Please read in PDF
ካለፈው
ቀጠለ …
4. ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ስናጠና ልናስተውላቸው የሚገቡ ቃላት
ቃላትን
በትክክል መረዳት ወይም ትክክለኛ ትርጕማቸውን ማወቅ ወደ እውነተኛ ዕውቀት ያደርሳል። በተለይ ደግሞ ትምህርተ ሥላሴን ስናጠና፣
በጥንቃቄ ልናጠናቸው የሚገቡ ቃላት አሉ። እኒህም፦
4.1.
ሥላሴ፦ በአጭር ቃል፣ “ሥላሴ” የሚለው ቃል በአዲስ
ኪዳን መጻሕፍት ምንባባት ውስጥ የለም። ነገር ግን ለቃሉ ሳይኾን ለትምህርቱ ፍጹም ዕውቅናን እንሰጣለን። ምክንያቱም በቅዱሳት
መጻሕፍት ውስጥ የሥላሴ ትምህርትና መገለጥ በስፋት አለና።
“በግእዝ ቋንቋ ቃሉ “ሦስትነት” ማለት ነውና በትምህርተ
መለኮት ጥቅም ላይ ሲውል በአንዱ በእግዚአብሔር ሦስት አካላት እንዳሉ ያሳስባል። በ2ኛው መቶ ዓመት የአንጾኪያ ጳጳስ የነበረው
ቴዎፍሎስ
በግሪክ ቋንቋ “ትሪአስ” እና ተርቱሊያን
በላቲን ቋንቋ “ትርንታስ” (በእንግሊዘኛ TRINITY) ስለ እግዚአብሔር ሲያስተምሩ፥ አካላት ሦስትነትን ለማመልከት
ተጠቀሙባቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምረው የቤተ ክርስቲያን አባቶች በእነዚህ ቃላት እየተጠቀሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለማብራራትና
ለመወሰን ሰፊ ጥረት አደረጉ።”