“ያለ እውነት፥ የእውነት ቃል አገልግሎት!?” በሚል ርዕስ፣ ስለ “እውነት
ቃል አገልግሎት” ማኅበር ከታሪካዊ ዳራቸው ጀምሮ፣ ትምህርቶቻቸውን የሚያስቃኘው መጽሐፌ ታትሞ ከቀን 22/7/2013 ጀምሮ ለንባብ
ይበቃል! እንድታነቡት በፍቅር እየጋበዝኩ፣ አስተያየት እንድትሰጡበት፣ አንብባችሁ የማይረባና የማይጠቅም መስሎ ከታያችሁ “ጊዜያችንን
አቃጥለህብናል፤ የማይገባ ድካም ደክመሃል” ብላችሁ ልትወቅሱኝ፣ ፍሬና ቁም ነገር ካገኛችሁበት ደግሞ “ታንጸንበታል፤ በርታ!” ልትሉኝ
ትችላላችሁ።
Tuesday, 30 March 2021
በጌታ ቸርነት ኹለተኛ መጽሐፌ ታተመ!
Wednesday, 24 March 2021
Friday, 19 March 2021
አቢግያ - ኹለት ቤት ያዳነች ሴት
(የታማኝ ትዳር ውብ ምሳሌ)
መጽሐፍ ቅዱስ፣ እጅግ
አስደናቂ ስለ ኾኑ ሴቶች ካስቀመጠልን ሕያው ምስክር አንዷ አቢግያ ናት፤ እንዲህም የተመሰከረላት፣ “የሴቲቱም
አእምሮ ታላቅ፥ መልክዋም የተዋበ ነበረ፤” (1ሳሙ. 25፥3)። በተቃራኒው አቢግያ የስሙ ትርጓሜ “ጅል” ተብሎ ለሚጠራው
ለናባል ሚስቱ ነበረች፤ እርሱ በምግባሩ “ባለጌ፥ ግብሩም ክፉ ነበረ፤ ከካሌብም ወገን የኾነና
… ምናምንቴና ባለጠጋም ነበረ” (ቊ. 3፡ 25)። ሰውየው ባለጌ፣ ግብረ ክፉ፣ ካሌብ የስሙ ትርጉም “ውሻ” እንደ ኾነ፣ የውሻ
ጠባይ ያለው ሰው ነበረ፤ ከሚስቱ ፍጹም ተቃራኒ ሰው!
Thursday, 11 March 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፮)
ካለፈው የቀጠለ …
ባለፉት ጊዜያት የ“መድሎተ
ጽድቅ” መጽሐፍን በቀጥታ በመጽሐፍ ቅዱስ ከመመዘናችን በፊት፣ በመጽሐፉ ውስጥ ከቅዱሳት መጻሕፍት ዐሳብ ውጭ በኾነ መንገድ እንደ
ገና ተተርጕመው የቀረቡትን ቃላት መመልከት መጀመራችን ይታወሳል። ቃላቱን በተመለከተ ዛሬም ቀጣዩን ክፍል የምናቀርብ ይኾናል። መልካም
ንባብ።
· መዳን፦ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥና በአጭር ቃል ስለ መዳን ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “በእርሱ[በክርስቶስ] የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ. 3፥16)። በመጽሐፍ ቅዱስ መዳን የሚለው ዐሳብ፣ ልክ በዚህ ክፍል እንደ ተጠቀሰው የዘላለም ሕይወት፣ አዲስ ልደት (ቲቶ 3፥5)፣ አዲሱን ሰው መልበስ (ቈላ. 3፥10)፣ አለመጥፋት (ዮሐ. 3፥16፤ 2ጢሞ. 2፥11)፣ ልጅነት (ሮሜ 8፥13)፣ ዳግመኛ መወለድ (ዮሐ. 1፥12-13፤ 3፥3-8) በሚሉ ተካካይ ዐሳቦች ገልጦት እንመለከታለን።
Monday, 8 March 2021
ኢየሱስ እስኪመጣ - ዘጠኝ የአገልግሎት ዓመታቴ
በእግዚአብሔር ቸርነትና የተትረፈረፈ
ምሕረት፣ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በብሎግ ወይም በጡመራ መድረክ አገልግሎት አገልግያለሁ፤ በእነዚህ ዓመታት ከእግዚአብሔር የሰማኋቸውን፣
የተቀበልኳቸውን፣ ቅዱስ ቃሉን ሳነብብና ሳጠና መንፈስ ቅዱስ የገለጠልኝን፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የደረሱትን እጅግ አሳዛኝ
ሰቆቃዎችንና ከፍ ያሉ በደሎችን በአካል በስፍራው ተገኝቼ በመመልከት እግዚአብሔር ምን ይሰማው ይኾን? ብዬ ሙሾ አውርጄአለሁ።
Saturday, 6 March 2021
የጾመ ሕርቃልና የጾመ ዓቢይ ተቃርኖ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የዓቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ስያሜ “ዘወረደ” ወይም “ጾመ ሕርቃል” ይባላል። የመጀመሪያውን ሳምንት
“ዘወረደ” የሚለውን ስያሜ ያገኘው በባለዜማው ያሬድ ሲኾን፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማያት መውረድና የሰዎችን ልጆች ለማዳን
ያደረገውን የውርደት መንገድ በማሰብ፣ ከቅዱሳት መጻሕፍት ንባባት እየተነበበ አምልኮ የሚቀርብበትም ሳምንት ነው። ይኸው ሳምንት
ከዚህ ከጌታችን ባሕርይ ተቃራኒ በኾነ መንገድ “ጾመ ሕርቃል” ተብሎም ይጠራል።
የጾመ ሕርቃል አጭር ጥንተ ታሪክ[1]
Thursday, 4 March 2021
አዲሱ የሮዳስ ተረት!
መቼም የሐሰት መምህራንን
ጠባይ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “ክፉዎች
ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ” (2ጢሞ. 3፥13)። አንድ የስህተት አስተማሪ ፈጥኖ በቅዱስ ፍርሃትና የቅዱሳት መጻሕፍትን
ሥልጣን በማክበር በመታዘዝ ካልተመለሰ፣ እየባሰ፣ እየከፋ፣ ኀጢአቱን እየጨመረ፣ አሳሳችነቱን ይበልጥ እየገፋበት ይሄዳል።