ካለፈው የቀጠለ …
·
ኀጢአት
በመጽሐፍ ቅዱስ ኀጢአት
ወይም ኀጢአትን ማድረግ አንድና ወጥ ትርጉም ያለው ብቻ አይደለም፤ በተለይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በአምስት በተለያዩ መንገዶች ተገልጦ
እንመለከተዋለን፤
1.
ሃማርቲያ[ሺያ]፦ (ዒላማን መሳት)፦ ይህ ቃል በአዲስ
ቃል ውስጥ ኀጢአት ወይም ኀጢአተኛ ተብሎ ከ250 ጊዜ በላይ ተጠቅሶአል፤ ትርጕሙም እግዚአብሔር ወዳቀደላቸው ዓላማና ግብ ኀጢአትን
በማድረግ፣ በገዛ ፈቃዳቸው ወይም ምርጫቸው ባለመድረሳቸው አዳምና ሔዋን[የሰው ልጆች] ዒላማ መሳታቸውን የሚያመለክት ነው፤ እግዚአብሔር
ወዳሰበላቸውና ወዳቀደላቸው ዐሳብና ክብር አልደረሱምና ከእግዚአብሔር ክብር ጎደሉ (ማቴ. 9፥2፤ ዮሐ. 1፥29፤ ሮሜ 3፥23)።