Friday, 30 September 2022

Dubbi Ateetee warra Waaqefannaa Gabaabinaan!

 

“ Waaqtaanummaa – Waaqefannaa fi Kiristaanummaan maal waliif ta’u? mata duree jedhuun kitaaba dhiyootti maxxansiisu irraa kan fudhatame.

“… Ateeteen mallattoo ykn mallattoo aadaa qofaati yaada jedhu irraa ni darba. Hawaasa Oromoo keessatti dhugummaa hawaasichaatiin alatti mallattoo  waaqefachuus ni qaba.[1] Ateeteen mallattoo firii, hortee, kabaja haadhummaa ti. Ateetee dubartiin takka kabaja olaantummaa hafuuraa keessatti kenna fudhatamummaa hortee kan kennituu dha.  Humna nageenya waaqummaa dubarti,[2] ykn ayyaana dubartootaa fi[3] waggootti yeroo tokko kan kabajamtu yoo ta’u; sababni kabajaas gadaamessaa fi eebba firii gadaameessaa (goddess of fertility) waaq eebbistu jedhamee ti.[4] Dubartootnis ateeteedhan waa’e fayyaa fi hortee ni kadhatu.

የዋቄፈና ነገረ አቴቴ በአጭሩ!

 Please read in PDF

“ዋቄስትና - ዋቄፈናና ክርስትና ምንና ምን ናቸው?” ከሚለውና በቅርብ ከሚታተመው መጽሐፌ የተወሰደ!

“… አቴቴ ለምልክትነት ወይም የባህሉ ምልክት ብቻ ከመኾን ያልፋል፤ በኦሮሞ ማኅበረ ሰብ ዘንድ ከማኅበራዊ እውነታነቱ ባሻገር አምልኮአዊ ምልከታዎች አሉት።[1] አቴቴ የፍሬያማነት፣ የወላድነት፣ የእናትነት ክብር መገለጫ ናት። አቴቴ ሴት ልጅ በመንፈሳዊ ልዕልናና ክብር ውስጥ የመውለድን ሞገስ እንድታገኝ ጸጋ የምትሰጥ ናት። ሰላማዊ የሴት መለኮት ኃይል[2] ወይም የሴቶች መንፈስና[3] በዓመት አንድ ጊዜ የምትከበር ሲኾን፣ የመከበርዋም ምክንያት የማኅፀንና የፅንስ ባርኮትን (goddess of fertility) ባራኪ አማልክት ናት ተብሎ ነው።[4] ሴቶችም አቴቴን ስለ ጤናና ስለ መውለድ ይለማመናሉ።

Monday, 26 September 2022

ከዕጸ መስቀሉ ወደ ተሰቀለው ፊታችሁን አቅኑ!

Please read in PDF

በዚህ ሳምንት ከሚከበሩት በአላት አንዱ፣ ጌታችን ኢየሱስ ተሰቅሎበታል የተባለው፣ የዕጸ መስቀሉ በአል ነው። የሚከበርበት ምክንያት በአጭሩ ሲገለጽም፣ አይሁድ በጥላቻ ኢየሱስ የተሰቀለበትን መስቀል ከቆሻሻ መጣያ ቦታ ወስደውት ስለ ቀበሩት፤ ይህን የተቀበለውን መስቀል ከዓመታት በኋላ በአንድ ሰው መሪነት የቆስጠንጢኖስ እናት የኾነችው ከዓመታት ፍለጋ በኋላ፣ የተቀበረውን የእንጨት መስቀል እንዳወጣችና በአሉም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ መከበር እንደ ጀመረ ይተረካል።

Saturday, 24 September 2022

ጳጳሳት ባሉበት ጉባኤ የሴት አገልግሎት!

 በአንድ ወቅት አቡነ መርሐ ክርስቶስ ባሉበት ጉባኤ፣ አንዲት “ዘማሪ” ስለ ተክለ ሃይማኖት፣ “ባለ ስድስት ክንፉ” ብላ ስትዘምር፣ “ሰውየውን ወፍ አደረገችው” ብለው አሳፍረው አስቀምጠዋታል ይባላል። በርግጥ የአደባባይ ስህተት አደባባይ ላይ መታረም አለበት፤ አግባብም ነው! በዚህ ረገድ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ብዙ መልካም ምሳሌነት አላቸው።

Sunday, 18 September 2022

“ጳጳስ፣ የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል ሊኾን ይገባዋል!”

 Please read in PDF

አባቶቻችን ሐዋርያት በነበሩበት ዘመን ሳይፈቱት የቀረ ችግር፣ ረስተው የተዉት ነገር የለም። በመልእክታቸው ተጽፎ የምናገኘው እምነታቸውን ደግሞም የእምነታችውን ሥርዓት ነው። በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል። ከእነዚህ ውሳኔዎች አንዱ የጵጵስና ጉዳይ ነው። ጳጳስ መኾን ያለበት ምን ዓይነት ሰው ነው? እኛ የሐዋርያትን ውሳኔ ላለመቀበል ቃላትን በመሰንጠቅ ትርጉምን ማጣመም ውስጥ ካልገባን በስተቀር፣ እውነቱን በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኘዋለን።

ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊኾን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የኾነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?” (1ጢሞ. 3፥1-5)።



Saturday, 10 September 2022

በዘመናት የሸመገለው “የሰው ልጅ”!

 Please read in PDF

ከሰማይ በታች ያለው መላለም(መላው ዓለም) አንድ ቀን ወይም በጌታ ቀን፣ በታላቅ ድምጽ፣ በትኵሳትና በመቅለጥ ሊያልፍ ቀን ተቀጥሮለታል፤ መጽሐፍ፣ “በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።” እንዲል (2ጴጥ. 3፥10)። ሰማይና ምድር የሚያልፍበት ኹኔታ፣ የሰው ልጆች ኹሉ ሥራ በእግዚአብሔር ፊት የሚመረመርበት ወይም የሚታይበት መንገድ እጅግ አዳጋችና ኹኔታውን ለመግለጥ የሚያስቸግር እንደ ኾነ ይታመናል፤ ለጌታ ግን ኹሉ ይቻላል!

Thursday, 1 September 2022

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲፱)

 Please read in PDF

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን የእግዚአብሔር የራሱ ሥልጣን ነው ስንል፦

1.   ቃሉ የእግዚአብሔር ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ኾነ፣ ለቤተ ክርስቲያና መሠረትና ዓምድዋ ነው። ቃሎቹ የእግዚአብሔር ባሕርይ ገንዘብ አድርገዋልና፣ መጽሐፍ ቅዱስ አይለወጥም (ማቴ. 5፥17)፤ ልብን ኹሉ ይመረምራል (ዕብ. 4፥12)፣ ይቀድሳል (ዮሐ. 17፥17)፤ ይፈውሳል (መዝ. 107፥20)።