Monday, 29 July 2019
Monday, 22 July 2019
ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (የመጨረሻ ክፍል)
Please read in PDF
“ወንጌላውያን” ነቢያትና ቤተ
መንግሥታዊ ማስታወቂያነታቸው
“ወንጌላውያን” ነቢያትና ጥቂት የማይባሉ ኦርቶዶክሳውያን አገልጋዮችም
ጭምር ቤተ መንግሥቱ በሕዝብ ዘንድ ዕውቅና ያገኝ ዘንድ ተግተው “እያገለገሉ” ይመስላል፤ ለዚህም ለምሳሌ፦ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ
መወቀስ አይገባቸውም እስከሚለው ጥግ የሄዱ አገልጋዮችን አይተናል፤ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን ከቤተ መንግሥት ባነሰ ማንነት
መኖሯን ራሳቸውን ጭምር በመስደብ ያቀረቡትን ሰምተናቸዋል። ለዚህም ለከት አልባ በኾነ መንገድ ግልጥ ፖለቲካዊ ቃላትን በመጠቀም
ሲወርዱ ተመልክተናቸዋል።
ለምሳሌ፦
- “አርበኝነት
በደሙ የተዋሐደው” ኢትዮጲያዊነት፣
- ሃያ
ሰባት ዓመታት መብታችን ተጥሶ … ፣
- የኢትዮጵያ
… የጠላቶቿ ድንጋይ አቀባዮች (የማርሲሉ ዮናታን አክሊሉ)፣
- ኢትዮጵያን
እግዚአብሔር በቃል ኪዳን ጠብቆአታል፣
Tuesday, 16 July 2019
ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (ክፍል - 2)
ራሱን ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እንደ አንዱ እንደ ኾነ
የሚቈጥረው፣ የ“Christ Army” ቴሌቪዥን ባለቤት ኢዩ ጩፋ፣ ስሙንና ክብሩን በሚናኝበት በገዛ ቲቪው ላይ “ለጠቅላይ
ሚኒስቴሩ ጻፍኩት” ባለውና በገዛ ቲቪው ላይ “ሲደሰኩር”፣ ለኢየሱስ የሚነገሩትን ምሳሌዎች በመላ ወስዶ ለጠቅላዩ ሲናገር
እንሰማዋለን፤ እንዲህ ይላል …
“ … ዕውቀትህ አስገራሚ ነው፣ ንግግርህም ይፈውሳል፤ እንደ ነቢይ
ትተነብያለህ፣ እንደ መምህር አስተማሪ፣ እንደ አባት መካሪ ነህና ዕድሜ ይጨምርልህ፤ አባት ነህና እንደ አብርሃም፣ ንጉሥ ነህና
እንደ ዳዊት፣ ነቢይ ነህና እንደ ሙሴ፣ ካህን ነህ እንደ ኢያሱ፣ ጠቢብ ነህ እንደ ሰሎሞን፣ ደፋር ነህ እንደ ጳውሎስ፣ ታጋሽ
ነህ እንደ ኢዮብ፣ ቆራጥ ነህ እንደ ሩት፣ ባለ ራእይ ነህ እንደ ዮሴፍ … እነዚህን ኹሉ ነህና …”
Saturday, 13 July 2019
ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (ክፍል - 1)
Please read in PDF
መግቢያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መካከለኛ ዘመን ታሪክ፣ የቤተ መንግሥትን አስነዋሪ ድርጊት ፊት ለፊት
ከተጋፈጡት መካከል በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን የተነሡት ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን፣ በአጼ ፋሲል ዘመን የተነሡት መነኮሳት፣ አባ
ፊልጶስና አኖሬዎስ ዘጸጋጅን ተጠቃሽ ናቸው፤ እኒህ አባቶች የነገሥታቱን አመንዝራነት፣ ፍትህ አልባነት፣ ድኃ ገፊነት፣
እጆቻቸውን በደም መታጠብ ፊት ለፊት የተጋፈጡና በሕይወታቸው ተወራርደው ዋጋ የከፈሉ ናቸው።
እስጢፋኖሳውያን
ዘርዐ ያዕቆብ እጁን ከቤተ ክህነትና ከቤተ ክርስቲያን እንዲያነሣ ደጋግመው ሞግተዋል፤ ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነት ጋብቻ
ሊፈጽሙ አይገባም በማለት ይናገሩ የነበሩት የመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን አማኞችና አባቶች ሳይሳሱ ፊት ለፊት ተጋፋጭና ተሟጋችም
ነበሩ፤ በቤተ ክርስቲያን በትር ዙፋናቸውን ያጸኑ አያሌ ነገሥታት ኢትዮጵያ የነበራትን ያህል፣ ነገሥታት በቤተ ክርስቲያን በትር
ዙፋናቸውን ማጽናታቸውን እንዲያቆሙ የተጋደሉ አያሌ አባቶችንም[መጨረሻቸው መሥዋዕትነት ቢኾንም] ነበሩ።
Friday, 12 July 2019
የዓምዳዊ ስምዖን ጸሎት
በመስቀል ላይ ሳለህ ራስህን
ዘንበል(ዘለስ) ያደረግህ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ አንተ ምስጋና አሳርግ ዘንድ ለሞተውና ላዳነኝ ምስጋና ይሁን እያለች
ነፍሴ በአምላካዊ በገና ታመሰግን ዘንድ የነፍሴን ራስ ከፍ ከፍ አድርግ፡፡
Monday, 8 July 2019
Subscribe to:
Posts (Atom)