መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ የቤተ ክርስቲያንን
ታሪክ ስናጠና ጸጋ ልዩ ልዩ እንደሆነ ፤ ነገር ግን መጋረጃን እንደሚያያይዘው ኩላብ የተያያዙና አንድን አካል እንደመሥራት ያሉ
እንደሆኑ እናስተውላለን፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ጸጋዎችን ለቤተ ክርስቲያን አማኞች የሚሰጠው የጸጋ ድኃ እንደሌለና
የቤተ ክርስቲያንን ምልአት ለማሳየት ነው፡፡ በጸጋ ትምህርት ትንሽ የሚባል ጸጋ ከሌለ ሁሉም እኩል ሊከበሩና አገባብ ያለው ሥፍራ
፤ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በጳጳስነት ጸጋ እንደ ኤፌሶን ሽማግሌዎች የሚመራ አማኝ ፥(ሐዋ.20፥28) የእርሱ
ጸጋ ቃሉን እንደልድያ በመስማት ልቡ ከተከፈተለት ሰው ጋር (ሐዋ.16፥14) ምንም የጸጋ ልዩነት የለውም፡፡
Wednesday, 28 January 2015
Thursday, 22 January 2015
ዕድሜና ፍሬያችን
ከትላንት በስቲያ …
አሜሪካ ʻምትባል ትልቅዬ አገር
በአንድ መልሳ ፣ የሥጋ መንፈስዋን ፣ ክፍልፍሉን መንደር
ʻስቴቶቿን ሁሉ ቀምራ አዋህዳ
ተተኮሰች “አሉ” አድጋ ተመንድጋ
እኛን እዚህ ትታ እርሷ ወደህዋ …
Sunday, 18 January 2015
“የምወድህ ልጄ አንተ ነህ …” (ማር.1፥10)
ጌታ የማስተማር አገልግሎቱን ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ሲሆን (ሉቃ.3፥23)
በግልጥ ለማገልገልና ለመጠመቅ ከመውጣቱ በፊት ይኖር የነበረው ደግሞ በገሊላ ናዝሬት ነው፡፡ (ማቴ.2፥23) ናዝሬት በብሉይ ኪዳን
በአንድም ሥፍራ ስሟ ያልተጠቀሰችና የማትታወቅ ከተማ ናት፡፡ ናዝሬት የማትታወቅና ያልተጠቀሰች ከተማ ብትሆንም፥ ለጌታ ኢየሱስ “ቅጥያ
ስያሜ” ሆና “የናዝሬቱ ኢየሱስ” ለመባል የበቃች ከተማ ናት፡፡ ጌታ “የናዝሬቱ ኢየሱስ” የተባለው ስለተወለደባትና ስላደገባት ብቻ እንጂ እንደነሶምሶን
“ልዩ ናዝራዊ” ለመባል አይደለም፡፡
Monday, 12 January 2015
ፊደል ከንባብ ፤ መንፈስ ከትርጓሜ ይስማማልን?
“የሥጋ ሕግ
ያጠፋል፤ የነፍስ ሕግ ግን ያድነናልና”
(በግርማዊ ቀዳ. ኃይለ ሥላሴ ንጉሰ
ነገስት ዘኢትዮጲያ
መልካም ፈቃድ
በአሜሪካ ከታተመው የ1938 ዓ.ም
መጽሐፍ ቅዱስ ከታተመ የተወሰደ፡፡
ገጽ. 386)
በማስጨነቅ ወይም እጅ በመጠምዘዝ ከሚተረጎሙ የመጽሐፍ
ቅዱስ ክፍሎች አንዱ ከላይ በርዕሳችን ያነሳነው ቃል በብዛት ይዘወተራል፡፡ ይህንን ቃል ብዙ ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ በሕዝብ ዘንድ
“ተቀባይነት ያላቸው” የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ሰባኪዎች ጭምር በመጽሐፎቻቸውና በስብከቶቻቸው መሐል ከመጽሐፉ ሐሳብ ውጪ በመውጣትና
ወደራስ ሃሳብ በመሳብ ሲተረጉሙት አይተናል፤ ሰምተናልም፡፡
Tuesday, 6 January 2015
የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ልዩ ነው!
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
መታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!!
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተወልዷል፡፡ መወለዱም “ልደተ አዳም እምድር ፤ ልደተ ሔዋን እምገቦ ፤ ልደተ አቤል እምከርሥ ፤ ልደተ በግዕ እምዕፅ ፤ ልደተ
ሙታን እመቃብር” እንደሆነው ያይደለ የእርሱ ከዚህ የተለየ ልዩ ልደት ነው፡፡ (ወንጌል አንድምታ፤ ከቀድሞ አባቶች ጀምሮ ሲወርድ
ሲዋረድ የመጣው ንባብና ትርጓሜው ፤ 1997፤ በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ድርጅት የታተመ፤ ገጽ.44) እርሱ የተወለደው ከእመቤታችን
ከቅድስት ድንግል ማርያም ፤ ከሰው ነው፡፡ ለዚህም ነው ወንጌላዊው “ቃል ሥጋ ሆነ” ብሎ ሳያበቃ ፤ “ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ
በእኛ አደረ” ሲል የእኛን ሥጋ መዋሐዱን በማስረገጥ የተናገረው፡፡(ዮሐ.1፥1 ፤ 14)
Friday, 2 January 2015
Subscribe to:
Posts (Atom)