"... ወደ የትኛውም ሃይማኖት ዛሬ ተነስታችኹ ለመግባት ትችላላችሁ።
ጴንጤ ለመኾን ግን መመረጥ ያስፈልጋል" (በጋሻው ደሳለኝ)
“ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል
ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።” (ኢየሱስ ክርስቶስ - ዮሐ. 10፥16)
"... ወደ የትኛውም ሃይማኖት ዛሬ ተነስታችኹ ለመግባት ትችላላችሁ።
ጴንጤ ለመኾን ግን መመረጥ ያስፈልጋል" (በጋሻው ደሳለኝ)
“ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል
ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።” (ኢየሱስ ክርስቶስ - ዮሐ. 10፥16)
የትምህርትም፤ የምግባርም ውድቀት፣ የቤተ ክርስቲያንን ኹለንተናዊ መልክ
ከሚያበላሹ መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። ትምህርቱ እንደ ኑፋቄ ያለ ሲኾን፣ ምግባራዊ ውድቀቱ ደግሞ እንደ ሰዶማዊነትና
ዓለማዊነት ያሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲከሰቱ እጅግ ጆሮን ጭው ያደርጋሉ። እኒህን ተግባራት የሚፈጽሙ ሰዎች አንዳንድ[?] በ“ሃይማኖት”
ጥላ ሥር ያሉ ሰዎች ስለ መኾናቸው ብዙዎቻን እማኝ ነን።
ዘነበ ወላ፣ ሰሞኑን ሥራና ምናኔን አስመልክቶ የሰጠው አስተያየት በብዙ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ጥርስ አስነክሶበታል። ብዙ ኦርቶዶክሳውያን የሰላ ትችት ሲሰነዘርባቸው፣ ችግሮቻቸውንና ስህተቶቻቸውን ከማረቅ ይልቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማዋረድ የሚነገር አድርጎ ማሰብ፣ “ልጅ እናቷን ምጥ አታስተምርም” የሚል አጉል ፈሊጥ መጥቀስ፣ ዛሬ መጥታችኹ ቤተ ክርስቲያንን ወንጌል ልትሰብኳት፣ ችግሯን ልታመለክቱ አትችሉም … የሚሉ አያሌ አሉታዊ ምላሾች ይቀርባሉ። ይህን ስንል ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዋረድ የሚሠሩ የሉም ማለት አልችልም። ይኹንና ደግመን ደጋግመን መናገር የምንፈልገው፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ወደ እውነተኛ የወንጌል ጐዳና እስክትመለስና በመካከልዋ ያለውን “ዕድፍና ጉድፍ” እስክታስወግድ ድረስ “የተሐድሶ ድምጽ” ማሰማታችንን አናቆምም!
የእግዚአብሔር መግቦት እጅግ አስደናቂ ነው። ጌታ ፍጹም መጋቢ ስለ ኾነ
በፍጥረት መካከል አድልዎ ሳያደርግ የሚተገብራቸው አያሌ መግቦቶች አሉ፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዋቢ አድርገን ምሳሌ ብንጠቅስ፦ “ርሱ[እግዚአብሔር] በክፎዎችና በበጎዎች
ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” (ማቴ. 5፥44)፣ እንዲኹም እግዚአብሔር አምላክ ጋብቻን ባርኮ
ለመላለሙ በአምላካዊ መግቦቱ መስጠቱን እናስተውላለን፤ (ዘፍ. 2፥24፤ ማቴ. 19፥4-5)።
በእስራኤል ልጆች ታሪክ ውስጥ አያሌ አስከፊ ተግባራት ተከናውነዋል፤ ዛሬ
የምናየው ይህ አንዱ ነው፤ “በዚያም
ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ በሌለበት ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ማዶ የተቀመጠ ሌዋዊ ነበረ፤” (መሳ. 19፥1) ይላል፣ በመሳፍንት
መጽሐፍ ውስጥ ከተቀመጡት የብንያም ሰዎችን የሥነ ምግባር ብልሹነትና በምላጭ ጫፍ ላይ መቆማቸውን ከሚያሳዩት ታሪኮች አንዱን
ለመተረክ ሲነሳ።
በርግጥ ሌዋዊው ካህን ቁባቱን ፍለጋ ከኤፍሬም ወደ ቤተልሔም መሄዱ፣ ከአንድ
ሚስት በላይ ማግባቱን ያሳያል፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ተግባር አልነበረም፤ በተጨማሪም፣ እግዚአብሔር
ለእስራኤል ልጆች መሳፍንትን የሰጠው፣ ርሱ ብቻውን በነርሱ ላይ ሊነግሥ ነበር። ነገር ግን ለጌታ ከመታዘዝ ይልቅ፣ የሃይማኖት
መሪዎቿ ድካምና ኃጢአት እያየለባቸውና እየባሰባቸው ሲሄድ በተደጋጋሚ እንመለከታለን።