Monday, 30 June 2014

የጠፋው ልጅ ወንድሞች(ሉቃ.15፥28)


ከሌሎች ወንጌላት ይልቅ ጠፍቶ ስለመገኘት ሉቃስ ብዙ ምሳሌዎችን ይሰጠናል፡፡“ጠፍቶ የተገኘው” ህጻኑ ኢየሱስ(ሉቃ.2፥46)፣ ጠፍቶ የተገኘው በግና ድሪም (ሉቃ.15፥3-11) ሉቃስ የዘገባቸው እውነትና ምሳሌዎች ናቸው፡፡በእርግጥ በኃጢአት ጠፍቶ ለበጎነት እንደመገኘት ያለ ፍጹም ሰማያዊ ደስታ የለም፡፡(ሉቃ.15፥10)
     የጠፋው ልጅ የአባቱን ሀብት ለመካፈል ሲነሳ ወደአባቱ ቤት ለመመለስ ፈጽሞ ያሰበ አይመስልም፡፡ከአባቱ ቁጥጥር ውጪ በመሆን ያሻውንና የወደደውን ሊያደርግ በመፈለግ ወጥቶ የሄደ ነው፡፡“ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ የሄደው ወደሩቅ ሀገር ነው፡፡”(ሉቃ.15፥13) በሄደበት ሀገር ግን ሀብቱን በተነ፡፡ እንዳይመለስም እጅግ ርቆ ሄደ፡፡ የኃጥዕ መንገድ ከእግዚአብሔር የተለየ ነውና ሩቅ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር የተለየው አዳም መልካም በሚመስለው መንገድ ሲጓዝ ፤በገነት እያለ ከእግዚአብሔር ሩቅ ነበር፡፡(ዘፍ.3፥6) በተመሳሳይ መንገድ ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት ወደተርሴስ የሄደው ዋጋ ከፍሎ፤ከስሮ ፤ርቆም ነው፡፡(ዮና.1፥3)
     የጠፋው ልጅ ከመራቁ ባሻገር በረሃብ ምክንያት የሚጨነቅም ሆነ፡፡ የረሃቡን ጭንቀት ለማስታገስ “ … ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች ከአንዱ ጋር ተዳበለ፥ እርሱም እሪያ ሊያሰማራ ወደ ሜዳ ሰደደው።እሪያዎችም ከሚበሉት አሰር ሊጠግብ ይመኝ ነበር፥ የሚሰጠውም አልነበረም።”(ሉቃ.15፥15) ይላል፡፡ የጠፋው ልጅ የእሪያ እረኛ በመሆን ያደረገው ይህ ድርጊት በአይሁድ ልማድና  በኦሪት ህግ እጅግ ርኩሰት ነው፡፡(ዘሌ.11፥7) ይህ ብቻ አይደለም ለእንሰሳት የሚሰጠውን የእህል ገለባ (አሰር) ሊበላ እየተመኘ እንኳ ሊያገኝ ያልቻለ ነበር፡፡

Thursday, 26 June 2014

ሰቀሉህ ብዬማ እኔስ አላነባ!

Please read in PDF:- sekeluh byema enes alaneba!

ስለአይሁድ ጅራፍ፤ ችንካርና እንግልት፣
ስለ አክሊለ እሾሁ ሚስማርና ቁስለት፣
ጎንህ በጦር  ስለት ስለመወጋቱ፣
በጠቆረ ህሊና በዘንግ መቀጥቀጡ፣
ለሞት ለመቃብር ይህ አላበቃህም፣
ባለብዙ ምህረት ኢየሱስ መድህን፡፡

     የግፍ ግፋታቸው በጥላቻ ገፍቶህ፣
     የአመጻ ፍትህ አሽቀንጥሮ ደፍቶህ፣
     በማይራራ መዳፍ ከግንድ እያማቱ ፣
     በደል ሳያገኙ ባ’ድማ እየተንጫጩ፣
     አቁመው ዕርቃንህን የኋሊት ጠፍረው፣
     ስላሉህ አይደለም ስቀለው! ስቀለው!
     የ’ኔን ሞት ጌታዬ አንተ ለ’ኔ የሞትከው፡፡

Friday, 20 June 2014

“ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ”(ማቴ.23፥8) – (የመጨረሻ ክፍል)


            
    
            
   ፈሪሳውያን  ወንድማዊ መሪነትን ወደ አስፈሪ አለቃነት ለውጠውታል፡፡እኛንም እንደወንድም አለመተያየትና አለመዋደዳችን የጎዳን ብቻ አይደለም፤ ብዙዎችን ያሰናከልንበትም ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ጥቂት የማይባሉ በአሜሪካ፣በአውሮፓ፣በካናዳና በሌሎችም የስደት ምድር ላይ ያሉት “አማኝ ተብለው” በጽዋና በጉባኤያት የሚሰባሰቡት በብሔር ተኮር ስብስብ፤ ያውም ከኦሮሞ ወለጋና አርሲ፣ከአማራ ጎንደርና ጎጃም፤ከደቡብ ወላይታና ሲዳማ … በሚል ተከፋፍለው “በቤተ ክርስቲያን” ሲሰበሰቡ ማየት የሚያመውን ያህል ምንም ህመም፤ከባድ ስቃይም የለም፡፡ እዚህ አይናችን ሥርም ያለው የሀገር ቤቱ የሚብስ እንጂ የሚሻል ነገር የለውም፡፡በብዛት የአንድ ሀገረ ስብከትን ሥራ አስኪያጅ ወይም ጳጳስ ዘርና ወንዝ ቆጥረው የሚሰባሰቡትን የቄስና የዲያቆን መንጋ ማየት እንግዳ አይደለም፡፡ሥር የሰደደው የዘረኝነታችን ዘር የእግዚአብሔር ነፍስ አብዝታ የምትጠየፈውን በወንድማማች መካከል ጠብ መዝራትን እንኳ ረስተነዋል፡፡(ምሳ.6፥19)
    አገልጋይ ግን እንዲህ ያለውን ነገር ሊያጠራ፤ እንደወንድም በቅርብ ሊመራ እንጂ አለቃ ሆኖ ሊያዝ አልተጠራም፡፡ ስለዚህ ፈሪሳውያን አለልክ ክብርን ሽተዋልና ፍፁም ወቀሳቸው፡፡ አለመታደል ሆኖ እንጂ አለቅነት ከወንድምነት አይበልጥም፡፡ ወደሌላ ከምትተላለፍ ህልቅናና ሹመት ይልቅ ለዘለዓለም አብሮን  የሚኖረው ወንድምነት ትልቅ ክብር አለው፡፡
    ወንድም ገመና ሸፋኝ ነው፤ ወንድም የገዛ ወንድሙን ገመና ለማይራራ ባዕድ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ወንድማማችነት በደም ተሳስሯልና እስከመከዳዳት በሚያደርስ ክፋት አይያዝም፡፡ አዕምሮው ካልጎደለው በቀር ወንድም ወንድሙን “ወንድሜ አይደለህም” ብሎ ለመካድ አቅም አይኖረውም፡፡ወንድምነትን የሚክድ እርሱ ነው እንጂ ከዳተኛ ፤ወንድምነቱ ፈጽሞ የሚሻር አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ወንድማችነትን ክደን ስንነካከስ፣ስንበላላ፣ስንጠፋፋ … ዓለም እንኳ ታዝባናለች፤  የስድብ ምክንያትም ሆነናል፡፡ መንፈሳዊነቱ ብቻ ሳይሆን የሀገራችንን ተጨባጭ የመሪዎችና የህዝቡን ቅርርቦሽ ስናይም እጅግ የመረረ ነው፤ዛሬም መሪ የሚባሉቱ በወንድምነት መንፈስ ህዝብን ማገልገል የሚቀፋቸውን ያህል ሌላ ነገር የሚቀፋቸው ያለ አይመስለኝም፡፡
     ለምን እንደሆን ለራሴ ግራ ይገባኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ከሚያገለግሉኝ ወንድሞቼ መካከል ብዙዎቹ ትህትና የሚጎድላቸው ብቻ አይደሉም፤ እንደወንድም የማያቀርቡም ናቸው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ሲነገራቸው እንኳ ለመስማት ዝግጁ አለመሆናቸው ነው፡፡ … ግን ከሁሉ በላይ በአማኑኤል የተዛመድን ወንድማማቾች ከደም ይልቅ በህያውና ለዘላለም በሚኖር፤ ከማይጠፋው ዘር በመወለድ አንድ የሆንን ነን፡፡እንኪያስ ከሥጋ ወንድምነት በሚልቅ የወንድማማች ፍቅር ልንዋደድ፣ልንከባበር፣ገመና ልንሸፋፈን፣ ሳንሸነጋገል በምክር ቃል በግልጥ ልንነጋገር፣ልንተያይ … በእውነት ይገባናል፡፡

Monday, 16 June 2014

“ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ”(ማቴ.23፥8)(ክፍል አንድ)

    Please read in PDF :- hulachihu wendmamach nachihu 1

 “ወንድም” የሚለው ቃል በቀጥታ ትርጉም ከአንድ እናትና አባት የተወለዱ ተወላጆችን የሚያመለክት ሲሆን በታላቁ መጽሐፍ ግን ከተወላጅ ባሻገር ለሌሎች ወገኖችም በተለያየ ጊዜ ተሰጥቶ ሥራ ላይ ሲውል እናገኛለን፡፡  ጥቂቱን ብንመለከት፦
ሀ. በሀገር ተወላጅነት
    የአንድ ሐገር ተወላጆች ብቻ በመሆን ወንድም መባባል እንደሚቻል መፅሐፍ ቅዱስ ሙሴንና  የእስራኤልን ልጆች በመጥቀስ እንዲህ ይላል፦ “በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወደወንድሞቹ ወጣ፤ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፥ የግብፅም  ሰው የወንድሞቹን የዕብራውያንን ሰው ሲመታ አየ” (ዘፀ.2፥11 ፤ ሐዋ.7፥23-26)፡፡ በእርግጥም ሙሴ ለሀገሩ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ፍፁም ታላቅ ወንድም(ወንድም ጋሼ) ነበር፡፡
ለ.  ከጥብቅ ወዳጅነት የተነሣ
     ግብረ ሰዶማውያን በክፉ የተሰጡለትን የኃጢአት እሾህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል እጅ ጠምዝዘው ከሚተረጉሙት ታሪክ አንዱ የዳዊትንና የዮናታንን የጠበቀ ወንድማዊ ፍቅርን በመጥቀስ ነው፡፡ ዳዊትና ዮናታን ወዳጅነታቸው እንደወንድም የነበረ መሆኑን ፥ዳዊት ዮናታን በተገደለ ጊዜ በእንባ ቃል በአንደበቱ እንዲህ አለ፦ “ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለአንተ እጨነቃለሁ፤ በእኔ ዘንድ ውድህ እጅግ የተለየ  ነበር፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም ነበር ፡፡ (2ሳሙ.1፥26-27 )

Wednesday, 11 June 2014

የኢየሱስ ዝቅታ …

Please read in PDF :- yeEyesus zikta

ሐማዊ ከፍታ …
ሰማይ ሰማይ ሰማይ - አርጤክስስ ዙፋን ሥር፤
ከዚያ ዝቅ ሲሉ - ሌላ ሥፍራ የለም - ከመቃብር በቀር፡፡
     የኢየሱስ ዝቅታ …

Friday, 6 June 2014

መንፈስ ቅዱስ ግን ለምን ነው የተረሳው?

   Please read in PDF:- Menfes kidus gn lemn teresa? 
 የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ በጻድቃን በሰማዕታት፣በመላዕክት፣ በሥላሴ፣ በኢየሱስ፣ በአብ … ሥም “በመታሰቢያነት” የተሰሩ የገጠር አጥቢያ፣ አድባራት፣ ገዳማትና ካቴደራሎች አሏት፡፡ ከእነዚህ እልፍ ሺህ “አብያተ ክርስቲያናት” መካከል የመንፈስ ቅዱስን “መታሰቢያ ህንጻ” ማግኘት በምድረ በዳ መልካም ጥላ የመፈለግ ያህል እጅግ ይከብዳል፡፡ለምን ይሆን? … (በእርግጥ የመንፈስ ቅዱስ አማናዊ ማደርያ ቅዱሱ በጌታ ቤዛነት ያመነ አማኝ ሰውነት ቢሆንም! (1ቆሮ.3፥16፤ሮሜ.8፥9) የንጽጽሩም አላማ ስለመንፈስ ቅዱስ ያለንን ግንዛቤ አናሳነት ለመታዘብ እንጂ ድካምን ለማጉላት ከማሰብ አይደለም፡፡)

Monday, 2 June 2014

እንዲሁ ይመጣል!

Please read in PDF :- Indihu yimetal!
ለምን ነው ‘ምታዩት እንዲህ አንጋጣቹ’፤
ወደሰማይ ፋና አይና‘ቹን ልካቹ’፤
በነፍስ ትካዜ በመንፈስ ታክታ’ቹ … ? ፤
ሳይረቅ እየራቀ ሲሄድ የምታዩት፤

Monday, 26 May 2014

የትንሣኤው ምስክሮች

    የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ሙስና መቃብርን አጥፍቶ መነሣት የክርስትና መሠረት የቆመበት ጽኑ ዐለት ነው፡፡ አሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ደም በጸጋ ድነናል፤ ወደፊት ደግሞ ፍጹም እንድናለን፤ (ኤፌ.2፥8) ብለን ደፍረንና ጨክነን ጮኸን የምንናገረውና ቤተ ክርስቲያንም አሰምታ የምትሰብከው እርሱ ዝጉን መቃብር ሳይከፍት፤ የታተመው ድንጋይ ሕትመቱ ሳይፈታ፤ ሞትን ድል አድርጎ ከሙታን መካከል ስለተነሣ ነው፡፡
     የጌታ ትንሣኤ የስብከቶች ሁሉ ዋናውና የመጀመርያው፤ ትልቁም ርዕስ ነው፡፡ አንድ ሰባኪ የእግዚአብሔርን ቃል ሊናገር በወጣበት አውደ ምሕረት ላይ “ብዙ ቃል” ሰብኮ የጌታን ትንሳኤ ሳይናገር ቢወርድ፤ በእውነት! እውነተኛ ሰባኪ መሆኑ ያጠራጥራል፡፡ ምንም እንኳ ጥቂት እንከኖች ቢኖርባትም ያቺ በተራራ ላይ የተሠራችውና ታበራ የነበረችው የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን በአስቆሮቱ ይሁዳ ፈንታ ሌላ ሐዋርያ ሊመርጡ ባሉ ጊዜ ያስቀመጡት የመጀመርያው መስፈርት “ … ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል”(ሐዋ.1፥22) የሚል ነው፡፡
    ደቀ መዛሙርቱ ያልተደራደሩበት እውነት “ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር” የሚሆን ብቻ እርሱ እውነተኛ የጌታ ሐዋርያ ነው ብለው ማመናቸው ነው፡፡ ጌታ ከሙታን መካከል መነሣቱን የሚያምኑና የሚያውቁ ብዙ ሰዎች በዚያን ጊዜ ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ የተፈለገው፤ ጌታ “እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ ”(ሮሜ.1፥4) መሆኑን ሳይፈራ ሳያፍር በአደባባይ የሚመሰክር ሐዋርያ ነው፡፡

Wednesday, 21 May 2014

“Innoo ka’eera,asi hinjiru.” (Mat.16:6)

Please read in PDF

Goftaan IYesus Kirstos irra-daddarbaa fi cubbuu ilmaan namaa baadhachuudhaan fannoo irratti fannifameera. kanas barreesitootni wangeelaa sagalee tokkon mirkaneesaniru. (Mat.27:35,Mar.15:25,Luq.23:33,Yoh.19:18).duu’a fi dhiignii Goftaa IYesuus biyya lafa tanaafi ilmaan namaa hundaaf baayyee barbaachisaa dha. Sababn isaas dhiiga osoo hindhangalaasin dhiifamuun cubbuu waan hinjirref.(Ibr.9:22)
     Ilmaan namaa bittaa cubbuufi waanjoo seexanaa jalaa gaarummaa fi hojii isaaniitiin bilisa ba’u hindandeenye. qajeelummaatti fi hojiin gaariin keenya sababii cubbuu irra kan ka’een akka huccuu abaarsaatti ta’e (Isa.64:6) nuti  hundinuu karaa Waaqayyoorraa gorree ture. (Rom.3:12) kanaaf cubbuu nama tokko irraa kan ka’een gara biyya lafaa hundatti duuti dhufee. akkasumaas namootni waan yakkaniif du’i sanyii namaa hundaa walga’era.(Rom.5:12)
   Biyyii lafaa hundii abdii dhabee, du’a fi dukkanaan marfamee, seexanni bittaasaa yeroo babbal’ifatee jirutti, namni aarsaa hoolaa fi jibbichaa dhiyeesuus  gatii lubbuusaa wajjin waan walhinmadaaleef … baraarsa cubbuu fi nageenya sammuu waan argachuu hindandeenyeef Waaqayyoon ilmowwasaa hunda akkanumatti  waan nu jaalateef nu kenneera.(Yoh.3:16)

Monday, 19 May 2014

አንደኛው መስቀል

Please Read in PDF
በህይወት የማይስማሙ በሞት ይጣመራሉ፡፡በክርስቶስ የሚካካዱ ለሰይጣን ሊገዙ በአንድ ያብራሉ፡፡በምድረ በዳ ሰው ለመግደል ፣የሰው ንብረት ለመዝረፍ የሚስማሙ ቀራንዮ ላይ መለያየት ይጀምራሉ፡፡በወንበዴነት ሚስማሙ የክርስቶስ በመባል ግን ይለያያሉ፡፡በኃጢአት የሚጣበቁ በጽድቅ ይነጣጠላሉ፡፡አይለያዩም የተባሉ የኃጢአት ባልንጀሮች ክርስቶስን በማመንና ባለማመን  እስከማይተዋወቁ ድረስ ይከፋፋሉ፡፡
       ቀራንዮ ድካማችን አይጸድቅባትም፡፡ድካማችንን በመስቀሉ ጠርቀን፤ ክፉ ምኞት አንቂ አሮጌውን ሰው ሰቅለን አዲሱን ሰው የምንለብስባት፤ ለአንዱ ጌታ መገዛታችንን በግልጥ ውሳኔያችንን የምንገልጥባት ስፍራ ናት፡፡ቀራንዮ ላይ ብዙ አማራጮች ብዙ መንገዶች የሉም፡፡ብዙ የመዳን ቀመሮች ፣ከሁለት የዘለሉ የድህነት ስሌቶችም የሉም፡፡ቀራንዮ ላይ ሁለት መንገዶች ብቻ አሉ፡፡አንዱ የሲዖል አንዱ ወደእግዚአብሔር ገነት፡፡ሦስተኛ ምርጫ የለም፡፡ብንፈልግም ፈጽሞ ማግኘት አይሆንልንም፡፡
        አንደኛው መስቀል ላይ ዘመኑን በውንብድና የጨረሰ፣ለክፋቱ ዳርቻ ሳያበጅ ከነክፋቱ የተገኘ ለጥፋቱም ተካካይ ፍርድ በህጉ የተሰጠው አንድ ደካማ ሰው አለ፡፡አለም ሞት ብትፈርድበትም ክርስቶስ ግን ዛሬም የርህራሔ እጁን ዘርግቶ እስከማታ "ልጄ ሆይ አትሙትብኝ እኔ ልሙትልህ!!!" እያለ ይለምነዋል፡፡ ከእግዚአብሔር መዝገብ ፍርድ እስካልወጣ አለም ሞት ፈርዳ ለፍርዱ መፈጸም ብትቻኮልም የህይወት ጥላችንን ማንም አያጥፈውም፡፡አለም ሞት ብትደግስም ክርስቶስ ግን የማይደክም የማዳን እጅ ዘርግቶለታል፡፡

Sunday, 11 May 2014

ደቀ መዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ለምን ተጠራጠሩ?(የመጨረሻ ክፍል)


3.    መጠራጠር ፦ ደቀ መዛሙርቱ ነገረ ትንሳኤውን ሲሰሙ የተነገራቸው “ … ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑም፡፡”(ሉቃ.24፥11) ደቀ መዛሙርት አርብ ዕለት በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን መከራ አይተነዋል፡፡ስለዚህ ሁሉም “ተሰብስበው … አይሁድን ስለፈሩ ደጅ ዘግተው … ” በፍርሐት ቆፈን ውስጥ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ (ዮሐ.20፥19) እግዚአብሔርን የማይፈራ ፍርሃት ጥበብ የጎደለው ፍርሃት ነው፡፡እግዚአብሔርን እስከመካድ ያደርሳልና፡፡
   ጴጥሮስ “አንተ ክርስቶስ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ”(ማቴ.16፥16) ብሎ የመሰከረለትን ጌታ ከሥጋዊ ፍርሃት የተነሳ በአንዲት “ነጻነት በሌላት”ሴት ፊት በተጠየቀ ጊዜ “የምትይውን … ሰውየውን አላውቀውም” ብሎ ካደ፡፡(ማቴ.26፥70፤72) “መለኮታችን” መለኮትን ፤ፍርሃታችን እግዚአብሔርን መፍራት ካልቻለ ፍርሃታችን የራሱን መለኮት ፈጥሮ መካዳችን የማይቀር ነው፡፡ጌዴዎን የመፍራቱና የመጠራጠሩ ምንጭ የምድያማውያን ጥቃትና እግዚአብሔርም እንደተዋቸውና እንደጣላቸው ማሰቡ ነበር፡፡(መሳ.6፥11-13) 
     አይሁድ ሁሉንም ሰው በክርስቶስ ሞት እንዲተባበር ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉት ወይም እንዲገድሉት ህዝቡን እጅግ አባብለዋል፡፡ስለዚህም ሁሉም ይሰቀል እያሉ ጩኸት አብዝተዋል፡፡(ማቴ.27፥20፤23) ይህም በራሱ ለደቀ መዛሙርቱ ከባድ የፍርሃትና የጥርጥር ምንጭ ነው፡፡ አለሙ የተስማማበት ብዙዎች የተከተሉት ውሸት በእርግጥ ለዘመናት ብዙዎችን በጥርጣሬ መንፈስ ወደኋላ ስቧል፡፡ ዛሬም ወንጌልን በድፍረት እንዳንመሰክር የሚያደርገንና የፍርሃታችን አንዱ ዋናው ምንጭ ስህተት የሆነውን ነገር የተቀበለው ህዝብና ወገን በፍጥራዊው አይናችን ፊት በዝቶ ስለታየንና ትልቁን የጌታ ክንድ መዘንጋታችን ወይም መጠራጠራችን ነው፡፡ በመጠራጠር ወደኋላ መመለስ ደግሞ ውጤቱ ካለማመን ይበልጥ ሊከፋ ይችላል፡፡ስለዚህም “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና”(2ጢሞ.1፥7) በመንፈስ አካለ መጠን ልንጎለምስ ይገባል፡፡

Tuesday, 6 May 2014

ደቀ መዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ለምን ተጠራጠሩ? (ክፍል - 2)

     ደቀ መዛሙርቱ የተወራውን ወሬ በማመናቸው ሲጠራጠሩ ታይተዋል፡፡የመግደሎሟ ሴት “ጌታዬን ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም … አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ”(ዮሐ.20፥13-16) ማለቷ መሰረቁንና መወሰዱን ያመነች ይመስላል፡፡ጌታ ስለዚህ አለማመኗ “አትንኪኝ” በማለት ወቅሷታል፡፡ማርያም መግደላዊት ቀድሞ የት እንዳኖሩት ወይም እንደቀበሩት ቆማ ተመልክታ ነበር ግና ከመነሳቱ መሰረቁን ተቀበለች፡፡(ማር.15፥47)፡፡የጠላት ወሬ ምን ያህል ልብ እንደሚለውጥ አስቡ! ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ እነሳለሁ ያላቸውን ጌታ ረስተው፤ ቃሉን ዘንግተው ግን የተወራውን አብልጠው ተቀበሉ፡፡ደቀ መዛሙርቱ ከወንጌሉ ይልቅ ለጊዜውም ቢሆን የጠላትን ወሬ ማመናቸው እጅግ ይደንቃል!
   በእርግጥም የዛሬ ዘመን እልፍ አገልጋዮችና አማኞች የሚፈሩት ነገር ከሌላ ወገን የሚወራን ወሬ ነው፡፡ከሁሉ ይልቅ በተለይ ብዙዎች አገልጋይና አማኞች በኢየሱስና በስሙ መታማት አንፈልግም፡፡ምክንያቱም ስሙን ከደጋገምን አንድ ከባድ የሚለጠፍብን ታርጋ አለ፡፡“ጴንጤ ፣ተሐድሶ፣ጸረ ማርያም፣ጸረ ቅዱሳን፣መናፍቅ … ”የሚሉና ሌሎችም፡፡ ብዙ ጊዜ የክርስቶስ ስሙን ለሆዳቸው የሚቸረችሩ አገልጋይና አማኞችን በማየቴ ብዙም አልደነቅም፡፡ነገር ግን ለእውነት ሳንቆም በገና ለገና የሰው ወሬ የምንፈራ ከሆንን እውነተኛ ምስክር መሆናችን አይገለጥም፡፡
   ወሬው በጊዜው ቀላል አይደለም፡፡ማቴዎስ ወንጌሉን ይጽፍ በነበረበት ዘመን እንኳ ተሰርቋል የሚለው ወሬ በአይሁድ ዘንድ በጣም ይወራ ነበር፡፡(ማቴ.28፥15) አዎ! ታርጋ ከተለጠፈብን በኋላ ስለምንናገረው እውነት ሰሚ ማግኘት በጣም ከባድ ነው፡፡ለልባችን ቅርብ የነበሩቱ እንኳ በወሬው ብቻ በጠላትነት ጎራ ሊሰለፉብን ፣የማያውቁን አይናቸውን ጨፍነውና በጨው አጥበው ስማችንን ጥላሸት ሲቀቡት ተለምዶ፣ተዋህዶ፣ሥርዓት ሆኖ ይኸው እያየን ነውና በእርግጥም ያማል፡፡
     በተለይ መገናኛ ብዙሃን ለእውነት ሳይቆሙና ሳይቀኑ በእንቶፈንቶ ቋታቸውን ሲሞሉ ለሀገርና ለወገን የሚረባውን ትተው ተራ ወሬና ያልተባለን እየቀጣጠሉ ሲያወሩና እንደመቃኞ በሬ ሰዎችን ሲነዱ ማየት የበለጠ ልብ ይሰብራል፡፡ ብናስተውል ፖለቲካችን ያልተፈወሰው፣ስብከታችን የጠነዛው፣ክህነታችን የገረጀፈው፣ድቁናችን የነቀዘው፣ ቅስናችን የተናቀው፣ጵጵስናችን የተነቀፈው፣ ንግግራችን የተጠላው … ወሬን ማለፍ ስላልቻለና ከተግባራችን ጋር ፍጹም ዝምድና ስለሌለው ነው፡፡

Wednesday, 30 April 2014

መስቀል ላይ ያላችሁ!

Read in PDF: Meskel Lay yalacheu

 ሥቁል ነኝ ለዓለም የማልረባ ባዶ
እርሷም በእኔ ፊት ፍሬ የሌላት ነዶ
የዓለምን አምሮት ቋቅ እንትፍ አድርጌ
በሞት ኢየሱስን ደግሞም በመቃብሬ
አንድ ሆኛለሁ ሎሌው በእርሱ በዝቶ ክብሬ፡፡

Sunday, 27 April 2014

ደቀ መዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ለምን ተጠራጠሩ?(ክፍል - 1)

    “ትንሳኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሳማ፤ክርስቶስም ካልተነሳ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ከንቱ ናት፤ደግሞም ክርስቶስን አስነስቶታል ብለን በእግዚአብሔር ላይ ስለመሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል … ፡፡”(1ቆሮ.15፥13-16)
   “የክርስቲያን የሃይማኖት ትምህርት መነሻና መድረሻ፣በሞትና በትንሳኤ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው ቢባል ከእውነት የራቀ አይሆንም፡፡” (አበራ በቀለ(ሊቀ ጉባኤ አባ)፡፡(1996)፡፡ትምህርተ ሃይማኖት እና ክርስቲያናዊ ህይወት፡፡አዲስ አበባ፡፡ንግድ ማተሚያ ድርጅት(ማህበረ ቅዱሳን)፡፡ገጽ.209)

   “የክርስቶስ ትንሳኤ ለክርስቶስ አምላክና ለክርስቲያናዊ ትምህርታችን እውነተኛነት ከፍተኛ ምስክር ነው፤ምክንያቱም ክርስቶስ ሲገረፍ፤ሲዋረድ፤ሲሰቀል እንደዕሩቅ ብእሲ ተቆጥሮ ነበር፤ደካማም መስሎ ተገምቶ ነበርና፤ በመለኮታዊ ሥልጣኑ ሞትን አሸንፎ ሲነሳ ግን አምላክነቱን ኃያልነቱን ገልጧልና፡፡ እንዲሁም ክርስቶስ የተናገረው ያስተማረው ሁሉ ማጠቃለያው ትንሳኤው ስለሆነ ነው፡፡” (መልከጼዴቅ(አባ)፡፡1984፡፡ትምህርተ ክርስትና ፪ኛ፡፡አዲስ አበባ፡፡ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ድርጅት፡፡ገጽ.59

     ከመሠረታውያን የክርስትና ትምህርት አንዱና ዋናው የጌታን ትንሳኤ ማመንና መቀበል ነው፡፡የጌታን ትንሳኤ አለማመን ወይም መጠራጠር በጠቅላላ ክርስትናን እንደመካድ ይቆጠራል፤ከመናፍቃን እንደአንዱም ያስደምራል፡፡“ክርስቶስ ካልተነሳ እምነታችን ከንቱ ናት እስከአሁን ድረስ በኃጢአት አለን” ማለትን ያስደፍራል፡፡(1ቆሮ.15፥17) የክርስትና እምነት መገለጥ ነው፤እግዚአብሔር ራሱን በልጁ ገለጠልን፤ራሱ እግዚአብሔርም ከእኛ እንደአንዱ ሆኖ በእኛ መካከል ለእኛ ተገለጠ፡፡የዚህ ትምህርትና እምነት መደምደሚያ የተስፋውን ነገር ስናምን ነው፡፡ትልቁ የተስፋ ትምህርት ደግሞ የክርስቶስን ትንሳኤ በማመን የሙታንን ትንሳኤ ተስፋ ማድረግ ነው፡፡“የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለንና”፡፡(አንቀጸ ሃይማኖት)

Tuesday, 22 April 2014

"ዘፋኝ" ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ምኗ ነው?

Please read in PDF :- zefagn lebetekiristiyan mnua new?
ከሰሞኑ አንድ ዘፋኝ “ከወንጌላውያን ህብረት አብያተ ክርስቲያናት አባል ነህ” ያሉትን ድህረ ገፆችና  መገናኛ ብዙሀን እንደሚከሰና እርሱ “ኦርቶዶክሳዊ” እንደሆነ ማረጋገጫ እንዲሰጡት፤ይቅርታ  እንዲጠይቁትም ሊያደርግ  እንዳሰበ ከመገናኛ  ብዙሀን  ሰምተናል፡፡“ተደንቀናልም”፡፡ ለመሆኑ “ዘፋኝ” ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን  ምኗ  ነው? አማት ወይስ ምራት? አጎት ወይስ  አክስት? “የወንጌላውያን ህብረት አብያተ ክርስቲያናት” ዓለም  ያከበረቻቸው  ሰዎች ሲመለሱላቸው “የሚደሰቱት”፤ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ዓለም ያከበረቻቸውን እርሷም አብራ በመመቻመች የሚዘልቁት እስከመቼ  ነው? (ምነው የትም በጭፈራ እያሳለፉ የዚህ እምነት ተከታይ ነበርኩ ዛሬ ጌታ “ተገለጠልኝ” ማለት አልበዛም እንዴ?)

    አንደራደርም ፤“ዘፋኝነት” (አዲሱ “የቤተ-ክርስቲያናችን  መጽሐፍ  ቅዱስ” ባይጠቅሰውም) የሥጋ ሥራ ነው፡፡(ገላ.5፥21) የሥጋን ሥራ የሚያደርግ ሁሉ ደግሞ የእግዚአብሔርን  መንግስት  አይወርስም፡፡ (1ቆሮ. 6፥11) በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግስትም ርስት የለውም፡፡(ኤፌ.5፥5)፡፡እርግጥ ነው በቀደመው ዘመን ሁላችን የኃጢአት ባርያዎች፤ የሞትም አገልጋዮች ነበርን፡፡ ነገር ግን ዛሬ ከዚያ ከምናፍርበትና ከምንፀፀትበት ህይወታችን ያተረፍነው ምንም ፍሬ ስለሌለን፤ መጨረሻውም ሞት እንደሆነም ስላመንን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆነን አሁን ከኩነኔ ነፃ ነን፡፡(ሮሜ 6፥20፤8፥1) ባዕለጠጋው እግዚአብሔር  ‹‹ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩም የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጠን፤ በፀጋውም አዳነን››፡፡(ኤፌ.2፥4-6)