማርቆስ አማካኝነት፣ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ሰኔ 24ን “የስብከተ ወንጌል” ቀን ብላ ሰይማለች፤ ዓላማውንም ጳጳሱ እንዲህ ብለው
ያስረዳሉ፣ “የስብከተ ወንጌል ቀን ሲባል ስብከተ ወንጌል የሌለበት ቀን የለም። የወንጌልን ቀን ማክበር የተፈለገበት ዕውቅናን
ለመስጠት ነው፤ ይበልጥ በትውልዱ አእምሮ … ዛሬ የወንጌል ቀን ብሎ እንዲያዘክረው እንዲያከብረው … ሕፃናት ጭምር እንዲያውቁት
ነው ትልቁ ዓላማው።” መሪ ቃሉም፣ “በወንጌል ተልእኮ ትውልዱን መታደግ” የሚል እንደ ኾነ ተጠቅሶአል።