Please read in PDF
2. ተዋጉ፦ በክርስቶስ ኢየሱስ ካመንንበት ቀን ጀምሮ ከክፋት ሁሉ አሠራርና ከዲያብሎስ ጋር ውጊያ ለመግጠም ፊት ለፊት ተፋጥጠናል፡፡ ደጋግመን እንዳነሣነው ውጊያችንም ከሥጋ ለባሽ ፍጡር ጋር ሳይሆን፣ ከጀርባው ለራሱ ክብርና አምልኮን ለመቀበል ከሚሠራው[ወንጌል የጨበጡ አገልጋዮችንም ጭምር በመጠቀም] ከክፉ መንፈሳውያን ሠራዊት አለቃ ከሆነው ከዲያብሎስ ጋር ነው፤ (ኤፌ.6፥12)፡፡ ውጊያውን በተመሳሳይ መንገድ በመቆም እንጂ በግል ማንነታችን ብቻ ማሸነፍ እንደማንችል መጽሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ ነግሮናል፡፡

“በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤
የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት
ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን፤ ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፤” (2ቆሮ.10፥3-5)
እንዲል፣ ሰይጣን የሚሰወርበትንና የሚሰውርበትን የክፋትን ምሽግ፣ የስህተትን ትምህርት፣ ርኩሰትና ኃጢአትን ሁሉ ለማፍረስና ለመደምሰስ
ፍጹም የሆነ ብቃት ያለውና ጠንካራው መሣርያ ከእግዚአብሔር የምናገኘው ጦር ዕቃ ብቻ ነው፡፡