ዘጠነኛ ክፍል እንግሊዘኛ ያስተምሩን አስተማሪያችን ይኅደጐ ይባላሉ፣ ማስተማር
ከመጀመራቸው በፊት ጥቊር ሰሌዳውን በሚገባ ደጋግመው ያጸዱት ነበር፤ አንድ ቀን አንዱ ተማሪ፣ “ቲቸር ለምን እንዲህ ውልውል አድርገው
በሚገባ ያጸዱታል?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም፣ “በሚገባ ባልታጠበ ትሪ ምግብ ትበላለህ?” ብለው ጥያቄውን በጥያቄ መለሱለት። እኔም
ዛሬ ሳስተምር፣ እንደ ቀደመው አስተማሪዬ በሚገባ መወልወልን ልማዴ አድርጌ አስቀርቼዋለሁ። ወደ ክርስትና ስመጣ የእኒህ አስተማሪ
“መርህ” በዋዛ የሚታለፍ አይደለም።
Saturday, 27 February 2021
ኢየሱስ ጣዖት አይደለም!
Monday, 22 February 2021
“በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።” (ዮና. 3፥8)
ጥንተ ታሪክ
ሊመጣ ካለው ቊጣና ፍርድ ታመልጥ ዘንድ፣ የንስሐ ዕድልን ሊሰጥ እግዚአብሔር
የአማቴ ልጅ ዮናስን ወደ ነነዌ ላከ። ነገር ግን ነቢዩ ዮናስ እግዚአብሔር ላዘዘው ምላሹ አለመታዘዝና ወደ ራሱ ፈቃድ አዘንብሎ
ከእግዚአብሔር ፈቃድ ሸሸ። እግዚአብሔር ግን ሉዓላዊና ኹሉን ሲያደርግ የሚሳነው የሌለ ነውና ዮናስን ወደ ነነዌ በራሱ ማጓጓዣ [በተአምራዊ
መንገድ] በዓሳ አንበሪ ሆድ ጭኖ ነነዌ አደረሰው።
Tuesday, 16 February 2021
ራቪ ከሞት ወዲያ፤ እኛ ከወዲህ ኾነን!
ራቪ ዘካርያስ፣ “የገዛ ሚኒስትሪያቸው” ያረጋገጠባቸው አስቀያሚው የዝሙት ገመና ብዙ ነገሮችን እንዳብሰለስል አድርጎኛል። በርግጥ ከደካማው ሥጋ ለባሽ ይልቅ፣ ቅዱስ ቃሉ የማይለወጥና ብርቱ አስተማሪያችን፣ የሚረባንንና የሚጠቅመንን የሚነግረን ኹነኛ መምህራችን ነበረ፤ እንዳለመታደል በትክክል ከመስማትና ከመታዘዝ ቸል አልን እንጂ። አዎን መጽሐፍ ቅዱስ “የብርቱዎችን” ድካም ያራቆተው፣ እንማርበትና እንታነጽበት ዘንድ እንጂ እንገበዝበት ዘንድ አይደለም።
Monday, 8 February 2021
Tuesday, 2 February 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፭)
ካለፈው የቀጠለ …
·
እግዚአብሔርን መምሰል፦
“በርካታ የምዕራብ
ክርስቲያኖች የኦርቶዶክስን የቲኦሲስ ወይም እግዚአብሔርን የመምሰል ሥነ ሐሳብ በትክክል ሊረዱት አልቻሉም። በተለይም ‘ሰው አምላክ
ይኾን ዘንድ አምላክ ሰው ኾነ’ የተሰኘውን የቅዱስ አትናቴዎስን ጥቅስ ሲያነቡ፣ ይህ የምሥራቃዊ ሂንዱይዝም ወይም የፓንቴይዝም ተጽዕኖ
ነው በማለት ያስባሉ።”[1]
“በቅድስና እግዚአብሔርን
በመምሰል የማደግ ሂደትም ከእግዚአብሔር ቅድስና የመሳተፍ ሱታፌያዊ ሂደት ነው። … ሐዋርያው፣ ‘ … ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥
በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።’ ያለው የባሕርዩ መገለጫና መታወቂያ የኾኑትን ነገሮች
- ኃይላተ እግዚአብሔር ቅድስና፣ ቸርነት፣ ደግነት፣ ጥበብ፣ እውነተኛነት፣ ገዢነት … የመሳሰሉትን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ የተሰጠን
በመኾኑ ነው። ይህም ከፓንቴይዝም እርሾ የጸዳ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርት ነው።”[2]