“ሁላችን በሃይማኖትና የእግዚአብሔርን ልጅ በማወቅ አንድ እስክንሆን
ድረስ በክርስቶስ ፍጻሜ ልክ የአካል መጠን እንዲደርስ ፍጹም ሰው እንሁን” (ኤፌ.4፥13)
መግቢያ
በዘመናችን ሰዎች ክርስቶስን በትክክል መኾን እንደሚቻላቸው አያሌ የስህተት ትምህርቶችን መስማት ከጀመርን ሰነባብተናል። አንዳንዴ ክርስቶስን የፍጥረቱ አካል በማድረግ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ እኛ ራሱ ክርስቶስን ልንኾን እንደምንችል በአደባባይ ታውጆአል፤ በተለያየ መንገድ ይህን ትምህርት ፊት ለፊት በመቃወም፣ የትምህርቱን ስሑትነትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ያልተቀዳ መኾኑን ተናግረናል፤ አስተምረናል። ዛሬም ክርስቶስ የፍጥረት አካል እንዳይደለ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተማሩንን፣ ፍጹም አምላክነቱና ፍጹም ሰውነቱን ደፍረን እንናገራለን።