Thursday, 29 June 2017

“እኔ” ሥልጣን ይጣ!

አርነት አታውጣኝ ለሥጋ ፈቃዴ፣
ነጻነት አትስጠኝ እንድሆን መደዴ፤
የቃልህን ብርሃን በዝቶልኝ ካየሁህ፣

Friday, 23 June 2017

ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አሥራ ሁለት)

Please read in PDF

2.    ኃጢአት፦ በዕብራይስጥ [ኀቻታ] በግሪክ ደግሞ [ሐማርቲያ] ተብሎ የተነገረ ቃል ሲሆን፣  በተካካይ የአማርኛ ትርጉሙ ደግሞ “ዒላማን መሳት” ተብሎ ተተርጉሟል፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር እንድንደርስበት የሚፈልገው ዋና ዒላማና ግብ አለ፡፡ እዚያ እርሱ ካሰበበት መድረስ አለመቻል ዒላማን መሳትና ኃጢአት ነው፡፡
     የእግዚአብሔር ልጆች ዋና ዒላማችን እግዚአብሔር ራሱ ነው፤ ከእርሱ ፈቀቅ ማለት ቀስትን እንደሚስት ዒላማ ሳች (መሳ.20፥16)፣ እግሩን በማፍጠን ከእውነት መንገድ ይስታል፤ (ምሳ.19፥2)፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ከእግዚአብሔር ያነሰ ዒላማ፣ ከእርሱ ያነሰ ግብም ሊኖረን አይገባም፡፡ ከእግዚአብሔር ያነሰ ዒላማ ካለን ግን፣ ያ የያዝነው ዒላማ መልካምም ቢሆን እንኳ ኃጢአት ነው፡፡

Sunday, 18 June 2017

ዘፈን - የወደቀው መልአክ እንጉርጉሮ (ክፍል 5)

Please read in PDF
በቋንቋው ተናጋሪ ሊቃውንት[1] ዘንድ ዘፈን ኃጢአት ነው!
      አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም ሆነ ደስታ ተክለ ወልድም የዘፈንና የዘፋኝነትን ዓለማዊነት ወይም ኀጢአትነት በግልጥ አስቀምጠዋል፡፡ በመጽሐፎቻቸውም በግልጥ ቃል፦ “ዘፊን፤ ኖት፤ (ዘፈን ይዘፍን ይዝፍን፡፡ ዐረብ)፤ መዝፈን መወዛወዝ፤ ማሸብሸብ ማጋፈት መዝለል መፈንጨት፡፡ … ዘፋኒ፤ (ኒት፤ ንያን፤ ያት)፤ የሚዘፍን ዘፋኝ፤ ተወዛዋዥ፡፡ ዘፈን፤(ናት)፤ በቁሙ ዝላይ እስክታ፡፡”[2]
    የደስታ ክለ ወልድ መዝገበ ቃላትም “ዘፈን”[3] የሚለውን፣ “ዘፈን፤ (ዘፊን ዘፈነ)፤ ቀነቀነ አወረደ ግጥም ገጠመ፣ አዜመ፣ አንጐራጐረ፣ ዘለለ፣ ተውረገረገ፡፡” አሁንም ዘፈነ፤ ተንቀጠቀጠ ተንዘፈዘፈ፡፡ ዘፋኝ(ኞች)፤ የዘፈነ የሚዘፍን፤ አውራጅ አንጐራጓሪ ዘፈን ወዳድ(መዝ.፹፯፥፯)” በማለት ሲያስቀምጡት፣ ገላ.5፥21 ላይ የተቀመጠውን ዘፋኝነት የሚለውን ሃሳብ ደግሞ፣ “መጽሐፍ ግን መሶልሶል[4][ሶለሶለ - አንሶለሶለ፣ አዞር፣ አንቀዠቀዠ፣ አንቀለቀለ መንሶልሶል፣ መዞር፣ መንቀዥቀዥ] ይላል” በማለት ጥቅሱን ጠቅሰው አስቀምጠውታል፡፡
   ሰርጸ፣ ሽምጥጥ አድርጎ “የመጽሐፍ ቅዱስ መተርጉማን ሌላ ስያሜ ስላጡለት ዘፈን አሉ እንጂ ዘፈን መባል አይገባውም” የሚል ጽኑ አቋሙን ደጋግሞ አስተጋብቷል፡፡ ምናልባት ይህንን ሲል ሁሉን አዋቂ ነገር ጠንቃቂ ወደመሆን የተጠጋ ሳይመስለው፤ እንደሆነ ሳያስብ አልቀረም፡፡ ነገር ግን የእርሱን ሃሳብ መተርጉማኑም ሆኑ የቋንቋው ሊቃውንት ሲደግፉት ፈጽሞ አይታይም፡፡

Wednesday, 14 June 2017

አታወሳስቡብን!

ውስብስብ አይደለም ያልተብራራ ቅኔ
ለእርሱ እንደተገባሁ ኃጢአተኛው እኔ፤
ለብዙ ኃጢአቴ እልፍ ምሕረት ፈሶ

Sunday, 11 June 2017

ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አሥራ አንድ)

Please read in PDf
የምንዋጋው ከማን ጋር ነው?
    በአጭር ቃል፣ የየራሳችንን ሰባኪና ማኅበር፣ ዘማሪና መጋቢ፣ የሐሰት አጥማቂዎችን፣ የነቢያትና “መፍትሔ አምጪ ነን” ባይ የሆኑ የመጋብያን ትንቢተኞችን  … ቃል ከኢየሱስ ጌታችን ቃል ይልቅ በማድመጥና በመከተል ስተናል፡፡ ልክ እንዲሁ ከማን ጋር እንደምንዋጋ አለማወቃችን ከደካማው ፍጡር ጋር በመታገል ዘመናችንን እንድንጨርሰው አድርጐናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ከማን ጋር እንደምንዋጋ፥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ፤” (ኤፌ.6፥12) በማለት ገልጦታል፡፡

Thursday, 8 June 2017

ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አሥር)

Please read in PDF
5.  ውነተኛ ወታደር በማናቸውም የራሱ እቅድና ዝግጅት ቢኖረውም ዘወትር ግን ወደየትኛውም አቅጣጫ መሄድና ማናቸውንም ሥራዎች ለመሥራት ዝግጁ ነው፡፡ እውነተኛ ክርስቲያንም የራሱ የሆኑና በግሉ የሚሠራቸው ብዙ መልካም ነገሮች ሊኖሩት ይችላሉ፤ ነገር ግን በክርስትና ሕይወት ጉዞው ቀዳሚውና ዋናው የሚኖርለት የክርስቶስ ነገር ሊሆን ይገባዋል፡፡
      ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ላነሰ ኑሮ ልንኖር አልተጠራንም፡፡ ክርስቲያን ከእርሱ ላነሰ ኑሮ የሚኖር ከሆነ ከሁሉ ይልቅ ምስኪን ነው፡፡ የክርስቶስ የሆኑቱ ታማኞቹ ደቀ መዛሙርት፣ “በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮች” (ሐዋ.1፥8) የሆኑት፣ ለየትኛውም ለጌታችን ኢየሱስ ሥራ ዝግጁና በማናቸውም አቅጣጫ ቢሄዱ በደስታ በመታዘዝ ነበር፡፡ ለየትኛውም አገልግሎትና ለኢየሱስ ጌታችን ሥራ የጨከነና የበረታ ልብና መንፈስ ነበራቸው፡፡

Saturday, 3 June 2017

ሙሽሪትን ሊያስውብ

ክርስቶስ በሞቱ በደሙ ያቆማትን
ከፊት መጨማደድ ሊያጠራና “ሊያድን”
አዲስ ማኅበረሰብ አዲስ ልዩ ትውልድ

Thursday, 1 June 2017

ዘፈን - የወደቀው መልአክ እንጉርጉሮ (ክፍል 4)

Please read in PDF

የቤተ ክርስቲያን አባቶችም ዘፈንን በኀጢአትነቱ ገልጠዋል፤

   የቤተ ክርስቲያን አባቶች ስንል እንዲሁ ከምንም ነገር ተነስተን አይደለም፡፡ እኒህ አባቶች ለእውነተኛው የክርስትና ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ቆመው ዋጋ የከፈሉ በመሆናቸውና ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት “በመሟገታቸው” ነው፡፡ ትምህርቶቻቸው፣ ምክሮቻቸው፣ ተግሳጾቻቸው ብቻ ያይደለ የሕይወታቸውም ቅድስና ጭምር የተመሰከረላቸው፣ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነትና የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን አምነው የተቀበሉና በዚህም መሠረትነት ላይ ቆመው የጻፉ መሆናቸውን በመመዘን የምንቀበላቸው ናቸው፡፡
   ከእነዚሀ ቅዱሳን አባቶች መካከል ዘፈንን በግልጥ የተቃወመውና እንድንርቀው ያስተማረን አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው፡፡  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በተግሳጹ እንዲህ አለ፣ “ስለዚህ … ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችኋለሁ፡፡ ኀላፊ የሚሆን ፈቃደ ሥጋን ተዉት ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሲዘፍኑ ላደሩት ጧት ለዋሉት ማታ መሸታ መግዛትን ተው ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡”[1] “ዳግመኛም ሲሰስን እንዳየኸው ጋሬዳ፤ ዘፈን፤ ጨዋታ፤ መሸታ ወዳለበት ሲሔድ ብታየው፡፡ ይህንንም ይተው ዘንድ መላልሰህ ማልደው፡፡”[2]