እንኳን ለብርሐነ ትንሣኤው መታሰቢያ
በዓል በሠላም አደረሳችሁ፡፡
የእስራኤል ልጆች የብሉይ ኪዳኑን ፋሲካ በተለያየ ዘመን እንዴት እንዳከበሩት
ስናስተውል እንዲህ የሚመስሉ ቁም ነገሮችን እናገኝበታለን፦
ü በሙሴ ዘመን፦ የመጀመርያው ፋሲካ እንዲፈጸም የተሰጠው ለሙሴ ሲሆን ይህም በፈርዖን
ቤት የበኵር ልጅ ሲገደል፥ በቤተ እስራኤል ይህ መቅሰፍት እንዳይደርስና እንዲያልፋቸው (ፋሲካ ማለት ማለፍ ማለት ነውና) ይህም
የዘለዓለም ሥርዓት እንዲሆናቸው ተሰጣቸው፡፡ (ዘጸ.12፥14) ለፋሲካው የሚቀርበው ጠቦት በግ “ነውር የሌለበት”(ዘጸ.12፥5)
ነው፡፡ ይህ በግ የሚበላው በመራራ ቅጠል እርሾ ከሌለበት ቂጣ እንዲሆን ታዘዋል፡፡ በእነዚህ የበዓል ቀናት እርሾ ያለበትን ቂጣ
የሚበላ፦ “ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል
ተለይቶ ይጥፋ” (ቁ.15) የሚል ግልጥ ማስጠንቀቂያ አለ፡፡ ስለዚህም ከዚህና ከሌሎችም ማስጠንቀቂያዎች የእስራኤል ልጆች ራሳቸውን
ይጠብቁ ነበር፡፡ (ዘኍል.9፥6)