Tuesday, 28 February 2017
Friday, 24 February 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል ስድስት)
Please read in PDF
5. ጌታ ኢየሱስ ራሱን እንደአገልጋይ ቆጠረ (ማቴ.20፥28)፤ “እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” በማለት፣ እንደአገልጋይ እንጂ “እንደጌታ” አለመምጣቱን ተናገረ፤ (ማር.10፥45 ፤ ፊል.2፥8)፡፡ ስለዚህም መብቱን ሁሉ ለእኛ ሲል ትቶ፣ ሕይወቱንም ጭምር ሊሰጥ መጣ፤ (ዮሐ.10፥11)፡፡ ኢየሱስ በማገልገሉ እኛ ወደድኅነተ ሥጋ ወነፍስ፣ በሞት ጥላ ሥር በጨለማ ውስጥ የነበርን ሕዝቦች በእርሱ መምጣትና መገለጥ፣ ዝቅ ብሎ እንደባርያ ማገልገል ወደሚደነቅ ብርሃንና ወደበዛ ሕይወት መጣን፤ አገልጋይ ለራሱ እንደማይኖር ጌታ ኢየሱስም ለአባቱ ትእዛዝና ፈቃድ እንጂ ለራሱ አልኖረም፤ ይህንንም በአንደበቱ፥ “አብም እንዳዘዘኝ፥ እንዲሁ አደርጋለሁ” “እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ” (ዮሐ.14፥31 ፤ 15፥10) ሲል ተናገረ፡፡

Tuesday, 21 February 2017
Friday, 17 February 2017
Tuesday, 14 February 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አምስት)
Please read in PDF
3. ለክርስቶስ አገልጋዮች የሆንነው በፈቃዳችን ነው፤ ደኅንነት በደመወዝ መልክ አይገኝም፤ ደኅንነት ሁል ጊዜ ከጸጋ ጋር ብቻ የተያያዘ ነው፡፡ ደኅንነት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ፣ በሠራነውም ሥራና ሰዓት አይወሰንም፡፡ ከጸደቅንና ከዳንን ደግሞ (1ቆሮ.6፥11)፣ ስለጸደቅንበትና ስለዳንንበት ነገር የምናውጀው እውነትና የምንመሰክረው ምስክርነት አለን፡፡

“ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ
ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም” (ኤፌ.2፥8-9) እንዲል አሁንም፣ ዘወትር መርሳት የሌለብን ነገር፣ መዳን
ጥረትን አይጠይቅም፤ አገልግሎት ግን ስለዳንንበትና እውነት መመስከርና ማወጅን ይጠይቃልና ጥረትን፣ ድካምን፣ የወዝ ጥሪትን፣ መውጣት
መውረዳችንን ይሻል፡፡ የምንለፋው ትሁታን አገልጋዮች ሆነን ነው፤ ዋጋችን በእርሱ እንጂ በሰው ወይም በሌላ
አካል ፈጽሞ አይደለም፡፡ ስለዚህም በፈቃድ አገልጋይ ከሆንለት ጌታ እንጂ ዋጋችንን ከማንም አንቀበልም፡፡ ጌታ አገልጋዮቹን የጠራቸው
በፈቃዳቸው ነው፤ “ተከተለኝ” በሚል አጭርና ግልጥ ጥሪ፡፡ ለ“ልዩ ሥራ” ካልሆነ በቀር ጌታ ማንንም አስገድዶ ጠርቶ አያውቅም፡፡
ሁሉን በፈቃዱ ስለሚጠራ የሚከፍለውንም ዋጋንም በተመለከተ፣ እንደወደደ መክፈል እንደሚችል በግልጥ ተናግሯል፤ (ማቴ.20፥11-15)፡፡
Thursday, 9 February 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አራት)
Please read in PDF
2. ሠራተኛ(አገልጋይ) ባሪያ ፦ “ባሪያ ተገዥ፤ አገልጋይ ሰው የተማረከ ወይም የተገዛ ግዝ፤ ውላጅ፡፡ …” [1] በማለት ይተረጉሙታል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፡፡ “ነጻነትና መብት የሌለው፥ በራሱ ፈቃድ የፈለገውን ማድረግ የማይችል፡፡ በመጀመርያ እግዚአብሔር አንዱን ለሌላው ባሪያ እንዲሆን አድርጎ አልፈጠረም፡፡ ቃሉ ለመጀመርያ ጊዜ በስካር ኃጢአት ከወደቀው ከኖኅ አንደበት ተገኘ፤ ዘፍ.9፥26፡፡” [2]

ቃሉ በመርገም መልክ ለካም ልጅ ለከነዓን የተነገረ ነው፤ እርግማኑ ከባድ
ከመሆኑም ባሻገር እግዚአብሔርን የማይወዱ[ለፈቃዱ የማይታዘዙ] ሁሉ የሚደርስባቸው እርግማን ነው፡፡ የራስን ወላጅ ሆነ የዘመድን
ኃፍረተ ሥጋ መመልከት አጸያፊና ነውር ነውና፤ (ዘሌ.18፥4-17) ይህን ያደረገው ከነዓን የባርነቱም እርግማን በትክክል ደርሶበት
አይቶታል፤ (ኢያ.16፥10)፡፡ ከዚህ በኋላ በባርነት መያዝና በዚያ መኖር የኃጢአት ውጤት አንዱ መገለጫ ሆኗል፡፡ ለዚህም የእስራኤል
ልጆች በመሳፍንት ዘመን በአረማውን እጅ በተደጋጋሚ መውደቃቸውንና በባቢሎንም መማረካቸው በቂ ምስክር ሆኖ በመጽሐፈ መሳፍንት ተጽፎ
አለ፡፡
Sunday, 5 February 2017
ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (የመጨረሻ ክፍል)
Please read in PDF
4. ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም፦ ጽድቅ የሚለው ቃል፣ ቀጥታ ከዕብራይስጥ የተቀዳ ሲሆን ትርጉሙ፥ ፍጹም ትክክለኛነት፣ ቀጥተኛ፣ ፍትሓዊ፣ በጐ ምግባር ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት “በትክክለኛ ሁኔታ” ላይ ሆኖ መገኘት ማለትን በግልጥ ያሳያል፡፡ እግዚአብሔር ከመጀመርያው ለሰው ያለው ሃሳቡ እንዲህ ነበር፡፡ ፍጹም ጻድቅና መልካም እንዲሆን፥ ሰው ግን በእግዚአብሔር ፊት በመልኩና በአምሳሉ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ወደገዛ መንገዱም በማዘንበል በምሳሌው እንደ መልኩ ማንነቱን በመያዝ (ዘፍ.5፥3) በኃጢአት ተሰነካክሎ ወደቀ፤ ከትክክለኛነትም ተሰናከለና በዕድፈት ረከሰ፡፡

መጥምቁ ዮሐንስ አስቀድሞ ጌታ ኢየሱስን
ለማጥመቅ ፈቃደኛ አልነበረም፤ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስ ምንም በደልና ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ጻድቅ መሆኑን አስተውሏልና፡፡ ስለዚህም
አብረውት ስለኃጢአታቸው ሊጠመቁ ከቆሙት እንደአንዱ ሊቆጥረው አልደፈረም፤ ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ከሁሉ የተለየ ልዩ መሆኑን የአዋጅ
ነጋሪው ሰው ተገነዘበ፡፡ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” በማለት፣ ራሱን ከኢየሱስ ጋር በማስተያየት፣
ዮሐንስ ራሱ መጠመቅ የሚያስፈልገው ፍጹም ኃጢአተኛ መሆኑን መሰከረ፡፡ በእርግጥም፣ ሰው ከሆነው ከኢየሱስ በቀር አንዳች ፍጹምና
ጻድቅ ከምድር ስለጠፋ ክርስቶስ ጽድቃችን ሊሆን መጣ፡፡ እርሱ አንዳች በደልና ነውር ያልተገኘበት ነውና ጽድቅን በመሥራት ለእግዚአብሔር አቀረበን፤ (ዕብ.4፥14 ፤ 1ጴጥ.2፥22-23)፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)