“ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል፡፡ እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን
የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ፤” (ሮሜ.13፥12) ሌሊቱ ተብሎ የተጠቀሰው አሁን ያለው ክፉ ዘመን ነው፡፡ ጊዜውም ክርስቶስ ከሙታን
ከተነሣበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የሚያካትት ነው፡፡ ቀጥሎም ሐዋርያው የክርስቶስን መምጣት አጽንቶ ይናገራል፡፡ “ቀኑም ቀርቦአል”
ሲልም፣ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ “ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ” (ማቴ.24፥33)፣ “ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤”(1ቆሮ.7፥29)፣
“ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል”(1ጴጥ.4፥7)፣ “የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ” (2ጴጥ.3፥11)፣
“ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ … ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን” (1ዮሐ.2፥18) “ጌታ እስኪመጣ ድረስ
ታገሡ” (ያዕ.5፥7)፣ “ዘመኑ ቀርቦአል” (ራእ.1፥3) ተብለው ከተገለጡት ምንባባት ጋር በመስማማት የዘመኑን ከፊት ይልቅ ወደእኛ መቅረብና ክርስቶስ ሊመጣ በደጅ መኾኑን ይገልጥልናል፡፡
Thursday, 24 August 2017
Monday, 21 August 2017
Wednesday, 9 August 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አሥራ ስድስት)
Please read in PDF
3. በሠላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፦ የጫማ ዋና ሥራ ከማናቸውም እንቅፋት፣ እሾኽና እግርን ከሚጎዳ አደጋ መከላከልና መደገፍ ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት “ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ፡፡ ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው” (መዝ.119፥104-105) አለ፤ በጥንት አይሁድ አንድ ሰው የሩቅ መንገድ ሲጓዝ ድንገት ቢጨልምበት፣ በሚሄድበት መንገዱ እንዳይሰናከል በእግሮቹ ላይ መብራትን ያሥራል፡፡ ይህም የሚረግጥበትን በትክክል እንዲያስተውልና ወድቆም ከመሰበር እንዲድን ይረዳዋል፡፡
3. በሠላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፦ የጫማ ዋና ሥራ ከማናቸውም እንቅፋት፣ እሾኽና እግርን ከሚጎዳ አደጋ መከላከልና መደገፍ ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት “ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ፡፡ ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው” (መዝ.119፥104-105) አለ፤ በጥንት አይሁድ አንድ ሰው የሩቅ መንገድ ሲጓዝ ድንገት ቢጨልምበት፣ በሚሄድበት መንገዱ እንዳይሰናከል በእግሮቹ ላይ መብራትን ያሥራል፡፡ ይህም የሚረግጥበትን በትክክል እንዲያስተውልና ወድቆም ከመሰበር እንዲድን ይረዳዋል፡፡
ዳዊት በማናቸውም የሕይወት መንገዱ የእግዚአብሔር ሕግ መብራትና ብርሃኑ
ነው፤ ስለዚህም በማናቸውም መንገዱ ቢሆን ከሐሰት ጋር አያመቻምችም፣ አይስማማምም፡፡ የሐሰትን መንገድ ከነፍሱ እጅግ ይጠየፋል፡፡
መብራትና ብርሃኑ የሕጉ ቃል ነውና፣ ይህንንም ሕግ በማናቸውም መከራ ውስጥ እንኳ ቢያልፍ ከመጠበቅና በሕጉም ከመጽናናት ቸል አይልም፡፡
በዳዊት ንግግሮች ውስጥ ሁል ጊዜ ዝግጁነትና ፍጹም ታማኝነት አለ፡፡
Tuesday, 1 August 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አሥራ አምስት)
መጽሐፍ ቅዱስ ከማን ጋር መዋጋት እንዳለብን አበክሮ የተናገረውን ያህል
ከጠላታችን ጋር በመዋጋት በትክክል ስለምናሸንፍበት መሣርያም በግልጥ ይናገራል፡፡ ከዚህ በፊት እንዳየነው የምንዋጋው የእምነት ጦርነት
ነው፡፡ የውጊያውም የጊዜ ቆይታ እስከክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ “በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታን ሆነን
… የዲያብሎስን ሽንገላ መቃወም እንዲቻለን፣ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ መልበስ ያስፈልገናል”፡፡ ልብሱንና የጦር ዕቃውን መልበስና
መለማመድ ግድ ነው፤ ያልተለማመድንበትና አብረን “ያልሰለጠንበት” ልብስ ለውጊያ ሊሆነን ፈጽሞ አይችልም፡፡
የመሣርያው ዓይነት፣ የትጥቆቹ ይዘት በመከላከልና በማጥቃት ላይ የተመሰረቱ
ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለቱንም ሥራዎች[መከላከልና ማጥቃትን] ክርስቲያኖች መፈጸም እንዳለባቸው ያስተምራል፡፡ ለጌታ መታዘዝን
በባርያ ማንነት ውስጥ ሆነን የምናሳየውን ትጋት ያህል፣ ለጠላትና ለሚያስጨንቀው ገዢ አለመታዘዛችንና ግልጥ ተቃውሞዓችንን የምናሳይበት
መንፈሳዊ ጠባይ የጌታ መንፈሳዊ ወታደር በመሆን ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)