የክርስቶስ አገልጋይ ትጥቁ አጭር (ማቴ.10፥5-11) ፤ ዕለት ዕለት
መስቀሉን ተሸክሞ በመከተል የሚኖር (ማር.8፥34) ፤በቁም ሳለ ከሚገድል ቅምጥልነት የራቀና “ወደዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥
አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል።” የሚል ቅዱስ አቋም ያለው (1ጢሞ.5፥6 ፤ 6፥7-8)
፤ በሕይወቱ (ሮሜ.12፥2) ፣ በንግግሩ (ቈላ.4፥6) ፣ በመንገዱ ሁሉ የአምላኩን ስም የሚያስመሠግንና ከማስነቀፍ ፈጽሞ የራቀ
፤ ለሁልጊዜ ለፈጣሪው የሚያደላና የሚኖር ፤ ለሕይወቱ ምሳሌና መርሕ የሚሆነውን ነገር ለመፈለግ ሁልጊዜ እግረ ልቡን ወደ ታላቁ
ቅዱስ መጽሐፍ የሚያቀና ሊሆን ይገባዋል፡፡ (ሐዋ.17፥10 ፤ 1ዮሐ.4፥1)
እንዲህ ስል አገልጋይ
ባዕለ ጠጋ መሆን የለበትም የሚል አቋም የለኝም ፤ ዳሩ ግን አማኝም ሆነ አገልጋይ መሠረታዊ የሆነውን ነገር፥ ማለትም ምግብን ፣
ልብስንና መጠለያ በማግኘቱ ፣ እርካታ ይኖረው ዘንድ አስፈላጊ ፤ የተገባም ነው፡፡ ይህ ማለት አገልጋይ እንደሚሠራው ሁሉ አገባብ
ያለው ደመወዙ ይገባዋል ማለት ነው፡፡ እንዲሁ ገንዘብ የሚጠይቅ የተለየ ነገ ርቢከሰት ፣ በልግስና በመስጠት እግዚአብሔርን እያገለገለ
(2ቆሮ.8፥3 ፤ 9፥6) “በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።” እንዲል፥ እግዚአብሔር እንዲሰጠው ወደእርሱ
መመልከት ይኖርበታል፡፡ (መዝ.50፣15) ይህንን የምንለው ሁልጊዜ መንግሥቱንና ጽድቁን መቅደምና ማስከተል ከሌለብን ብቻ ነው፡፡
(ማቴ.6፥33)