ይህ ጽሁፍ በዚህ
ብሎግ በመጀመርያ ሲወጣ ተቃዋሚዎች ገጥመውታል፤ በተቃውሞው ምክንያትም ለጊዜው ከዚህ ብሎግ ላይ ለማንሳትና ያለውን ነገር ለማጤን
ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ነገር ግን ቁጣውና ተቃውሞው ለእግዚአብሔር ስላላደላና ኃጢአትን ስላልተቃወመ ምንም ሳልቀንሰው ሙሉ ጽሁፉን
እንዳለ መልሼ አውጥቼዋለሁ፡፡ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው ፊት አናደላም፤ የሚያስጨንቀን የቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ሸክም እንጂ
በእግዚአብሔር ምህረት ላይ ለሚዘብቱና ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መነቀፍ ግድ ለማይላቸው አይደለም!!!
ስለግብረ ሰዶም ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጉልበት ቤተ ክርስቲያንን ስለሚያሳድፍ
ስለየትኛውም ነውር ለክርስቶስ አድልተን ከመገሰጽ ዝም አንልም፡፡ ግብረ ሰዶም አገር እያካለለ ለመሆኑ የቅርብ ሌላ ማሳያ ብናመጣ፤
ሬድዮ ፋና “የአመቱ የፍቅር አሸናፊ ግጥም” ብሎ በግዮን ሆቴል በሸለመው ሽልማትና በራሱ ሬድዮ በትላንትናው ዕለት የለፈፈው ከሴት
ለሴት የተጻፈ “የፍቅር ግጥምን” ነው፡፡ መቼም በአገራችን የፍቅር ግጥም ብሎ ከሴት ለሴት የሚጻፍ ይኖራል ብሎ ማሰብ ወይ የአገርን
ባህል መናቅ፤ ወይ ግብረ ሰዶምን መደገፍ እንጂ ሌላ ትርጉም አይሰጠውም፡፡
ይህንና ሌላም እየሰማን ዝም ለማለት የተቀበልነው አደራ አይፈቅድልንም፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ስለግብረ ሰዶማዊነት
በሁለት የተለያዩ ክፍሎች መጻፌና በሁለቱ ክፍሎችም ለጊዜው የነበረኝን ሃሳብ ማጠቃለሌን አልዘነጋውም፡፡ ነገር ግን አሁንም
ግብረ ሰዶማዊነት የቤተ ክርስቲያንን ቅድስና ከማርከስ፤ ምድራችንን ለከፋ ጉስቁልናና ርኩሰት አሳልፎ ከመስጠት ያላቆመ ፍጹም
ወደመስፋፋት የሄደ ክፉ ርኩሰት ነውና ዳግም ይህንን ርዕስ ማንሳት አስፈልጎኛል፡፡ ለዚህ እውነታ ብዙ የቅርብ ጊዜ ማሳያ ብቻ
ማንሳቱ በቂ ይመስለኛል፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ነው፡፡ የሠላሳ ሁለት አመት አጐት የአራት አመት የወንድም ልጁን
በእረኝነት ሥፍራ በመሄድ ጫት እንዲቅም ያግባባዋል፡፡ ህጻኑ እንቢ ቢልም ያስገድደዋል፡፡ ጫት እንዲቅም ካስገደደው በኋላ ልጁ
ራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው ልጁን የግብረ ሰዶም ጥቃት ይፈጽምበታል፡፡ የልጁ የሰገራ ማውጫ ሙሉ ለሙሉ ይቀዳዳል፡፡ ከሆዱ የወጣው
የውስጠኛው የሰገራው ክፍል ሙሉ ለሙሉ የልጁን ጠረን ይለውጠዋል፡፡ ልጁ ፍጹም ራሱን ስቶ ሲወድቅ ከወደቀበት ቦታ ተሸክሞት
ከወላጆቹ ጓሮ አምጥቶ ጥሎት ይሰወራል፡፡ ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የልጁ ህይወት ያልፋል፡፡