Sunday, 31 May 2015

ለመኪና ሸላሚዎችና ተሸላሚዎች “አማኞች” ምክር ቢሆን!



    “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር” (ዘዳ.25፥4 ፤ 1ቆሮ.9፥9)

  ቅዱስ ነቢይ ሙሴ፥ እስራኤል የሚገለገሉባቸውን እንሰሳት በተለይም በሬ እያበራየ ባለበት ወቅት ጤንነቱ እንዲጠበቅ በቂ ምግብ ማግኘት እንዳለበት ሕዝቡን ያዛል፡፡ ይህም በመራራት ፣ የሚሰጡትን አገልግሎት በማሰብ እንሰሳቱን መንከባከብ ፣ ተመጣጣኝና የሚበቃቸውን ያህል መብልን ሊሰጣቸው እንደሚገባ ያሳስባል፡፡ ይህ ለእንሰሳት የተነገረው ቃል ፥ በአዲስ ኪዳን ቃል በቃል ለጌታ ወንጌል አገልጋዮች የአገልግሎት መርሕ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

Friday, 29 May 2015

ቅዱስ ሲኖዶስና የመሰብሰቡ ዓላማ (ክፍል - 2)

     

                                                                    Please read in PDF      

 
  “በበጋና በበልግ ወራት ቸነፈር የድንገት ሞት ይበዛልና ከሞት አስቀድሞ ፍቅር ሰላም ይሆን ዘንድ፡፡” እንዲል  “ … ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።” (1ጢሞ.5፥8) በሚራራና በፍቅር ስስት ለሃይማኖት ቤተሰብ ማሰብ ከአማኝ ሁሉ የሚጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታ ነው፡፡ ከአንደኛው ሃሳብ ጋር ብናስተሳስረው የአምልኮዓችን ጤንነት ያለው ለባልንጀራችን ባለን የርኅራኄ ዕይታ ነው፡፡ ባልንጀራችን ለአደጋ ተጋልጦ (ሉቃ.10፥29-37) ፣ ተርቦ ፣ ተጠምቶ ፣ ታርዞ ፣ ታስሮ (ማቴ.25፥37-40) ፤ በስደትና በመቅበዝበዝ ሲኖር ሳለ እኛ ተቀማጥለን ልብስና ምግብ በማማረጥ ያማሩ ቤቶች ሠርቶ ዕቃዎችን በመገጥገጥ እንድንኖር ክርስቲያናዊ አስተምህሮም ሆነ ትውፊቱ በዝምታ ይነቅፈናል፡፡

Saturday, 23 May 2015

ድል የነሣው ጌታ - አርጓል!



   
  ጌታ ወደሰማያት ያረገው ከአባቱ ዘንድ የተላከበትን ዋናውን ዓላማውን “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤” (ዮሐ.17፥4 ፤ 13፥31) በማለት ፈጽሞ (ዮሐ.19፥30) ያከናወነ መሆኑን ተናግሯል፡፡ (ዮሐ.19፥30) ጌታችን ከአባቱ ዘንድ የተላከበት ዋና ዓላማው፥ የሰውን ልጅ ከዘላለም ሞትና ቀንበር ማዳን ነው፡፡ (ሉቃ.9፥56 ፤ 19፥10 ፤ ዮሐ.3፥15 ፤ 17 ፤ 8፥15) ይህንን በመስቀል ላይ በሠራው የፍቅር ሥራው ፈጽሞታል፡፡ ድል መንሳቱንና የሰው ልጆችን መዳን መፈጸሙን ስናነሳ ፥ በጌታ የሆነውን ሁለት ነገሮች ማስታወስ ግድ ይለናል፡፡

Monday, 18 May 2015

ቅዱስ ሲኖዶስና የመሰብሰቡ ዓላማ (ክፍል - 1)


“በየቦታው ሁሉ ኤጲስቆጶሳት በያመቱ ሁለት ጊዜ ከጳጳሳቸው ወይም ከሊቀ ጳጳሳቸው ዘንድ ይሰብሰቡ፡፡ መጀመርያ ከጾመ ፵ በፊት ይሁን፡፡ ክፉንና ቁጣን በሚያርቁ ገንዘብ ቁርባናቸውም ለእግዚአብሔር ንጽሕት ክብርት ቅድስት ትሆን ዘንድ፡፡ ሁለተኛውም ከበዓለ መስቀል በኋላ በመከር ወራት ይሁን፡፡ በበጋና በበልግ ወራት ቸነፈር የድንገት ሞት ይበዛልና ከሞት አስቀድሞ ፍቅር ሰላም ይሆን ዘንድ፡፡ ወደጌታችን ወደኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ንጽሕና በሚቀርቡ ገንዘብ፡፡ ከካህናት ወገን ወይም ከሕዝቡ ወገን ቢሆን ኤጲስ ቆጶስ አውግዞ የለየውን ሰው ፍርድ ይመረምሩ ቸልታ እንዳይሆን ወይም ይህን በሚመስል ነገር ሁሉ እንደተገለጠላቸው ይፈርዱ ዘንድ፡፡”
(ፍትሐ ነገሥት አን.5 ቁ.165 ገጽ 61)

Thursday, 14 May 2015

ከሳሽ ዕድፉን ሳያይ ...


               Please read in PDF
         

ስታመነዝር አገኘናት፣
ብለው አካልበዋት፣
ከጌታ ፊት እያቻኮሉ፣
ከእግሩ ሥር አምጥተዋት ጣሉ፡፡

Friday, 8 May 2015

“ … ለደቀ መዛሙርቱ እንደገና ተገለጠላቸው” (ዮሐ.21፥1)

  

  ጌታችን ከሙታን መካከል ከመነሳቱ በፊት ገና በተሰቀለ ጊዜ በደቀ መዛሙርቱ ልብ የቀረው ነገር እጅግ አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ እንዲያውም ተስፋ እስከመቁረጥም አድርሷቸው ሉቃስና ቀለዮጳ ወደመጡባት ከተማ ወደኤማሁስ(ሉቃ.24፥13) ፥ ብዙዎቹም ጥለው እንደሸሹ ያልተመለሱ ሲሆን (ማቴ.26፥56) ፥ ስምዖን ጴጥሮስ ፣ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ፣ ናትናኤል ፣ የዘብዴዎስ ሁለቱ ልጆች (ያዕቆብና ዮሐንስ) ደግሞ እጅግ ተስፋ ከመቁረጥ የተነሳ የዕለት ጉርሳቸውንና የዓመት ልብሳቸውን ለመሸፈን ጌታ እነርሱን ከጠራበትና ትተውት ተከትለውት ወደነበረው (ማቴ.4፥18 ፤ ዮሐ.21፥1) ወደቀደመ ህይወታቸው አሳ አስጋሪነት(አጥማጅነት) ተመልሰው ተሰማሩ፡፡

Monday, 4 May 2015

ሁለት ብዕርና ምላስ ላላቸው “ሰባኪዎች” ሙግት አለኝ!

     
                                      Please read in PDF            

   ሰሞኑን በISIS ከታረዱት ወገኖቻችን መካከል ኤፍሬም የማነ ስለተባለ ኤርትራዊ ወንድማችን ቀድሞ ሲወራ የነበረው ጀማል በሚል የእልምና ስም እንደሆነና የእምነቱም ተከታይ እንደሆነ ፤ አብሮ ለመሰዋት በመወሰኑ ከክርስቲያን ወንድሞቹ ጋር መታረዱን ብዙ ንግግሮችና ጽሁፎችን አድምጠንም ፤ አንብበንም ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ሲነገሩም የነበሩ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ አስተምህሯዊ ንግግሮች ስናደምጥም ፤ ስናነብም ታዝበናል፡፡ በተጨማሪም ጥቂት የማይባሉ ሰባኪዎች የቤተ ክህነቱንና የቤተ መንግሥቱን የሚድያና የስብከት አውደ ምህረትን ተቆጣጥረው “ጀማል ከክርስቲያን ወንድሞቹ ጋር ሰማዕት ሆነ” በሚለው ዙርያ የተናገሩትንም ሰምተናል ፤ የጻፉትንም አይተናል፡፡ እኒህ ሰባኪዎች ደስ ሲላቸው ራሳቸውን እንደ“ተመራማሪ” ፥ ሲላቸው ደግሞ እንደየ“ፖለቲካ ተንታኝ” ቆጥረው ሳያበቁ “የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ሙላት” እንዳላቸውም ደግሞ ለመስበክ ደፍረው ሲቀርቡም እናያለን፡፡