1.8.
ግብረ ሰዶማዊነት
“ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን
ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ …” (ሮሜ 1፥26-27)
“… ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ … የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” (1ቆሮ. 6፥9-10)
ኀጢአትን አዘውትረው ለሚሠሩ ሰዎች ሁሉ
(ክርስቲያኖችን ጭምር) መንፈሳዊ ሞት የሚያገኛቸው መኾኑን ታላቁ መጽሐፍ ደጋግሞ ተናግሯል (ሮሜ 6፥16፤ 8፥13፤ ገላ. 5፥21፤
ኤፌ. 5፥5-6፤ 1ዮሐ.2፥4፤ 3፥9፤ ያዕ. 1፥15)። ኀጢአትን በተመለከተ ምንም መታለል አይገባም፤ ብዙ ሰዎች በክርስቶስ ሞት
ያገኙትን ነጻነት ለራሳቸው የኃጢአት ሥራ በነጻነት ለመፈጸም እንዲያመቻቸው ሲጠቀሙበት እናያለን። ይህንንም በተመለከተ ታላቁ መጽሐፍ፦
“ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ … ” (ገላ. 5፥13) እንዲሁም
“አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ” (1ጴጥ. 2፥16) በማለት
በግልጥ ያለምንም ማወላወል አርነታችንን ኀጢአትን ለመፈጸም እንደ መሸፈኛ ማቅረብ እንደማንችል ያስቀምጣል።