ካለፈው
ቀጠለ …
3.4. ከሰውም ኾነ ከሌላው ፍጥረት ጋር ያለንን
ግንኙነት የተሻለ ያደርገዋል፤
ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በኤደን ገነት በቅድስና ይመላለስ ሳለ፣ ግንኙነቱ ፍጹምና እንከን አልባ ነበር፤ (ዘፍ. 2፥8፡ 15፡ 25)። ነገር ግን ሰው በኀጢአት በወደቀ ጊዜ፣ ኀጢአት የሰውንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት አበላሸ። ከዚህም የተነሣ ሰው፣ ወደ ወደቀውና ወደ ተሰበረው ዓለም መጣ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ጸንቶ በሚኖረውና በማይለወጠው የቅድስናና የፍቅር ባሕርይው ጸንቶ አለ፤ (ዘጸ. 3፥14፤ ሚል. 3፥6፤ ኢሳ. 48፥12)።