ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጋር “ተቃራኒ” በነበረችባቸው ዘመናት፣ ማለትም
ነገሥታት ጸረ ክርስትና አቋም ይዘው ተነሥተው በነበሩባቸው ዘመናት፣ ቤተ ክርስቲያን ከሩቅ የሚታይ አብረቅራቂ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን
ተጐናጽፋ ነበር፤ ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት በላይ ከኔሮን ቄሣር እስከ ዲዮቅልጥያኖስ የዘለቀው ጽኑ የመከራ ዘመን ቤተ ክርስቲያን
እንደ ቦኸር በዐለት ላይ ተከላት እንጂ፣ ፈጽሞ ካመነችው እውነትና ከመንፈስ አንድነቷ አላነወጣትም፤ አልከፋፈላትም፡፡ መከራ ማጥሪያዋ
ብቻ ሳይኾን መጽናኛዋም ጭምር ነበር፡፡
Friday, 30 August 2019
Tuesday, 27 August 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፪)
Please read in PDF
2.
ለመስረቅ፦ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጐች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤” በማለት ሲናገር ሾላኮቹ ራሳቸውን በማመሳሰልና በመደበቅ የተካኑ መኾናቸውን
እየነገረንም ጭምር ነው፤ (ዮሐ. 10፥1)። ሌባ በባሕርይው ተደብቆ ወይም ሾልኮ እንጂ በግልጽ መግባትን አያውቅም። ይህንም የሚያደርገው
ተቀዳሚ ዐላማው የእርሱ ያልኾነውን ነገር፣ ለራሱ ጥቅምና ፍላጎት ለመስረቅና ለመውሰድ ነው።
Monday, 19 August 2019
Monday, 12 August 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፩)
Please read in PDF
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ
ቃል ሐራጥቃ[1] የኾኑ መናፍቃንን
ጠባያቸውን ሊገልጥ በሚችል መንገድ፣ ሾላኮች ወይም ወደ ቤቶች ሾልከው የሚገቡ በማለት ይጠራቸዋል፤ (ገላ. 2፥4፤ 2ጢሞ. 3፥6፤
ይሁ. 4)። ቅዱስ ጳውሎስ ወደ እግዚአብሔር አደባባይና ወደ አማኞች የሚገቡት እንደ ሰላይ ነው ይለናል፤ ጌታችን ኢየሱስ ደግሞ
ከአማኞች ጋር ልዩነት የሌላቸው እስኪመስሉ ድረስ “እንደ ተኩላ” (ማቴ. 7፥15) ነው ይለናል፤ ሰላይ መመሳሰልን ገንዘብ ያደርጋል፤
ተኩላም ኹለ ነገሩ ከበግ ጋር አንድ ዓይነት መኾንን ይመርጣል፤ ይህን ተፈጥሮአዊ ተመሳስሎታቸውን የሚጠቀሙት ግን የሚፈልጉትን ለማግኘት
ወይም በጭካኔያቸው ለመንጠቅና በግን በሕይወቱ ቦጫጭቀው ለመብላት ነው።
Saturday, 3 August 2019
የእምነት እንቅስቃሴ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን በዐውድ አያውቁትም!
Please read in PDF
ዐውድ አንድን
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመረዳት ወሳኝ ነው፤ ዐውድን አለመረዳት ጠቅላላ የመጽሐፉን ዐሳብ አለመረዳት ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ቀድሞ
የተናገረውን ያብራራልናል ይገልጥልናል እንጂ፣ አዲስ መገለጥም ኾነ ኢየሱስ ከተናገረው የተለየ የሚነግረን ምንም ነገር የለውም፤
ይህም በዐውድ ውስጥ ልንረዳው እንችላለን ማለት ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ፣ ዐውድ የቀደመው መልእክት ለዝንተ ዓለም ዘመን ዘለቅ
ኾኖ እንዲሻገር ኹነኛ አጥር ነው ማለት እንችላለን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)