ሰውየው አስቀድሞ መጠሪያው “Faith World Church - የእምነት ዓለም ቤተክርስቲያን” በተባለ፣ በአኹን ወቅት
ደግሞ “World Healing Center Church - የዓለም የፈውስ ማዕከል ቤተክርስቲያን” የሚል ስያሜ የተሰጠው የግል “ቤተ ክርስቲያን” ያለውና “የብልጽግና
ወንጌልን” አቀንቃኝ “ንጥጥ ባለጠጋ” ነው። ከባለጠግነቱና ከቅምጥልነቱ የተነሣ፣ የሂን የወንድም ልጅ የኾነው
ፓስተር ኮስቲ ሂን በርሱ ቤት ተጠልሎ ሳለ ያየውን ሲናገር፣ ቅዱስ ጳውሎስና
እነርሱ የሚለያዩበትን አንድ እውነት፣ “እኛ የጳውሎስን አይነት ወንጌል አንሰብክም ነበር።” በማለት ገልጦታል።[1]
በምስክርነቱ ላይ ኮስቲ ሂን፣ እሱ እና ቤተሰቡ የያዙትን ውድ መኪናዎች እና ውድ ቤቶችን እና በጉዞው ዙሪያ ስላለው የቅንጦት ኹኔታ
ገልጦአል።[2]
ኮስቲ ሂን የአጎቱን የብልጽግና ወንጌል እና አስተምህሮ በመተቸት ብዙዎቹ ትንቢቶቹ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚቃረኑ ጽፎአል።[3]
ኮስቲ ሂን በሰጠው ምስክርነት፣ “በሒን ቤተሰብ ግዛት ውስጥ ማደግ
ማለት፣ በተከበረ ቤተሰብ እና ማፊያ መሐል እንደ መኖር ማለት ነው። የእኛ የአኗኗር ዘይቤ ቅንጦተኛ፣ ታማኝነታችን የሚከበር
እና የወንጌላችን አይነት ደግሞ ትልቅ ቢዝነስ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌላችን አንዱ አካል ይሁን እንጂ፣ ከነገሥታት
ንጉሥነቱ ይልቅ እንደ ምሥራቃዊ አስማት ጂኒ ነበር። ከእርሱ ጋር በሚገባ ከተጣበቅህ (ገንዘብ ብትለግስ እና በቂ እምነት
ቢኖርህ)መንፈሳዊ ውርስ ማግኛ በር ይከፈትልሀል። “የእግዚአብሔር ዓላማ ለራሱ ክብር ሳይኾን ለእኛ ጥቅም ነው። ጸጋው ከኃጢአት
ነጻ ሊያወጣን ሳይኾን፣ ሀብታም ሊያደርገን ነው፤ ለእኛ የሰጠን የተትረፈረፈ ኑሮ ገና የሚመጣ አይደለም፤ አኹን ነው!” ብለን
ብልጽግና ወንጌልን ኖረናል” ይላል።
በተጨማሪም፣ ኮስቲ ሂን የሂንን አገልግሎት “አሰዳቢ እና ተሳዳቢ”፣
ድሆችን እና አቅመ ደካሞችን የሚበዘብዝ፣ እና “በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን እያስጨነቀ ያለ እጅግ የጥላቻና አስጸያፊ የሐሰት
ትምህርት” በማለት ይጠራዋል።[4]
እጅግ በሚያስደንቅ መንገድ በመስከረም 2019 ዓ.እ. ቤኒ ሂን፣ በብልጽግና ነገረ መለኮት እንደማያምንና ማስተማር ለማቆም
እንደ ወሰነ ብሎም መሳሳቱን ተናግሮ ነበር።[5]
ከዚህ ባሻገር ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሰውየው ዋና ዋና ኑፋቄዎች
ናቸው፣
· “… አዲስ ፍጥረት ይህን ማንነት ይመስላል፤ በመንፈስ ሞተ! … ኢየሱስ
ክርስቶስ የሚሞተው መንፈሳዊ ሞት እንደሆነ ተረድቶአል። ከሰይጣን ተፈጥሮ ጋር በአንድነት … መንፈሳዊ ሞት ምንድን ነው?
መለያየት ከእግዚአብሔር ዘንድ”[6] ቤን ሂን የዚህ ትምህርት ውጤቱ እስከ ምን አድርሶታል ብንል፣
የክርስቶስን ፍጹም ሰውነት እስከ መናቅ ያደርሰዋል፤ እንዲህ ይላል፣ “መንፈስ ቅዱስ አብሮ ባይኖር ኖሮ ኢየሱስ ኃጢአት በሠራ
ነበር” በማለት።[7]
ነገር ግን ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን፣ “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው
ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” (ኢሳ. 9፥6) የተባለለት
ሲኾን፣ በአዲስ ኪዳን ደግሞ፣ “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር
አልቈጠረውም፥” (ፊል. 2፥6) ተብሎለታል። ክርስቶስ ሞቱም የሥጋ ሞት እንጂ መንፈሳዊ ወይም ከሰይጣን ተፈጥሮ ጋር አንድ
የኾነ ሞት አልነበረም፤ (ቈላ. 1፥21፤ ዕብ. 5፥7፤ 10፥10፤ 1ጴጥ. 4፥1-2)።[8]
· ቤንሂን ሰው “ትንሹ አምላክ” እንደ ኾነ በግልጥ ያስተምራል፤ እንዲህ በማለት፣
“… ዳግመኛ ስትወለድ ቃል በአንተ ሥጋ ኾነ። እና ከሥጋው ሥጋ ነህ፤ የአጥንቱ አጥንትም ነህ። ኢየሱስ አለኝ ብላችሁ እንዳትነግሩኝ ...
አለኝ አትበል። ይልቁን አንተ በላቸው፦ ‘እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ነኝ’ …በል”።[9] በሌላ ስብከቱም፣ “… ክርስቲያን ነኝ ስትል ‘እኔ መሲህ ነኝ’ እያልክ
ነው። የዕብራይስጡ እኔ ትንሽ መሲህ ነኝ፤ በምድር ላይ መራመድ በሌላ አነጋገር ይህ አስደንጋጭ መገለጥ ነው። … እንደዚህ
ልበል? በምድር ላይ የሚሮጥ ትንሽ አምላክ…”[10] ይላል።
ሰውየው ክርስቶስን የሚያገለግል ቢመስልም፣ ክርስቶስን በመናቅ ወደር የለውም። እኛ በምንም መንገድ አምላክ፤ በማናቸውም
የጸጋ አሰላል “ትናንሽ አማልክት” ልንኾን አንችልም። እኛ ፍጡራን ነን፤ ምንም ዳግመኛ ብንወለድ እኛ የእግዚአብሔር ፍጥረት በጸጋ
የዳንን ሰዎች ነን፤ አዎን ሰዎች ብቻ ነን። ፈጽሞ ክርስቶስን መኾን የማንችል የክርስቶስ ባሪያዎችና የእጁ ሥራዎች ነን፤ በርሱ
የዳንን ለርሱም የምንኖር!
·
በሌላ
አንድ ትምህርቱ ላይ፣ በአካል ሦስት የኾኑት እያንዳንዳቸው የመለኮት አካላት በየራሳቸው ሥላሴ እንደ ኾኑም ያስተምራል።[11] በርግጥ ቤን ሂን ይህን በግልጥ ሲያስተምር፣ ይህ በእኛ አገር ባለማወቅና ባለማስተዋል አንዳንዶች “ሥላሴዎች”
ብለው እንደሚጠሩት ነው። ቤን ሂን በሌላ ትምህርቱ ደግሞ፣ የሥላሴ የአካል ሦስትነት የተረዳበት መንገድ አሳዛኝ ነው፤ ፍጹም
አንድነት የሌላቸውና በየራሳቸው ጸጉር፣ ዓይኖች፣ ሥጋና መንፈስ ያላቸው መኾኑን በመጥቀስ ያስተምራል።[12]
ትምህርተ ሥላሴ በቅዱሳት መጻሕፍት የሰፋና የጠለቀ አስደናቂና ውብ ትምህርት ነው፤ የአካል ሦስትነት (አብ፣ ወልድ፣
መንፈስ ቅዱስ) በመለኮታዊ አንድነት (በአገዛዝ፣ በሥልጣን፣ በመፍጠር፣) የተዋበ ነው፤ ፍጹም ሦስትነት ከመለኮታዊ አንድነት
አይነጠልም፤ መለኮታዊ አንድነት፣ አካላዊ ሦስትነትን አይጥልም። በፍጥረት ጊዜ አብ ያሰበውን ወልድ ፈጠረው፤ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ
አጸናው፤ አስዋበው፤ አደራጀው። በማዳንም ጊዜ፣ አብ ዓለሙን ለማዳን ሲወድድ፤ ወልድ በተለየ አካሉ መጥቶ ሥጋን ለብሶአል፤
መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የወልድን ማዳን ለዓለም ናኝቶአል።
ከዚህም ውጭ ሰውየው ኢየሱስ በሲዖል ውስጥም ዳግመኛ መወለዱን፣
አማኞች ጨርሶ ሕመም እንደሌለባቸው፣ እግዚአብሔር ባሳየው ራዕይ “ድህነት ፍጹም አጋንንት እንደ ኾነና”[13] አያሌ ሌሎች የስህተት ትምህርቶችን የሚያስተምር ሰው ነው።
ይህ ሰው ነው ወደ ኢትዮጵያ ምድር የሚመጣና “ስብከትን ሊሰብክ ትንቢትን ሊያመጣ” የተባለ። ነገር ግን ከሐሰተኛ ነቢያት ተጠበቁ፤
ተጠንቀቁ ማለትን ዘወትር አንተውም!
ክርስቶስን እጅግ ከሚወድዱት ኹሉ ጋር ጸጋና ምሕረት ይኹን፤
አሜን።
[1] Hinn, Costi (20
September 2017. "Benny Hinn Is My Uncle, but Prosperity Preaching Isn't for Me". Christianity Today. Retrieved 10
April 2020.
[2] Hinn, Costi (26 October 2017). Televangelist's nephew criticizes uncle. CNN. Retrieved 10 April 2020.
[3] Hinn, Costi (20
September 2017). "Benny Hinn Is My Uncle, but Prosperity Preaching Isn't for Me". Christianity Today. Retrieved 10
April 2020.
[4] "Costi Hinn Exposes the Most
Abusive Kind of False Teaching Today". The Gospel Coalition. 27
August 2019. Retrieved 10 April 2020.
[5] Silliman, Daniel (7 September 2019). "Benny Hinn Renounces His Selling of God's Blessings. Critics Want
More". Christianity
Today. Retrieved 27 August 2024.
[6] New Creation in Christ sermon, late 1988
[7] Good Morning Holy Spirit, first edition, 1990, p. 135
[8] አቤንኤዘር ተክሉ፤ የእምነት
እንቅስቃሴ የዛሬዪቱ ቤተ ክርስቲያን ፈተና፤ 2010 ዓ.ም።
[9] Our Position in Christ#2, 1990, ኹለተኛው ካሴት
[10] Praise-a-Thon, TBN, 6th November' 90
[11] Benny Hinn, TBN, 3rd October 1990
[12] Orlando Christian Centre, Oct 13th 1990
[13] Praise-a-Thon, TBN, April 1990
.jpg)
ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ ❤❤❤❤❤❤❤
ReplyDelete