2. የክርስቶስ ኢየሱስን
ሕይወት አይታለች፦ ጌታችን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ የእርሱን
ሕይወት ከእርሱ ጋር ውለው፤ አድረው እንዲያዩ ደግሞም አብረውት እንዲኖሩ ፈቅዶአል፤ (ዮሐ. 1፥40)። ከዚህም ባሻገር ጌታችን
ኢየሱስ ራሱ ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልይ ካደረ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን ሲመርጥ “ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥” ወዶ
እንደ ኾነ ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጥ ይመሰክራሉ፤ (ማር. 3፥13-14)።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀጥአንን
ተቀባይ መኾኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ደጋግመው ገልጠዋል፤ ግብዞችንና አስመሳዮችን፣ የሕይወት ቲያትረኞችን እጅግ ይጠየፍ የነበረው ጌታ
ኀጥአንን ግን በአደባባይ ሳይታዘባቸው ተቀብሏል፤ አብሮአቸው ተመግቦአል፤ ሳይጠየፋቸው በአንድነት ከእነርሱ ጋር አሳልፎአል። ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስ ከኀጢአተኞች ጋር ማሳለፉ ለብዙዎች አይሁድ የማይዋጥላቸው ተግባር ነበር፤ ምክንያቱም በግልጥ እንደ ሕጉ መለየትና
መወገዝ እንጂ ተቀባይነትን ማግኘት አለባቸው ብለው ያምኑ አልነበረምና።