Please read in PDF
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነገሥታት “በዶግማና በቀኖና” አንድ ያልነበሩትን
“አብያተ ክርስቲያናት”፣ አንድ ለማድረግ እጅግ መጣራቸውን እናስተውላለን።
“ከኬልቄዶን ጉባኤ በኋላ ለሚቀጥሉት ፩፻፶ ዓመታትያህል የነገሡ የቊስጥንጥንያ ነገሥታት ቤተ ክርስቲያንን ለማዋሐድ
ብዙ ጥረት አድርገዋል። ለምሳሌ ከ፬፻፸፬-፬፻፺፩ ዓ/ም የነገሠው
ዘይኑን(ዚኖን)፣ ከ፬፻፺፩-፭፻፲፰ዓ/ም የነገሠው እናስታሲዮስ በተዋሕዶ አንድ ባሕርይ የሚለውን የተዋሕዶ እምነት ተቀብለው
ቤተ ክርስቲያን በሰላም የምትመራበትን መንገድ ለመፈለግ ተነሳሰተው ነበር። ለዚህም በጎ ፈቃድ መሰናክሉ የኬልቄዶን ጉባኤ
ውሳኔና የልዮን ጦማር መኾኑን በመገንዘብ የቊስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ አባ አጋግዮስ(አካኪዮስ) እና ንጉሡ ዘይኑን ተስማምተው
ይህን ለመሰረዝና ቤተ ክርስቲያንንም ወደ ጥንታዊ የተዋሕዶ እምነቷ ለመመለስ ከአንጾኪያና ከእስክንድርያው ፓትርያርኮች ጋር
ውይይት ጀመሩ።”[1]