Wednesday, 30 December 2015
Thursday, 24 December 2015
ክርስቲያን ያልሆኑት ኦርቶክሳውያን ወይስ ምህረተ አብ?! (ክፍል አንድ)
“ለትምህርትና
ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር” (2ጢሞ.3፥16) የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸውን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትንም
ሆነ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን መንፈስ ቅዱስ ለእኛ የሰጠው፥ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እናምን ዘንድ፥
አምነንም በስሙ ሕይወት ይሆንልን ዘንድ” ነው፡፡ (ዮሐ.20፥30-31)
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አንድና አንድ ፤ ግልጽና ግልጽ እንጂ ስውርና
ውስብስብ ፣ ለሰዎች እንዳይገባና እንዳይረዱት ተደርጎ የተጻፈ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅን የማዳን ተስፋና ተስፋው በኢየሱስ
ክርስቶስ መምጣት ፤ መሞትና መነሳት የተፈጸመ መሆኑን በማስረዳት ይህን መዳን የምሥራች ብለን ለፍጥረት ሁሉ በድፍረት ከመንፈስ
ቅዱስ ጉልበት የተነሳ እንድንናገር እንጂ ሌላ ስውር አጀንዳ የለውም፡፡ ጌታችን የመምጣቱን ምስጢር ራሱ ሲናገር፥ “እኔ ሕይወት
እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ” (ዮሐ.10፥10) ሲል ፤ ደቀ መዛሙርቱም ፤ “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደዓለም
መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው” (1ጢሞ.1፥15) በማለት መሰከሩ፡፡ ለቤተ ክርስቲያንም የተሰጠው ትልቁ ተልእኮና አደራ “ሂዱና
አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት
አድርጓቸው” የሚል አለም አቀፍ ጥሪና ሰፊ የመከር ሥራ ነው፡፡ (ማቴ.28፥19)
Friday, 18 December 2015
ግጭትና ጦርነት የማያስተምራት አገር
ስለራሳችን እንዲህ እንናገራለን ፦
-
እንግዳ ተቀባይ ሕዝቦች ነን ፤
-
ብዙ ብሔር ብሔረሶችና ሕዝቦች ተዋደው የሚኖሩባት አገር አለን ፤
-
ለቁጥር የሚታክት “ክርስቲያን” ፣ እልፍ አዕላፍ ገዳም ፣ መድረክ የሚያጨናንቁ
አገልጋይ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናትና ዘማርያን አሉን ፤
-
ከእኛ ወዲህ ማን አለ አማኝ? ከእኛ በላይ ጸዳቂ ፤ ታማኝ አገር ወዳድ
ወዴት አለ?! …
ስንታይ ግን፦
-
አገልጋዮቻችን ጸንሰው ወልደው ፣ አሳድገው የሰጡን አንዱ መልክ ዘረኝነትና
ልዩነት ነው ፤
-
ከእኛ በላይ ሁሌም ሰው የለም ብንልም ዘወትር ግን እየኖርን ያለነው ከሰው
በታች ጅራት ሆነን ነው …
ሰሞኑን በከፊል የአገራችን ክፍል
ብጥብጥና ሁከት ፤ ደም ማፍሰስና ግድያ ነግሶ ነበር፡፡ ይህን ሁሉ አድራጊው ሌላ ወራሪ ወይም እንግዳ አሸባሪ መጥቶብን አይደለም
፤ ሟችም እኛው፥ ገዳይም ያው እኛው ኢትዮጲያውያን ፤ ንብረት አውዳሚም፥ ንብረት የሚወድምበትም ያው የአንድ አገር ዜጎች ፤ የአንድ
ርስት ወሰንተኞች ፤ የአንድ ወንዝ ጠጪዎች እኛው ነን፡፡
እስኪ አስተውሉ፥ አንድ መቶ ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በእኛና እኛ መካከል
የተደረጉ ጦርነቶችን ብናነሳ፦ በ1909 ዓ.ም በራስ ተፈሪና በንጉሥ ሚካኤል መካከል በሰገሌ ፣ በ1922 ዓ.ም በራስ ተፈሪና በራስ
ጕግሳ በአንቺም ወይም በበጌምድር ፣ ከ1966-1983 ዓ.ም ወታደራዊው መንግሥት ደርግና ኢሕአዴግ በተለያየ ቦታ ያደረጉት አስቀያሚ
ጦርነት ፣ በ1994 ዓ.ም ሁለቱ “ወንድማማች” ኢትዮጲያና ኤርትራ ያደረጉትን ጦርነት (ወታደራዊው መንግሥት በአንድ ጉድጓድ የፈጃቸው
የንጉሡ ዘመን መሪዎችና ሌሎችም ሳይካተቱ) ይህን ሁሉ ስናነሳ ምን ይታወሰናል?!
Tuesday, 15 December 2015
ቃሉ የሚለው፥ “ከቶ አላወቅኋችሁም ፤” ነው!
በመጽሐፍ ቅዱስ በአገባቡ ወይም እንደተጻፈው ከማይነበቡ
ጥቅሶች መካከል አንዱ፦ “ … ከቶ አላወቅኋችሁም ፤ እናንተ ዓመፀኞች ፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” (ማቴ.7፥23) በማለት
የተጻፈልን ቃል ነው፡፡ ይህ ክፍልና ሌሎችም ከዚሁ ጋር የተያያዙም ንባባት ለአፈጻጸም ከፍ ያለ የሥነ ምግባርና የፍጽምናን መንገድ ይፈልጋሉ፡፡
ከዚህም የተነሳ ብዙዎች የተራራው ትምህርት ተብለው የሚታመኑትን ቃላት ማንም ሰው መፈጸም እንደማይቻለው ያስተምራሉ፡፡ በእርግጥም
የእግዚአብሔርን ማናቸውንም ሥራ በእግዚአብሔር ጉልበት ፤ ራሱ እግዚአብሔርንም መማር የሚቻለን በራሱ በእግዚአብሔር ዕውቀት ገላጭነትና
የጥበብ አስተማሪነት ነው፡፡ ይህ ማለት ግን የተራራውን ትምህርት በራሱ በእግዚአብሔር ጉልበትና መንፈስ መፈጸም ይቻለናል ማለት
እንጂ ፈጽሞ መፈጸም አይቻልም ማለት አይደለም፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ትምህርቱ ያስተማራቸው ትምህርቶቹ
በብዙዎች ዘንድ እጅግ የተደነቁና የሚያስደምሙ ትምህርቶች ናቸው፡፡ እውነትም! የእግዚአብሔር አምላካችን መንገድና ሕጉ ፤ ሥራውም
ፍጹም ነውና (ዘዳግ.25፥15 ፤ መዝ.18፥30 ፤19፥7) ፤ እኛም በእርሱ ዘንድ (ዘዳግ.18፥13) ፤ እንደእርሱም ፍጹማን እንሆን
ዘንድ ተጠርተናል፡፡ (ዘፍጥ.17፥1 ፤ ማቴ.5፥48 ፤ 19፥21) አዎን! የእግዚአብሔር ቅዱሳንም በፊቱ ያለነውርና ነቀፋ ነበሩ፡፡
(ዘፍጥ.6፥9 ፤ 1ነገ.11፥4 ፤ ኢዮ.1፥1 ፤ ሉቃ.1፥6 ፤ 2፥25) ፍጽምና ወይም በእግዚአብሔር
ፊት የበቃ ሆኖ መገኘት ለሰው የሚቻል ነገር አይደለም (ሮሜ.3፥11 ፤ 2ቆሮ.3፥5) ስለዚህም ስለፍጽምናና ቅድስና
ስናስብ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በተሰጠን ጸጋ እንጂ (ሮሜ.3፥21-24) በሕግ ወይም በራሳችን የምናደርገውም ፤ እናደርገውም
ዘንድ የሚገባን አንዳችም ነገር የለም፡፡
Friday, 11 December 2015
ወንድሜ ማን ነው? (ክፍል ሁለት)
ቃየን በልቡ ያሰላሰለውን ኃጢአት ከፍጻሜ ማድረስ አድብቷል፡፡ “ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም
በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።” (መዝ.10፥1) እንዲል ልበ ቅኑን አቤልን ይነድፍ ዘንድ ቃየን
በስውር ይናደፍ ዘንድ ተነሳ፡፡ ስለዚህም፥ “ቃየንም ወንድሙን አቤልን፦ ና ወደሜዳ እንሂድ አለው።” ልምድ ያላቸው ወንጀለኞች
“ትልቁ ክፋታቸው” ወንጀሉ እንዳይታወቅና ፤ እውነተኛ ፍርድ እንዳያገኙ የምስክር ደብዛ ያጠፋሉ፡፡
ቃየን ወንድሙን “ወደሜዳ እንሂድ” ያለው አብሮት ሊጫወት ፤ እንደወንድምም
ሊያወጋው አይደለም፡፡ አቤል ግን ወንድሜ እንዲህ ያደርግብኛል ስላላለ
አብሮት ሄደ፡፡ ለዳኝነት ብይን መስጫው ቁልፉ ምስክር ወይም ማስረጃ ነው፡፡ ቃየን ያለምስክር “በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል
ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።” (ዘፍጥ.4፥8) የጨለማ ሥራ ካልተሸሸገ በቀር ብቻውን መቆም አይችልም፡፡ “የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ
ትወዳላችሁ።” (ዮሐ.8፥44) እንደተባለ የዲያብሎስን ፈቃድ ሊያደርግ እግሩን አስቸኰለ፡፡ ኃጢአተኞች ትልቁን ምስክር ህሊናቸውን ዘንግተው
የሰው ምስክር ይሸሻሉ፡፡ እግዚአብሔር ግን ሁሉን ያያል!!!
Sunday, 6 December 2015
ጌታ ካላለበት
ከመድረኩ ቆመህ ከአውደ ምህረቱ፤
ተፋተህ ተራቁተህ ከእግዚአብሔር ፍርሃቱ፤
“በʻኔ የሚናገር ጌታ ነው” በማለት፤
ለምን ትጮኻለህ? የውስጥህን ክህደት፤
Friday, 4 December 2015
ድንግል ማርያም በድንግል ማርያም አንደበት (የመጨረሻ ክፍል)
6.
የእግዚአብሔርን
መጋቢነት
“የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል ፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን
ሰዶአቸዋል።” (ሉቃ.1፥53)
እግዚአብሔር የተራቡትን ከመራባቸው በፊት አዝኖ ሲያስብላቸው (ዘፍጥ.41፥25
፤ ሐዋ.11፥28) ፤ በተራቡና በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ሲያጠግባቸው አይተናል፡፡ (ዘፍጥ.41፥54-56 ፤ ዘጸ.16፥6-18 ፤ ማቴ.6፥26
፤ 31-32) ድንግል ማርያም በምድር ላይ ትኖር በነበረችበት ወራት ድኃ እንደነበረች የሚያሳየን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አለ፡፡
(ሉቃ.2፥22-24) በእርሱ መጥገብንም በሚገባ ታውቀዋለች፡፡ እንዲህ ያለውን ምስክርነት “ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፥ ተርበው
የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል” በማለት ቅድስት ሐናም ምስክርነት ስትሰጥ እናያለን፡፡ (1ሳሙ.2፥6)
Tuesday, 1 December 2015
የኖድ ምድሩ ሰው (ዘፍጥ.4፥16)
እግዚአብሔር ፍጥረትን ከፈጠረበት ጥበብ በሚልቅ ጥበብ፥ የሰውን ልጅ
ፈጠረው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እንደሚሉትም ሌሎቹን በቃልና በዝምታ ሲፈጥር ሰውን ግን “በእጁ አበጅቶ ግብር እምግብር”
ፈጠረው ይሉናል፡፡ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም፥ ሰው እጅግ በታላቅ ክብርና ሞገስ መፈጠሩን ይናገራሉ፡፡ (ዘፍ.1፥27 ፤
2፥7 ፤ መዝ.139፥14 ፤ 145፥10) ዕለትም ዕለትም ከእግዚአብሔር ጋር እጅግ የሚያስደንቅ ንግግርና ጨዋታ ያደርግ እንደነበርም
ታላቁ መጽሐፍ ሲነግረን ልባችን እጅግ መደመሙና እጁን በአፍ ጭኖ መደነቁ አይቀርም ፤ ትልቁ ጌታ ከፍጡሩ ጋር ዕለት ዕለት እንደመነጋገር
የሚያስደንቅ ምን አለ!? (ዘፍጥ.3፥8)
ታላቁ መጽሐፍ፥ ዘፍጥረት ምዕራፍ አንድንና ሁለትን እጅግ የሚደንቅ ትስስር
ከአምላኩ ጋር እንደነበረው የሚነግረን ብዙም ሳይርቅ በሦስተኛው ምዕራፍ አሳዛኙን ውድቀት ይነግረናል፡፡ ዔደን ገነት ልዩና የእግዚአብሔር
ሠላም የሰፈነባት ሆና ለሰው ልጅ የተሰጠች ፤ እንዲሁም የሰው ልጅ ቅዱስና ጻድቅ እግዚአብሔር ራሱን በሚገልጥበት በኪሩቤል አጠገብ
መኖር እንዳልሆነለት ፥ በኃጢአት ምክንያት ሁከት ፣ ፍርሃት ፣ ሽሽት ፣ ዔደን ገነት ጭንቀት የሰፈነባት ሆና ሰው ማረፊያ ሲያጣባት
እናስተውላለን፡፡ ኖድ ማለት የስሙ ትርጓሜ መቅበዝበዝ ማለት ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)