ካለፈው
የቀጠለ …
2.4.
እውነትን በመኖር ለማደግ
እውነተኛ
ዕውቀት አእምሮን ጤናማ ያደርጋል። እውነተኛ ዕውቀትና ጤናማ ትምህርት የሌላቸው ሕይወታቸውና ልምዳቸውም ጤናማ ሊኾን አይችልም።
በክርስትና ትምህርት ስናውቅ እናምናለን፤ ስናምነው ደግሞ የምናውቀው ብዙ አለን። የእምነት ዕድገት የሕይወት፣ የአምልኮና
የመንፈሳዊ ዕድገት ለውጥ ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ፣ “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።” (ኤፌ. 1፥17) በማለት፣ እግዚአብሔርን በማወቅ እንዲያድጉ የጥበብና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣቸው ልመና ያቀርባል። ይህም ዕውቀት ከራሱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሌላ ከማንም ሊመጣ እንደማይችልም ጭምር ይናገራል።