Please read in PDF
·
ዛሬ በኢየሱስ ስም መስበክ
ወይም ኢየሱስ ያድናል ማለት መናፍቅ አሰኝቶ ያስወግዛል!
·
ገድለ ተክለ ሃይማኖት
ደግሞ፣ የተክለ ሃይማኖትን ስም የጠራ ይድናል ይላል!
“መዳንም በሌላ
በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ከሰማይ በታች ሌላ የለም” (የሐ.ሥ 12፥4)
ይህን ቃል የተናገረው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነው። የተናገረውም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ
በቅዱስ ድፍረት ውስጥ ኾኖ ነው። ይህን ቃል ለመናገር ያበቃው ደግሞ፣ ሲወለድ ጀምሮ ሽባ የነበረውን ሰው ከፈወሰ በኋላ ለተነሣው
ሙግት ምላሽ ነው። ሰውዬው ለመሥራት ለመሮጥ፣ ለመቅደም፣ ለመታገል የማይችል ምስኪን ሰው ሆኖ፣ በወላጆቹ ላይ ወድቆ የሚኖር ሰው
ነበር። ጥዋትና ማታ በቤተ መቅደስ በር ላይ እያመጡ ይጥሉታል፣ ከሕዝብ ምጽዋት እየለመነ የዕለት እንጀራውን ያገኛል። ከዚህ ሕይወት
የሚያወጣው ሌላ እድል አያገኝም፣ ተስፋው በሙሉ በሰው ስጦታ ላይ የተመሠረተ ነው። አንድ ቀን በትክክል ቆሜ እራመዳለሁ ብሎ አስቦ
አያውቅም፣ የሚያስበው በቀን ምን ያህል ምጽዋት እንደሚያገኝና ኑሮውን እንደሚገፋ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ከ40 ዓመት በላይ አሳልፎአል።