Please read in PDF
ስለመብለጥ ሚዛናችንን ከቅዱስ ቃሉ አንጻር
ካላየንና ብልጫነትን ከሌላ ነገር ተነስተን
የምንመዝን ከሆነ በቅጽበት እድሜ ቃሉ
ያልፈቀደውንና ፈጽሞ የማይወደውን ሚዛን እናበጃለን፡፡በዓለም ላይ
ከሚገመተው ቁጥር በላይ የሆነው
ሰው የሚዋደቅለትና አብዝቶ የሚመኘው ነገር ቢኖር ብልጫነትን
ወይም መብለጥን ነው፡፡መቼም ለመልካምና እግዚአብሔር በሚወደው ነገር በቅዱስ ቅንአት ማደግና መጎልመስን ከዚህ እንደማናያይዘው ተስፋ
አደርጋለሁ፡፡ምክንያቱም በክርስትና ትምህርት ባደግን፣በቤቱ በኖርን ቁጥር መብለጣችንን ሳይሆን በተወደደ ትህትና አለልክ ዝቅ ብለን
ሁሉን ማገልገል እንዲገባን እንቆጥራለን እንጂ በአንዳች እንኳ የምንበልጥበት እንዳለን
በልባችን ሐሳብ አይገባንም፡፡
በእርግጥ ዛሬ ለምጽፋት "ትንስዬ" ጭብጤ ይህን
ብዬ ተንደረደርኩ እንጂ ዋና ሐሳቤ
ሌላ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የመስዋዕትን ህግ ለሙሴ ሲሰጠው
የተናገረውን ብዙ ጊዜ እንዲህ
ሲገለጥ እወደዋለሁ ፦ "ለእንሰሳ ቀንዱ ካልከረከረ፣ጠጉሩ ካላረረ፣ጥፍሩ ካልዘረዘረ
ከንጹህና ከተወደደው መካከል መርጦ" ፣ለእህል ቁርባኑ ደግሞ "ነቀዝ
ካልበላው ፣ወፍ ካልጠረጠረው፣ እንክርዳድ ከሌለው ከሰባውና "ከመልካም ዱቄቱ" መባሉን
አብዝቼ እወደዋለሁ፡፡በእርግጥ ቃሉም ይህን በሚገባ
ይገልጠዋል፡፡
እግዚአብሔር የብሉይ ኪዳኑን የሞትና የኩነኔ አገልግሎቱን እንኳ እንዴት ባለ ክብር
እንደወደደ እዩ!! እንኪያስ በደሙ የከበረውና
የመንፈስና የጽድቅ አገልግሎት የሆነው የምህረቱ ዘመን አገልግሎት እንዴት ባለክብር ይበልጥ ይሆን?እንደከበረው
ምርጡና ውድ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን
ትልቁና ዋናውን ነገር ቅዱስ ጳውሎስ
እንዲህ ብሎ ይገልጥልናል ፦