Please read in PDF
ሌሎችን በመናቃቸው ምክንያት የወደቁ ሰዎች
መጽሐፍ ቅዱስ አያሌዎች ሌላውን በመናቃቸው ምክንያት መውደቃቸውንና
መንኮታኮታቸውን በግልጥ ያስተምረናል፤ በዓለም ላይ ከተከናወኑ ጥቂት ያይደሉ ታሪኮች ውስጥ እንኳ፣ ገናና የተባሉትንና ያልተጠበቁትን ሲያዋርድ ተመልክተናል፤ አንብበናል። በተለይም “ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት
በጽድቅም ላለው ምክር” የተጻፈልን ሕያው የእግዚአብሔር እስትንፋስ የኾነው መጽሐፍ ቅዱስ፣ በንቀታቸው ምክንያት ስለወደቁት ሰዎች
እንዲህ ያስተምረናል፦
1.
የጎልያድ ንቀት
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጎልያድ የጦር ትጥቅ እንዲህ በማለት ይናገራል፤ “… የጌት ሰው ጎልያድ፥ ቁመቱም ስድስት
ክንድ ከስንዝር የሆነ፥ ዋነኛ ጀግና መጣ። በራሱም የናስ ቍር ደፍቶ ነበር፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር፤ የጥሩሩም ሚዛን አምስት ሺህ
ሰቅል ናስ ነበረ። በእግሮቹም ላይ የናስ ገምባሌ ነበረ፥ የናስም ጭሬ በትከሻው ላይ ነበረ። የጦሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅልያ
ነበረ፤ የጦሩም ሚዛን ስድስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ።” ጎልያድ እንዲህ ያለ አለባበስ በመልበሱና የውጊያ ትጥቅን በመታጠቁ፣ ከፍልስጥኤማውያን
ኹሉ አንደኛ አድርጎታል፤ በዚህ ሳይበቃ እስራኤልንና ንጉሡ ሳኦልንም ጭምር በማንቀጥቀጡ የሚደርስበት ፈጽሞ አልተገኘም።