Please read in PDF
ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም ሰው
የፈለገውን እምነት የመከተል መብት ከያህዌ ኤሎሂም ተችሮታል፤ የወደደውንም “አምላክ”[እግዚአብሔርንም ኾነ ሰይጣንን] መከተል ይችላል፤
ታድያ ካመለክነው ዋጋችንን መቀበል ሳንዘነጋ!!!! ይህ ጽሁፍ የኢሬቻን
አምልኮአዊ ሥነ ሥርዐት ለሚከተሉና ዋቄፈታን ሃይማኖታቸው ላደረጉ አልተጻፈም፤ ነገር ግን በክርስትና ውስጥ መስገው፣ ኢሬቻንና ዋቄፈታን
ወደ ክርስትና አሹልከው ለማስገባት የሚጥሩትን ሥራቸውን ዕቡይ፤ መንገዳቸውን እኩይ ለማለት የተጻፈ ክርስቲያናዊ የተግሳጽ ጽሁፍ
ነው!
ምክንያተ ጽሑፌ
ሰሞኑን ሚድያውን ከሸፈኑት ነገሮች መካከል አንዱ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
አበውና አንዳንድ “ክርስቲያኖች” [በክርስትና ስም ያሉትን ኹሉ ይመለከታል]፣ “ዕጣን ዕጣንነታቸውን፤ ክርስቶሳዊ ክርስቶሳዊነታቸውን”
ትተው፣ “እሬቻ እሬቻ፤ ዋቄፈታ ዋቄፈታ” መሽተታቸው ነው። እናም ይህ ተግባራቸው እጅግ ቈጥቁጦኛል፣ ለምንስ እንዲህ መኾን አስፈለገው?
ብዬ እንድሞግት አስገድዶኛል። በምን መሥፈርት አንዳንድ አባቶች “የኢሬቻ የክብር ተሸላሚ እንደ ኾኑና፣ ለምን ዓላማስ እንዲህ ሊሸለሙ
እንደ ተፈለገ፣ ኢሬቻ “ባሕላዊ ወሃይማኖታዊ መልክ” ሊይዝ እንዳለው [እንደ ያዘና ዋቄፈታ በሚለው ዐውድ፣ እንደ ክርስትናና እስልምና
ሃይማኖቶች “አምላኩን ጠርቶ” ሲባርክ እያየን ነውና] እየታወቀና እየተሄደበት፣ በግልጽ ሃይማኖታዊ ቀኖናና ዶክትሪን እየተዘጋጀለት
ባለበት በአኹኑ ሰዓት፣ ክርስትናን በተለይም ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መታከክ ለምን አስፈለገ?፣ ከክርስትናና የክርስቶስ
ጌትነትና አዳኝነት፣ ቤዛነትና ብቸኛ ዋጂነት በማይሰበክበት መድረክ ላይ፣ እኒህ አባቶች የስማቸው መጠራት፣ በተጨማሪም ጥቂት የማይባሉ
ክርስቲያኖች በማምለኪያው ሥፍራ[1]
መገኘታቸው አልኮሰኮሳቸው፣ አልከነከናቸው፣ አልቆጠቆጣቸው ይኾንን?” … የሚልና ብዙ የጥያቄ ማዕበሎች ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ምክንያት
ኾኖኛል።