Please read in PDF :- kalu Yemaysera aybila aylim(part 1)
እግዚአብሔር ሠራተኛ ነው፤ ይሠራል፡፡እግዚአብሔር አገልጋይ ነው፤
ያገለግላል፡፡በፍጥረት መጀመርያ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ የተገለጠው ሠራተኛና ሠሪ ሆኖ ነው፡፡ፍጥረትን በዝምታ፣በቃሉና በድርጊት ፈጥሯል፡፡ሠራተኛ
ነውና ሲሰራ አይተነዋል፡፡የሠራውንም ለዓይኖቻችን ድንቅ ሆኖ አይተነዋል፡፡በአስገኚነቱና በፈጣሪነቱ የሚታወቀው ቀዳማዊ አካላዊ ቃል
ኢየሱስ ክርስቶስ “ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ ያልሆነ”(ዮሐ.1÷3) ፣ብርቱና አስገኚ ጌታ ነው፡፡ሁሉ
በእርሱ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር ወልድ አዛዥ የሌለበት ሠራተኛ ነው፡፡
እግዚአብሔር እርሱን እንድንመስልበት ከሰጠን ጠባዩ አንዱ ሥራ ነው፤እርሱ
ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ በሠራዒነቱ እንደሚንከባከብ ሁሉ የመጀመርያው ሰው አዳምንም ምንም ባልጎደለባት የተድላይቱ ምድር “ … ያበጃትም
ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።”(ዘፍ.2÷15)ይለናል፡፡ የመጀመርያው ሰው ሁሉንም በጸጋ ያገኘውና የተሠጠው ቢሆንም ሥራ
ፈት እንዳይሆን የማስተዳደርና የመንከባከብ የሥልጣን ሥራ በዚያ ሥራ ወዝና ድካም በማይጠይቅበት በገነቱ የጸጋ ዘመን ተሰጠው፡፡