Monday, 29 December 2014

እኛ ኢትዮጲያውያን በአጼ ቴዎድሮስ እይታ …

      
                                  
                             Please read in PDF                       

       “እኛ ኢትዮጲያውያን” የሚለው ሃሳብ “ደምና አጥንታችንን ገብረንላታል” ለሚሉ አርበኞች ልብ የሚመላ ነገር አለው፤ በጥንት በሕገ ልቡና፣ ቀጥሎም በሕገ ኦሪት ከዚያም በክርስትና መኖሯን ለሚያምኑ ደፍረው የሚሉት ነገር አላቸው ፤ በአክሱምና በዛጉዌ የታነጹትን ሐውልትና ህንጻ አብያተ ክርስቲያናትን ለሚያደንቁ አርክቴክቸሮችና ሌሎች፥ እጃቸውን በአፋቸው ጭነው ብዙ የሚተነትኑት ነገር አላቸው፤ ሁሉም በየሙያውና በያለበት ደረጃ ስለኢትዮጲያችን ቢጠየቅ የሚለው ብዙ ብዙ አለው፡፡
     ሃሳቤ ግን ወዲህ ነው፤ አጼ ቴዎድሮስ በጥር 22 በ1858 ዓ.ም ለእንግሊዛዊቷ ንግሥት ለቪክቶሪያ በኢትዮጲያ ምድር ከታሠሩት የእንግሊዝ እስረኞች ጋር በተያያዘ፤ እንዲሁም ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ሲያስቀምጡ፦  “የኢትዮጲያን ሰዎች ድንቁርነታችነን ዕውርነታችነን ሣይሰሙት አይቀሩም ያማረ መስሎኝ ደፍሬ የላክሁብዎን ከፍቶብኝ (አጥፍቼ እንደሆነ) ቢገኝ ይምከሩኝ እንጂ አይክፉብኝ፡፡ እግዚአብሔር የመረጠዎ ንግሥት ዓይንዎ የበራ ነውና፡፡”(ጳውሎስ ኞኞ ፤ ዐጤ ቴዎድሮስ ፤ ግንቦት 1985 ፤ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት ፤ አዲስ አበባ ፤ ገጽ.214)
    አሁንም በድጋሚ በሚያዝያ 10 ቀን 1858 ዓ.ም ለዚህችው ንግሥት ድጋሚ በጻፉት ድብዳቤ እኛን ኢትዮጲያውያንን እንዲህ ገልጠዋል፦ “ የኢትዮጲያ ሰዎች እውር ነንና ዓይናችነን ያብሩልነ፡፡ እግዚአብሔር በሰማይ ያብራልዎ፡፡” በማለትም በግልጥ አስቀምጠዋል፡፡ (ጳውሎስ ኞኞ ፤ ዐጤ ቴዎድሮስ ፤ ግንቦት 1985 ፤ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት ፤ አዲስ አበባ፤ ገጽ 233)

Tuesday, 23 December 2014

የትኩረት ጩኸት ትኩረትን ሲያደበዝዝ


                                  Please read in PDF              

     በአገራችን ትኩረትን የሚስበው ድርጊት እንጂ ዝግጅት አይደለም፤ አንድ ከባድና ዘግናኝ ድርጊት ሲፈጸም ብዙ ጊዜ ስሜቶቻችን ተጋግሎ መንጫጫት፤ ድርጊቱ እንዳይፈጸም ቀድመን ከመሥራት ይልቅ ከድርጊቱ በኋላ በጣም መጯጯህ ፣ ሰላማዊ ሰልፎች ፣ ብዙ ስብሰባዎች ፣ የአቋም መግለጫዎችና የስሜት ዕርምጃዎችም ይወሰዳሉ፡፡  ማሳያዎችን በምሳሌ ብናነሳ፦ በባለፈው ወር የአዋሽ ፓርክን በሚያቋርጠው ትልቁ የምሥራቅ ኢትዮጲያ መንገድ በጉዞ ላይ ሳለ በአንድ ቅጥቅጥ አይሱዙ ላይ በደረሰው አደጋ ከሐያ ሰባት ሰዎች በላይ የሞት አደጋ መድረሱን ሰምተን ሳናባራ፤ ወዲያውኑ በተወሰደው እርምጃ መንገዶች ላይ በተደረገው (በዋናው አስፓልት ላይ መኪናዎች በጉዟቸው እንዲያቀዘቅዙ ለማድረግ በተደረገው ሌላ የአስፓልት ጉማጅ ሥራ) በተወሰደው የስሜት ዕርምጃ ሌሎች የመኪና አደጋዎች መከሰታቸውን ከቦታው ሄዶ ማስተዋል ይቻላል፡፡
    አሁንም ሌላ ማሳያ ብናነሳ ፦ በባለፈው ወር ከተከሰተው ጆሮን ጭው ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ የእህት ሐና ላላንጎ ጉዳይ  ነው፡፡ ድርጊቱ ከዳር እስከዳር ብዙ በጣም ብዙ አነጋግሯል፡፡ ከወረዳ እስከ ሚኒስቴር ቢሮ ፤ ከሆስፒታል እስከ የፖሊስ መምሪያና ጣቢያዎች ፤ ከመንገድ ዳር “ታዛቢ” እስከመኪና አሽከርካሪዎች በዚህ ሂደት ውስጥ ያሉበትን ልልነትና ግድ የለሽነት በሚገባ አጢነናል፡፡ ጥቂት ስህተት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል አይተናል፡፡ የፖሊስ ዳተኝት ፣ የሆስፒታሎቻችን ከልክ ያለፈ ቸለተኝነት ድርጊቱን ከፈጸሙት የማይተናነስ መሆኑን ሌላ ምስክር ሳያሻ የአደባባይ ገመና ሆኗል፡፡

Thursday, 18 December 2014

በመሠወሬ ነው!


                     Please read in PDF

ሺህ ሰልፍ ከፊቴ ፥ ትዕልፊት ከኋላ፤
እንደጉንዳን ፈልቶ ፥ እንዳʻንበሳ ቢያጓራ፤

Monday, 15 December 2014

የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አገልጋዮች(የመጨረሻ ክፍል)



4. አገልግሎቱን ለእግዚአብሔር ለቃሉ አደራ መስጠትን ያውቃል (ቁ.32)

                  “ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ
                  ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።” (2ጢሞ.2፥1)

   አገልጋዮች የእግዚአብሔርን መንጋ የምንጠብቅ ሲመስለን እንስታለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች (ጳጳሳት) “እናንተን ራሳችሁን … ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋችሁ” ሲላቸው እናያለን፡፡ የእግዚአብሔር መንጋ የሚጠፋው ወይም የሚጎዳው ከእግዚአብሔር በኃጢአቱ ሲለይ ወይም እግዚአብሔር ንስሐ ባለመግባቱ በኃጢአቱ ምክንያት ሲለየው  ነው፡፡ ያ እንዳይሆን መሪዎቹ ሕዝቡን ትክክለኛው የጸጋውን ቃል ወንጌል በማስተማር ሊመሩት ይገባል፡፡ በትክክል ሳይነግሩትና ሳያስተምሩት ሲቀር ግን ይጎዱታል ማለትም የመንግሥተ ሰማያት በር ይዘጉበታል፡፡
      ቅዱስ ጳውሎስ እርሱ ቀድሞ ወንጌልን ለመስበክ አደራ ከክርስቶስ ኢየሱስ እንደተቀበለ እንዲሁ፤ (ሐዋ.9፥1-16 ፤ 26፥16 ፤ 1ቆሮ.9፥17) አሁን ደግሞ እርሱ ለታመኑት ሲሰጥና የታመኑትም ለሌሎች ለታመኑ አደራ እንዲሠጡ ሲተጋ እናየዋለን፡፡ ወንጌል መስበክ አደራ ከሆነ አደራው ኃላፊነት ያለበት አደራ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ወንጌልን ኃላፊነት ተሰምቷቸው ከፍቅር በተነሳ ውዴታ እንጂ በምርጫ እንዲያገለግሉ አልተጠሩም፡፡

Tuesday, 9 December 2014

የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አገልጋዮች(ክፍል - አራት)




2. ለመንጋው ሁሉና ለራሱ ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡(ቁ.28)

    ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ጢሞቴዎስን “ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።” በማለት ይመክረዋል፡፡ በእርግጥ የሚያድን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ አማኞች ወደጌታ በመምጣት ሕይወታቸው  ዕለት ዕለት በማደግ እግዚአብሔርን ወደመምሰል እንዲደርሱ አገልጋዮች ትልቁን ድርሻ አላቸውና፥ ለራሳቸውም፤ ለትምህርታቸውም ሊጠነቀቁ ይገባቸዋል፡፡ ጤናማውን ጉዞ እስከፍጻሜው ልንጓዝ የምንችለው ለትምህርታችንና ለምናስተምረው የእግዚአብሔር መንጋ መጠንቀቅ ስንችል ነው፡፡
    ጥቂት እርሾ ብዙውን ሊጥ እንደሚያቦካ (1ቆሮ.5፥16)፤ ጥቂት የተባለም ኃጢአት ወይም ክፉ ትምህርት ብዙውን መንጋ ከመበከል አይመለስም፡፡ እንደዋዛ የሚደረጉና የሚነገሩ ነገሮች በመንጋው ላይ ሊያሳርፉ የሚችሉት ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ ትላንት እንደዋዛ ሲነገሩ የነበሩ ተረታ ተረቶች፥ ዛሬ ወደቤተ ክርስቲያን ሾልከው ገብተው ለብዙ ምዕመናን የሕይወት መመሪያ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁንም ለመንጋው ባለመራራት የሚጻፉትና የሚሰበኩት ስብከቶች በቃሉ ሚዛንነት ልንፈትሻቸው፤ ቀለው ከተገኙ ልናስወግዳቸው ይገባናል፡፡

Tuesday, 2 December 2014

የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አገልጋዮች(ክፍል - ሦስት)



5. የሚነሱት ከመካከላችን ነው፡፡
     እውነተኛውና ለእግዚአብሔር የጨከነ አገልጋይ ሲጠፋ ክፉው አገልጋይ ከውጪ ወደውስጥ ወይም በብዛት ከመንጋው መካከል ይነሳል፡፡ ከመካከል የሚነሱ የሐሰት መምህራን በዋናነት የመሳታቸውና የማሳታቸው ምክንያት ከመሠረተ እምነት ትምህርት ጉድለት ነው፡፡ ገበሬ እርሻውን አለስልሶ ከዘራ በኋላ በየጊዜው መከታተል ይገባዋል፡፡ የሚከታተለው አለስልሶ የዘራው እርሻ የማይበቃ ሆኖ ሳይሆን አረምና እንክርዳድ ዋናውን ዘር እንዳይውጠው ነው፡፡ አረምና እንክርዳድ ገበሬው የዘራው አይደልም፤ እርሱ ያልዘራው ከመካከል የበቀለው አረም ግን የዘራውና ዋና ዘር ሊያጠፋው ይችላል፡፡ ስለዚህ በየጊዜው  ሊያርም ፤ ሊኰተኩተው ይገባዋል፡፡ በመንፈሳዊ አለም ደግሞ መልካሙ ገበሬ እግዚአብሔር ዘርን ከዘራ በኋላ መጥቶ ክፉን ዘር የሚዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ (ማቴ.13፥28) ስለዚህ ልንተጋ ቃሉን በማጥናት ልንበረታ ይገባናል፡፡